Monday, March 4, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊሁለተኛው የአየር ብክለት መከታተያ ጣቢያ በአዳማ ተቋቋመ

ሁለተኛው የአየር ብክለት መከታተያ ጣቢያ በአዳማ ተቋቋመ

ቀን:

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ አምስት ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገበትን ሁለተኛውን የአየር ብክለት መከታተያና መመዝገቢያ ጣቢያ በአዳማ ከተማ አቋቋመ፡፡ ጣቢያው መጋቢት 14 ቀን 2008 ዓ.ም. በተከናወነ ሥነ ሥርዓት ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡

በአዳማ ከተማ የተቋቋመው ይህ የአየር ብክለት መከታተያ ጣቢያ በዋነኛነት ከተሽከርካሪዎችና ከኢንዱስትሪ የሚወጡ በካይ የሚባሉ የከባቢ አየር ጋዞችን የክምችት መጠን ይመዘግባል፡፡

‹‹ይህ በአዳማ ከተማ የተተከለው የአየር ብክለት መከታተያና መመዝገቢያ ጣቢያ የተገጠሙለት ዋና መሣሪያዎች አምስት ናቸው፡፡ እነዚህም የኦዞን፣ የካርቦን ሞኖኦክሳይድ፣ የናይትሮጅን ኦክሳይድ፣ የሰልፈርና የልዩ ልዩ ብናኞች መለኪያና መመዝገቢያ መሣሪያ ናቸው፤›› ሲሉ በብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ የሚቲዎሮሎጂ ጥናትና ምርም ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አባተ ጌታቸው ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በተለይ ከመተንፈሻ አካላት ጤና ጋር በተያያዘ በአሁኑ ጊዜ በአየር ብክለት ሳቢያ በዓለማችን የተለያዩ ጉዳቶች እየደረሱ እንደሆነ ያብራሩት አቶ አባተ፣ የብክለት መጠኑ ምን ያህል ነው ከሚለው መረጃ በመነሳት አስቀድሞ የመከላከል ሥራዎችን ለማከናወን ጣቢያው ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ መረጃው እየተደራጀና እየተጠናከረ ሲሄድ ደግሞ ትንበያ መስጠት እንደሚያስችል አመልክተዋል፡፡

ከዚህ ቀደም የአየር ብክለት መከታተያና መመዝገቢያ ጣቢያ በአዲስ አበባ የተገነባ መሆኑን ከዚህ ጣቢያ የሚገኘው መረጃ ለዶክትሬትና ለሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ለተለያዩ ጥናታዊ ሥራዎቻቸው እየተጠቀሙበት እንደሆነ፣ መጠኑን ደግሞ ለሚመለከታቸው አካላት እያሳወቁ መሆናቸውን አቶ አባተ ገልጸዋል፡፡

አዲስ አበባ ከተተከለው መሣሪያ በተገኘው መረጃ መሠረት መረዳት የሚቻለው በተፈጥሮ ይገኛሉ ተብሎ ከተቀመጠው ደረጃ አንፃር የአደገኛ ጋዞች ቁጥር በከባቢ አየር ውስጥ በጣም እየጨመረ እንደመጣም ተገልጿል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት አገሮች የየራሳቸውን ደረጃ እንዲያወጡ ምክር የሚለግስ ሲሆን፣ ከዚህ አንፃር አውሮፓም ሆነ አሜሪካ የራሳቸው ደረጃ አላቸው፡፡ ‹‹ምንም እንኳን ይህ ደረጃ በአገር ውስጥ ባይወጣም ነገር ግን ሌሎች አገሮች ካወጡት ደረጃ ጋር ተቀራራቢ የሆነና ከፍተኛ የሆነ ብክለት እየተመለከትን ነው፤›› በማለት አቶ አባተ ገልጸዋል፡፡

በዋናነት ለብክለት መንስዔ የሚሆኑ ከተሽከርካሪዎችና ከኢንዱስትሪዎች የሚወጡ በካይ ጋዞች ስለሆኑ፣ በዋና ዋና ከተሞች ይህን ዓይነት የአየር ብክለት መከታተያና መመዝገቢያ መሣሪያ ለመትከልና የክትትል ሥራዎችን ለማከናወን ዕቅድ መያዙን አቶ አባተ ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ የሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት በ19ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ አገር ውስጥ በገቡ ሚስዮናውያን አማካይነት በአዲስ አበባ አካባቢ በተቋቋሙ የሚቲዎሮሎጂ መረጃ መሰብሰቢያ ጣቢያዎች፣ በአንበጣ መከላከያና በእርሻ ማስፋፊያ ጽሕፈት ቤቶች ሥራዎች ጋር ተቆራኝተው የተመሠረቱ ሥራዎች ሲከናወኑ ነበር፡፡

የሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት ለሌሎች ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች የሚኖረውን ጠቀሜታ በመገንዘብ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ የሌሎች ዘርፎች ተጠቃሚዎች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ መንግሥት ብሔራዊ የሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት ድርጅትን ታኅሳስ 23 ቀን 1973 ዓ.ም. በአዋጅ አቋቁሟል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር ሲጨምር የሚኒባስ ታክሲዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ሊታሰብበት ይገባል

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ የሚባለውን ድርሻ...

ሃምሳ ዓመታት ያስቆጠረው አብዮትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጣ ውረድ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች የዴሞክራሲ ለውጥ ጥያቄ የሚነሳው ከፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተፈጸመው ሕገወጥ ተግባር ምንድነው?

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ፣...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ውሳኔ ተላለፈ

ፕሬዚዳንቷና ዋና ጸሐፊው ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል ከአዲስ አበባ ንግድና...