Monday, July 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ሥነ ፍጥረትእንቁራሪት

እንቁራሪት

ቀን:

እንቁራሪት አኗኗራቸው በወንዝ አካባቢ ነው፡፡ በእንቆቅልሽ ‹‹ወንዝ ለወንዝ ሠርገኛ አረህ ላረህ ክራረኛ›› እወቅልኝ ሲባል መልሱ እንቁራሪት ይሆናል፡፡

በማንይንገረው ሸንቁጥ በተዘጋጀው ‹‹ባለአከርካሪዎች›› መጽሐፍ እንደተገለጸው፣ እንቁራሪቶች ጅራት የላቸውም፡፡ ርባታቸው የተወሰነው በውኃ አካባቢ ብቻ በመሆኑ ከውኃ አካባቢ ብዙም ርቀው መሄድ ያዳግታቸዋል፡፡ ከዚያም በተጨማሪ ቆዳቸው ለስላሳና ውኃን የሚያተን በመሆኑ በየጊዜው ውኃ ውስጥ ገባ ወጣ እያሉ ብቻ ነው ሊኖሩ የሚችሉት፡፡ በዝያቸው የታወቁ ናቸው፡፡ ለዚህም የኋላ እግራቸው ረዥም መሆን ረድቷቸዋል፡፡ ሦስት ዓይነት የአተነፋፈስ (አየር ማስገቢያና ማስወጫ) ዘዴ አላቸው፡፡ እነርሱም በቆዳ፣ በሳንባ ሲሆን፣ በተጨማሪም የዕጭ ዕድገት ደረጃቸው ላይ በስንጥብ ይተነፍሳሉ፡፡

እንቁራሪቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ ለምግብነት ጥቅም ላይ በመዋል የታወቁ ናቸው፡፡ ለምግብነት ከሚውለው የአካላቸው ክፍል በዋነኝነት የኋለኛ እግራቸው በጣፋጭነቱ ይጠቀሳል፡፡ ከእንቁራሪቶች በተጨማሪ ሳላማንደር በጃፓንና ተዘውታሪ ምግብ ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሚዲያው በሕዝብ የህሊና ችሎት ከተዳኘ በቂ ነው!

መሰንበቻውን ድንገት ሳይታሰብ ያለ ማስጠንቀቂያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ...

የባህር በር ጉዳይ

በታምሩ ወንድም አገኘሁ ድሮ ድሮ ገና ልጅ ሆኜ ፊደል እንደቆጠርኩ...

አገሩ ፖለቲካዊ ስክነትና መደማማጥ ያስፈልገዋል

በንጉሥ ወዳጀነው    ኢትዮጵያ የሁላችንም የጋራ ቤት ነች፡፡ ‹‹ጥያቄዬ ተመለሰልኝ››፣...

የመንግሥት የሰብዓዊ መብት ተቋም ለምን የመንግሥት ሚዲያን ማስተማር አቃተው

በገነት ዓለሙ የአገራችን የ2016 የበጀት ዓመት መሰናበቻና የአዲሱ የ2017 በጀት...