Wednesday, December 6, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ውድ የተባለው የኮንዶሚኒየም ንግድ ቤቶች ጨረታ በከፊል ተሰረዘ

ተዛማጅ ፅሁፎች

– ባንኮች በርካታ የንግድ ሱቆች ተቆጣጥረዋል

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለገበያ ካቀረባቸው 2,398 የኮንዶሚኒየም ንግድ ቤቶች የ481 ንግድ ቤቶች የጨረታ ሒደት ሕጋዊ አልነበረም በማለት እንዲሰረዝ አደረገ፡፡

ከተቀሩት ንግድ ቤቶች ውስጥ 1,643 ያህሉ ሕጋዊ መንገድ የተከተሉ በመሆናቸው ለአሸናፊዎች እንዲተላለፉ በጨረታ ኮሚቴው ተወስኗል፡፡ ሌሎች 274 ንግድ ቤቶች በቂ ተጫራች ስላልቀረበላቸው ሊተላለፉ አለመቻላቸው ተገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ቤቶች አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ መስፍን መንግሥቴ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ 481 ንግድ ቤቶች ሕጋዊ የጨረታ ሒደት ባለመከተላቸው ተሰርዘዋል፡፡

የእነዚህ ንግድ ንግድ ቤቶች ጨረታ የተሰረዘው መመሳጠር፣ የስም ለውጥ፣ ዝቅተኛ ሲፒኦ ማቅረብ የመሳሰሉ ሕገወጥ ድርጊቶች በመታየታቸው ምክንያት መሆኑን አቶ መስፍን ተናግረዋል፡፡

በታኅሳስ 2008 ዓ.ም. ይፋ የተደረገው ኮንዶሚኒየም ንግድ ቤቶች ጨረታ ጥር መጀመርያ ላይ ተከፍቷል፡፡ በወቅቱ ከፍተኛ የመጫረቻ ዋጋ የቀረበበት የኮንዶሚኒየም ንግድ ቤቶች ጨረታ የዋጋ ክብረ ወሰን የተመዘገበበት ነው፡፡ በዚህ ጨረታ ባንኮች በስፋት ተሳትፈዋል፡፡ ንብ ባንክ፣ ብርሃን ኢንተርናሽናል ባንክ፣ አዲስ ኢንተርናሽናል ባንክና ናይስ ኢንሹራንስ 14 ያህል የንግድ ቤቶችን ለማሸነፍ ተወዳድረዋል፡፡ እነዚህ የፋይናንስ ተቋማት አንድ ንግድ ሱቅ ለመግዛት መነሻ ከሆነው 8,405 ብር አሥር እጥፍ የሚሆን የመጫረቻ ዋጋ አቅርበዋል፡፡

በዚህ ጨረታ በልደታ ክፍለ ከተማ መልሶ ማልማት ለቀረቡ 39 ንግድ ሱቆች ከፍተኛ ዋጋ ቀርቦላቸዋል፡፡ በዚህ ጨረታ በአንድ ካሬ ሜትር 101 ሺሕ ብር፣ 72 ሺሕ ብር፣ 64 ሺሕ ብር እና 40 ሺሕ ብር የመጫረቻ ዋጋዎች ቀርበዋል፡፡ ትላልቅ የመጫረቻ ዋጋዎች ያቀረቡት ባንኮች መሆናቸው ታውቋል፡፡

በአጠቃላይ ለጨረታ የቀረቡትን ንግድ ቤቶች ለመግዛት 21 ሺሕ ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ግዥ ፈጽመዋል፡፡ በአራት ቦታዎች ተከፋፍለው ለቀረቡት ቤቶች 655 በአቃቂ ቃሊቲ፣ 20 በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ 20 በኮልፌ ቀራኒዮ፣ 39 በልደታ፣ 45 በአራዳ፣ 1,250 በየካ፣ 366 ደግሞ በቦሌ ክፍላተ ከተሞች ነው፡፡

ለሽያጭ የቀረቡት ቤቶች ከ33 ካሬ ሜትር እስከ 65 ካሬ ሜትር ስፋት ያላቸው ናቸው፡፡ ይህ ጨረታ ከከፍተኛ የመጫረቻ ዋጋ በተጨማሪ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ቤቶች ለጨረታ የቀረቡበት ነው፡፡

ከዚህ ቀደም በክብረ ወሰን ደረጃ የተያዘው በዚሁ በልደታ ክፍለ ከተማ መልሶ ማልማት ክልል ውስጥ በካሬ ሜትር የቀረበው 56,164 ብር የመጫረቻ ዋጋ ነበር፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች