Thursday, June 13, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ስፖርትሶሻል ሚዲያው በአትሌቲክሱ ውጤት ላይ ተፅዕኖ ፈጥሯል ተባለ

ሶሻል ሚዲያው በአትሌቲክሱ ውጤት ላይ ተፅዕኖ ፈጥሯል ተባለ

ቀን:

ብሔራዊ አትሌቶችና ሞባይል ሊለያዩ መሆኑም ተጠቁሟል

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በዓለም ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የተመዘገበውን ውጤት አንደሚገመግም አስታወቀ፡፡ በፊንላንድ ታምፔሬ ከሐምሌ 3 እስከ 8 ቀን 2010 ዓ.ም. በተካሄደው የዓለም ወጣቶች አትሌቲክስ  ሻምፒዮና ሶሻል ሚዲያው በፈጠረው ተፅዕኖ  ኢትዮጵያ አራት የወርቅ ሜዳሊያ ማጣቷ ተነግሯል፡፡ ከዚህ በኋላ ማንኛውም ብሔራዊ አትሌት  ሞባይል የሚጠቀም ከሆነ እንደማይመረጥ ጭምር ተብራርቷል፡፡

በፊንላንዱ የዓለም ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና 29 አትሌቶች ያሳተፈችው ኢትዮጵያ ሦስት የወርቅ፣ ሁለት የብርና አራት የነሐስ በድምሩ ዘጠኝ ሜዳሊያዎችን አስመዝግባ ከዓለም አራተኛ፣ ከአፍሪካ ሁለተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች፡፡ ልዑካኑ ማክሰኞ ሐምሌ 9 ቀን አዲስ አበባ ሲገባ በፌዴሬሽኑ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡ የገንዘብ ሽልማትም ተበርክቶለታል፡፡ በሽልማቱ ሥነ ሥርዓት ላይ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ፣ ውጤቱ ፌዴሬሽኑ ባቀደው ልክ ባይሆንም እስከ ዛሬ ውጤት ባልተመዘገበባቸው በመካከለኛ ርቀት የተመዘገበው ውጤት ግን የሚያበረታታ መሆኑን ታናግሯል፡፡

- Advertisement -

ቡድኑ ለሻምፒዮናው ወደ ፊንላንድ ከማቅናቱ አስቀድሞ አትሌቶች፣ አሠልጣኞችና የቡድን አመራሮች በጋራ ውጤቱ ምን ሊሆን እንደሚገባ እንዲሁም የቡድን አባላቱ በአጠቃላይ ሊከተሉት ስለሚገባው ዲሲፕሊን በዝርዝር ቢነጋገሩም   አለመተግበሩን ነው ሻለቃ ኃይሌ የገለጸው፡፡ በዚህም የቡድኑ አሠልጣኞችና የቴክኒክ አባላት ሐምሌ 11 ቀን ውጤቱን የተመለከተ ግምገማ ይኖራቸል ተብሏል፡፡

በመድረኩ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ላቀደው ውጤት መጥፋት ምክንያት ተብሎ ሌላው የተጠቀሰው ሶሻል ሚዲያ ነው፡፡ አትሌቶች ሶሻል ሚዲያ እንዳይጠቀሙ ቀደም ሲል ጀምሮ ሲናገር መቆየቱን የገለጸው ኃይሌ፣ “አወዳዳሪው አካል ያሰለፋችሁት ተገቢ ያልሆነ አትሌት ነው ብሎ ሳይጠይቅ፣ በአንድ ግለሰብ ምክንያት ያውም ኢትዮጵያዊ በሆነ ሰው በሶሻል ሚዲያ አማካይነት በተሠራጨ ወሬ የቡድኑ ሥነ ልቦና በመነካቱ ኢትዮጵያ ማግኘት የነበረባት አራት የወርቅ ሜዳሊያ እንድታጣ ሆኗል፤” ብሏል፡፡

ኃይሌ ከዚህ በኋላ በብሔራዊ የሚታቀፍ ማንኛውም አትሌት በተለይ አኅጉራዊና ዓለም አቀፍ ውድድሮች ሲኖሩ ሞባይል መጠቀም እንደማይቻልም አስረድቷል፡፡ ከቡድኑ ጋር አብረው የተጓዙት የፌዴሬሽኑ ቴክኒክ ዳይሬክተር አቶ ዱቤ ጅሎ በበኩላቸው፣ ውጠየቱ የተጠበቀውን ያህል አጥጋቢ ባይሆንም ቡድኑ በዲሲፕሊን ረገድ ግን ከወትሮው በተለየ ጥሩ እንደነበረ ተናግረዋል፣ ስለ ግምገማው አስፈላጊነትም ተናግረዋል፡፡

ፌዴሬሽኑ ለልዑካን አባላቱ በአጠቃላይ 400 ሺሕ ብር ተሸለመ ሲሆን፤ የወርቅ ሜዳሊያ ላስመዘገቡ ለእያንዳንዳቸው 25 ሺሕ ብር፣ ለብር ሜዳሊያ 18 ሺሕ ብር፣ ለነሐስ 10 ሺሕ ብር እንዲሁም ለዲፕሎማና ለተሳትፎ ስድስትና ሦስት ሺሕ ብር ሸልሟል፡፡ ለአሠልጣኞችና ለቡድን አባላት እንዳስመዘገቡት ውጤትና የሥራ ኃላፊነት የገንዘብ ሽልማቱ ተበርክቶላቸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...