Monday, October 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ንብረት እንዳይንቀሳቀስ ታገደ

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ንብረት እንዳይንቀሳቀስ ታገደ

ቀን:

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ሦስተኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት፣ ላለፉት ዘጠኝ ወራት የቤት ኪራይ መክፈል ያልቻለው አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ማተሚያ ማሽኑን እንዳይሸጥ፣ እንዳይለውጥና ለሦስተኛ ወገን እንዳያሳልፍ እንዲሁም አሁን ከሚገኝበት ቦታ እንዳይወጣ አገደ፡፡

ፍርድ ቤቱ ይህን የዕግድ ትዕዛዝ ያስተላለፈው በቤቱ አከራይ አቶ ዘካሪያስ ብርሃኑ አማካይነት በቀረበ ክስ ነው፡፡ ፍርድ ቤቱ ታኅሳስ 4 ቀን 2008 ዓ.ም. በአራዳ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 16 የቤት ቁጥር አዲስ በካርታ ቁጥር አ/13/14/0564 ተመዝግቦ የሚገኘውን ቤት ፓርቲው ለአቶ ዘካሪያስ እንዲያስረክብ ወስኗል፡፡

በዚህም መሠረት አቶ ዘካርያስ ብርሃኑ 33,494 ብር የወጪ ኪሳራ ጠይቀዋል፡፡ የፓርቲው ማተሚያ ማሽን እስከ 33,494 ብር የሚያወጣ መሆን አለመሆኑን በባለሙያ ግምት ከተረጋገጠ በኋላ እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ፣ ለሦስተኛ ወገንም እንዳይተላለፍና ከከሳሽ ቤት እንዳይወጣ ታግዶ እንዲቆይ መታዘዙን የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ያስረዳል፡፡

ከሳሽ አቶ ዘካርያስ ብርሃኑ ለበርካታ ወራት ሲንከባለል በቆየው ውዝግብ የተነሳ ማግኘት የሚገባቸውን ጥቅም እንዳጡ ለሪፖርተር የገለጹ ሲሆን፣ ‹‹ለፍትሕና ለዴሞክራሲ እታገላለሁ የሚል ፓርቲ እንዲህ የአንድን ግለሰብ መኖሪያ ቤት ይዞ አልለቅም ማለቱ እጅግ ግራ የሚያጋባና ቆሜለታለሁ ከሚለው መርህ ጋር የሚጋጭ  ነው፤›› በማለት አስረድተዋል፡፡

የአከራይና የተከራይ ወገኖች ውዝግብ የተጀመረው በምርጫ ቦርድ ዕውቅና የተነፈገው የፓርቲው የቀድሞ አመራር ፓርቲውን ለቅቆ ከወጣ በኋላ፣ በምርጫ ቦርድ ዕውቅና የተሰጠው የእነ አቶ ትዕግሥቱ አወሉ አመራር ፓርቲውን ከተረከበ ጀምሮ ነው፡፡

የቤቱ አከራይ የሆኑት አቶ ዘካርያስ የቤት ኪራይ ዋጋ እንደሚጨምሩ በመግለጽ ለፓርቲው አመራሮች ማሳወቃቸውን፣ ፓርቲው ግን በጭማሪው ያልተስማማ መሆኑን መግለጹና ክፍያ እንደማይፈጽም ማስታወቁን መዘገባችን የሚታወስ ነው፡፡ የፓርቲውን በአሁኑ ወቅት አንድነት ፓርቲን የሚመሩትን አቶ ትዕግሥቱ አወሉን ለማግኘት የተደረገው ተደጋጋሚ ሙከራ አልተሳካም፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተመድንና ዓለም አቀፋዊ ሕግን ከእነ አሜሪካ አድራጊ ፈጣሪነት እናድን!

በገነት ዓለሙ በእኔ የተማሪነት፣ የመጀመርያ ደረጃ ተማሪነት ጊዜ፣ የመዝሙር ትምህርት...

የሰላም ዕጦትና የኢኮኖሚው መንገራገጭ አንድምታ

በንጉሥ ወዳጅነው ፍራንክ ቲስትልዌይት የተባሉ አሜሪካዊ ጸሐፊ ‹‹The Great Experiment...

ድህነት የሀብት ዕጦት ሳይሆን ያለውን በአግባቡ ለመጠቀም አለመቻል ነው

በአንድነት ኃይሉ ድህነት ላይ አልተግባባንም፡፡ ብንግባባ ኖሮ ትናንትም ምክንያት ዛሬም...