Wednesday, February 28, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልየበዓላቱ ማስታወሻ

የበዓላቱ ማስታወሻ

ቀን:

ቤተእምነቶችና ብሔረሰቦች ካሏቸው መገለጫዎች በቀላሉ ለተመልካች ተደራሽ የሚሆነውና የአባላቱ ሁሉ ተሳትፎ ትኩረት የማይለየው በአደባባይ የሚያከብሩአቸው በዓላት ናቸው የሚለው ሜጋ አሳታሚና አከፋፋይ ማኅበር፣ ‹‹ዝክረ በዓላት›› የተሰኘውን የበዓላት መድበል ለንባብ አብቅቷል፡፡

‹‹የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ቤተእምነቶች የአደባባይ በዓላት›› የሚል ታካይ ርእስ ባለው ቅጽ አንድ መጽሐፍ ውስጥ ስምንት በዓላት ተካትተውበታል፡፡ እነርሱም የኢሬቻ፣ የጊፋታ፣ የፊቼ ጨምበላላ፣ የቡሔ፣ አልከስዬ የሥልጤ የመውሊድ ሥርዓተ ክዋኔ፣ የአሸንዳ፣ አብሱማ የአፋር ሀገረሰባዊ የሠርግ ሥርዓተ ክዋኔ፣ የመስቀል ደመራ በዓላት ናቸው፡፡

አሳታሚው በመግቢያው ላይ እንዳመለከተው፣ የበዓሉ ገጽታዎች በርካታ የአገር ውስጥ ቱሪስቶችን ወደ አገር በመሳብ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጥቅምን ሊያስገኙ ይችላሉ፡፡ በአገር ውስጥ ያሉ የየበዓላቱ አድናቂዎችም በዓላቱ በሚከበሩበት እየተገኙ አንዳቸው ለአንዳቸው ያላቸውን መከባበርና መቻቻል ያሳዩበታል፡፡ ይረኩበታል፡፡ ይሳተፉበታል፡፡ ይህ ደግሞ ማኅበራዊ ፋይዳውን የላቀ ያደርገዋል፡፡  ከቅርብም ከሩቅም የሚመጡ ተመልካቾች ደግሞ ከዚያ የበዓሉ ባለቤት ከሆነው ወገን ጋር ይቀራረቡበታል፤ ይተዋወቁበታልም፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በመጽሐፉ የተካቱት በዓላት፣ ስለበዓላቱ አከባበርና ታሪካዊ አመጣጥ፣ በበዓላቱ ስለሚፈጸሙ ክዋኔዎች፣ ስለበዓሉ ባለቤቶች ማንነት፣ በዓሉ ስለሚከበርበት አካባቢያዊ ሁኔታ ወዘተ እጅግ ጠቃሚ ነጥቦች አንስተዋል፡፡ ወደፊትም በሌሎች እትሞች በእነዚሁ በዓላት ያሉ አዳዲስ መረጃዎችና ግልጽ ያልሆኑ ጉዳዮች ቢኖሩ በባለሙያዎችና በአንባቢያን አስተያየት መሠረት እየተሻሻሉ በመውጣት ለምርምርና ጥናትም እጅግ ጠቃሚ እንደሚሆኑ እምነቱ መሆኑን አሳታሚው አመልክቷል፡፡

የመጽሐፉ የሽፋን ዋጋ 55 ብር ነው፡፡

*****

‹‹ዮሬካ››

‹‹ተወልጄ ያደኩት አርሲ በቆጂ ነው፡፡ የዝነኛ አትሌቶች መፍለቂያ በሆነችው የአትሌቶች መንደር› ታዲያ ‹ለምን አትሮጥም› እንዳትሉኝ! እየሮጥኩ ነው፡፡ በጥበብ መንገድ፡፡ በማያልቀው የዕድሜ ዘመን ልክፍት ጎዳና! እየሮጥኩ ነው፡፡ በሜትሮች በማይለካ … በኪሎ ሜትሮች በማይመተር … የጥበብ መንገድ እየሮጥኩኝ ነው፡፡ በሩጫዬ ከያዝኩት የጥበብ ውኃ … ከተጠማች ነፍሴ ላይ … በላዬ ካርከፈከፍኩት የጥበብ ጠብታዎች … እኔን አረስርሰው በዕድሜዬ በመንገድ … የተንጠባጠቡትን እነሆ አቀረብኩላችሁ፡፡›› ያለው ጋዜጠኛ አንዱዓለም ጌታቸው ‹‹ዮሬካ›› ብሎ በሰየመው የግጥም መድበሉ ላይ ነው፡፡

‹‹ምስጋና›› ብሎ ባሰረው ስንኙም እንዲህ ብሏል፡፡

ተመስገን … ተመስገን … ይላል ያገሬ ሰው

ተመስገን … ተመስገን

የመከራ ትንሽ ሆነ

ትልቅ ሲመጣበት

ብሶት ከሸሸው

የባሰ እንዳይመጣበት፡፡

በሳምንቱ መገባደጃ ላይ አደባባይ የወጣው መድበል በውስጡ 50 ግጥሞችን ይዟል፡፡ የሽፋን ዋጋው 30 ብር ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...