Sunday, April 21, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ብሔራዊ ባንክ ከንግዱ ማኅበረሰብ አባላት ጋር በፋይናንስ ችግሮች ላይ ሊወያይ ነው

ተዛማጅ ፅሁፎች

የንግድ ማኅበረሰቡ በፋይናንስ ተቋማት የብድር አሰጣጥና ሌሎች ችግሮች ላይ ቅሬታዎችና አቤቱታዎች በማቅረባቸው፣ ከብሔራዊ ባንክ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ምክክር ሊያደርጉ ነው፡፡

ሚያዚያ 8 ቀን 2010 ዓ.ም. ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በሰጡት መመርያ፣ በፋይናንስ ተቋማት ላይ በቀረቡት አቤቱታዎች ላይ የብሔራዊ ባንክና የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ምላሽ እንዲሰጡበት አሳስበው ነበር፡፡

ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ማሳሰቢያ ተፈጻሚ እንዲሆን የተሰጠው የጊዜ ገደብ እስከ ግንቦት 30 ቀን 2010 ዓ.ም. ቢሆንም፣ እስካሁን ሳይካሄድ ቆይቷል፡፡

የንግድ ማኅበረሰቡን አቤቱታ ሲያሰባስብ ከቆየው የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ በፋይናንስ ተቋማት አገልግሎቶች ላይ የሚደረገው የምክክር መድረክ ሐሙስ ሐምሌ 12 ቀን 2010 ዓ.ም. እንዲካሄድ ተወስኗል፡፡

ይህ የምክክር መድረክ ላይ ብድርና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ችግር ገጥሞናል ብለው ላመለከቱ የንግዱ ማኅበረሰብ አባላት የፋይናንስ ተቋማት ምላሽ የሚሰጡበት ስለሆነ፣ የሁሉም ባንኮች የሥራ ኃላፊዎች በውይይቱ ላይ ይገኛሉ ተብሏል፡፡

የንግዱ ማኅበረሰብ በግብርና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ያለውን ጥያቄ በተመለከተ ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ጋር ተመሳሳይ ውይይቶች የተደረጉ ሲሆን፣ ከመሬት አቅርቦትና አስተዳደር ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን በተመለከተ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር ሊደረግ የታቀደው ውይይት እስካሁን አልተደረገም፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች