Monday, December 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናአቶ ድሪባ ኩማ በካናዳ የኢትዮጵያ አምበሳደር ሆነው እንደሚመደቡ ተሰማ

አቶ ድሪባ ኩማ በካናዳ የኢትዮጵያ አምበሳደር ሆነው እንደሚመደቡ ተሰማ

ቀን:

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ በመሆን ላለፉት አምስት ዓመታት ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ድሪባ ኩማ፣ በካናዳ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሆነው እንደሚመደቡ ታወቀ። አቶ ድሪባ ማክሰኞ ሐምሌ 10 ቀን 2010 ዓ.ም. ከከንቲባነት ሥልጣናቸው በመልቀቅ ኃላፊነታቸውን ምክትል ከንቲባ ሆነው በከተማው ምክር ቤት ለተመረጡት አቶ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) አስረክበዋል።

አቶ ድሪባ ከአዲስ አበባ ከንቲባነታቸው ከመልቀቃቸው አስቀድሞ፣ ባለፈው ሳምንት መጨረሻፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ (/) የባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደርነት ሹመት ከተሰጣቸው ስምንት የቀድሞ የመንግሥት ከፍተኛ አመራሮች መካከል አንዱ ናቸው።

በካናዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው በመሥራት ላይ የሚገኙትን / አስቴር ማሞን የሚተኩ ሲሆን፣ / አስቴር ከአምባሳደርነት ኃላፊነታቸው ለመልቀቅ ጥያቄ አቅርበው ተቀባይነት እንዳገኘ ከሁለት ሳምንት በፊት መዘገባችን ይታወሳል። / አስቴርና ባለቤታቸው በካናዳ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መመደባቸውን ፓርላማው ከወራት በፊት በመተቸት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማስተካከያ እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ በመስጠቱ፣ ሚኒስትሩ ለወ/ አስቴርና በተመሳሳይ ከባለቤታቸው ጋር የቤልጂየም አምባሳደር ሆነው ለተመደቡት አቶ እውነቱ ብላታ ሁለት አማራጮችን ሰጥቶ ነበር።

አማራጮቹም ባልና ሚስት ሆኖ በአንድ ኤምባሲ ኃላፊነት መውሰድ ተገቢ ባለመሆኑ የማስተካከያ ምደባውን እንዲቀበሉ ወይም ወደ አገር ቤት እንዲመለሱ የሚጠይቅ መሆኑን የሪፖርተር ምንጮች አስረድተዋል። / አስቴር ወደ አገር ቤት ለመመለስ በመወሰን መልቀቂያ ማቅረባቸውንና የአቶ እውነቱ ብላታ ባለቤት ደግሞ ማስተካከያ ምደባውን ለመቀበል ወስነው በአየርላንድ ኤምባሲ በከፍተኛ ዲፕሎማትነት መመደባቸውን ከሁለት ሳምንት በፊት መዘገባችን ይታወሳል።

አቶ ድሪባ ኃላፊነታቸውን ካስረከቡ በኋላ ቆየት ብለው ወደ ካናዳ እንደሚያቀኑ ይጠበቃል። በተመሳሳይ በፕሬዚዳንቱ የባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደርነት ሹመት የተሰጣቸው የቀድሞው የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ የነበሩት አቶ ዓለማየሁ ተገኑ፣ በሩሲያ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሆነው እንደሚመደቡ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልጸዋል። አቶ ዓለማየሁ የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን የተከታተሉት በሩሲያ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። አቶ ዓለማየሁ በሩሲያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር በመሆን እስካለፈው ወር ድረስ ሲያገለግሉ የነበሩትንና በዲፕሎማሲ ዘርፍ የረጅም ዓመታት ልምድ ያካበቱትን አምባሳደር ግሩም ዓባይን ተክተው ወደ ሩሲያ እንደሚያቀኑ ይጠበቃል።

አምባሳደር ግሩም በብራሰልስ የአውሮፓ ኅብረት ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር በመሆን በቅርቡ ተመድበው ሥራቸውንም ጀምረዋል። ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ ባለፈው ሳምንት የባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደርነት ሹመት ከሰጧቸው ውስጥ በቅርቡ ከደኢሕዴን ሊቀመንበርነታቸው በፈቃዳቸው የለቀቁት የግብርናና እንስሳት ሀብት ሚኒስትሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ የነበሩት አቶ ያለው አባተ፣ የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት አቶ አብዱልፈታህ አብዱላሂ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ የነበሩት አቶ ዮናስ ዮሴፍ፣ እንዲሁም አቶ እሸቱ ደሴና አቶ አዛናው ታደሰ መሆናቸውን መዘገባችን ይታወሳል። የእነዚህን ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደሮች ምድብ ቦታ ለማረጋገጥ የተደረገው ሙከራ አልተሳካም።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...