Sunday, April 14, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊዕውቅና ለሰብዓዊ አገልግሎት

ዕውቅና ለሰብዓዊ አገልግሎት

ቀን:

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር፣ ‹‹ለውጥን እንደግፍ›› በሚል መሪ ቃል ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም. በመስቀል አደባባይ በወጡ ሠልፈኞች ላይ በደረሰው የቦንብ ጥቃት ሕይወት የማዳንና ሰብዓዊ አገልግሎት ለሰጡ 115 በጎ ፈቃደኞችና ለቀይ መስቀል አመራሮች ዕውቅና ሰጠ፡፡ ሐምሌ 4 ቀን በተከናወነው ሥነ ሥርዓት የማኅበሩ ፕሬዚዳንት አቶ አበራ ቶላ፣ በሠልፉ ለነበሩ 167 ተጎጂዎች የመጀመሪያ ሕክምና ዕርዳታ ሰጥቶ መሸኘቱን፣ ለ117ቱ ደግሞ የነፍስ አድን ሥራ እየሠራ በአቅራቢያ ወደሚገኙ ሆስፒታሎች ማድረሱንም ተናግረዋል፡፡ ሐምሌ 1 ቀን 1927 ዓ.ም. የተመሠረተው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር  የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ተቋም 48ኛ አባል በመሆን መስከረም 18 ቀን 1928 ዓ.ም. ተመዝግቧል፡፡ ማኅበሩም ሲመሠረት 300 የበጎ ፈቃደኛ አባላት የነበሩት ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት 6.1 ሚሊዮን አባላትና 47 ሺሕ በጎ ፈቃደኞች እንዳሉት ከማኅበሩ የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡ ፎቶዎቹ የዕውቅናውን ሥነ ሥርዓት በከፊል ያሳያሉ፡፡ (ፎቶ ታምራት ጌታቸው)

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የም እና መስህቦቿ

በቱባ ሀገሬ የም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ የሚገኝ ሲሆን ከአዲስ አበባ በ239...

ከሴራ ፖለቲካ በስተጀርባ ጥቅማቸውን የሚያስጠብቁ ኃይሎች

በመኮንን ሻውል ወልደ ጊዮርጊስ የአፄ ቴዎድሮስ መንግሥት የወደቀው ከመቅደላ በፊት...

ስለዘር ፖለቲካ

በሀብታሙ ኃይለ ጊዮርጊስ  ‹‹በቅሎዎች ዝርያችን ከአህያ ነው እያሉ ይመፃደቃሉ›› የጀርመኖች...

አማርኛ ተናጋሪዋ ሮቦት

በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው የሳይንስ ሙዚየም፣ ሚያዝያ 2 ቀን...