Sunday, April 14, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትበአገር ውስጥ የሊግ ፉክክር የተገደበው የክለቦች ራዕይ

በአገር ውስጥ የሊግ ፉክክር የተገደበው የክለቦች ራዕይ

ቀን:

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከተመሠረተ ሁለት አሠርታትን ደፍኗል፡፡ ሊጉ ይህን የውድድር መርሐ ግብርና ስያሜ ይዞ ከተቋቋመበት ከ1990 ዓ.ም. ጀምሮ አምስት ቡድኖች ሻምፒዮና የሆኑበትን ድል አጣጥመዋል፡፡ ዋንጫውን ቅዱስ ጊዮርጊስ 14 ጊዜ በማንሳት ባለክብረ ወሰን ነው፡፡ ኢትዮ ኤሌክትሪክና ሐዋሳ ከተማ ሁለት ሁለት ጊዜ ዋንጫውን አንስተዋል፡፡ ኢትዮጵያ ቡና፣ ደደቢትና የዘንድሮ አሸናፊ ጅማ አባ ጅፋር አንድ አንድ ጊዜ በማንሳት ይጠቀሳሉ፡፡

በእነዚህ ሁሉ ዓመታት ታዲያ በተለይም ከተወሰኑ ዓመታት ወዲህ የእግር ኳስ ሜዳዎች ዜጎች በእግር ኳሰኞች ክህሎት ተዝናንተውና ተደስተው የሚወጡባቸው መሆኑ ቀርቶ፣ ‹‹የጦር ቀጣና›› እየሆኑ ለሰዎች ማኅበራዊ ግንኙነትና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ጠንቅ ከሆኑ ውለው ካደሩ ሰነባብተዋል፡፡ በአብዛኛው ስታዲየሞችና ማዘውተሪያዎች የእግር ኳስ ጥበብና ብቃት እንዲሁም ችሎታ ለማየትና ለማድነቅ ሳይሆን የጎጥ፣ የዘርና የፖለቲካ መናኸሪያ ሆነዋል፡፡

የውድድር ዓመቱ ፕሪሚየር ሊጉን ዘንድሮ በተቀላቀለው ጅማ አባ ጅፋር አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ ቡድኑ ፕሪሚየር ሊጉን ሁለተኛ ሆኖ ካጠናቀቀውና  ከባለ ክብረ ወሰኑ ቅዱስ ጊዮርጊስ ተሽሎ ሻምፒየን መሆን የቻለው በሦስት የጎል ክፍያ ልዩነት ነው፡፡ ይህ ማለት የፕሪሚየር ሊጉ ቡድኖች በውድድር ዓመቱ ማግኘት ከነበረባቸው 90 ነጥብ ውስጥ፣ አንደኛውና ሁለተኛው ቡድኖች ያስመዘገቡት እኩል 55 ነጥብ ሲሆን፣ ጅማ አባ ጅፋር 23 ጎል ሲያስቆጥር፣ ተከታዩ ቅዱስ ጊዮርጊስ ደግሞ 21 ጎል አስቆጥሯል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ቀደም ብሎ መውረዱን ካረጋገጠው ወልድያ ከተማ ውጪ ላለመውረድ እስከ መጨረሻው ትንቅንቅ ውስጥ የቆዩት አርባ ምንጭ ከተማና ኢትዮ ኤሌክትሪክ 34 እና 35 ነጥብ ይዘው ወራጅ መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ብዙ በተቆጠረበት ተሽለው ከመውረድ የተረፉት ድሬዳዋ ከተማ፣ ወላይታ ድቻ፣ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲና ሐዋሳ ከተማ በእኩል 35 ነጥብና በጎል ዕዳ ተበላልጠው ነው፡፡ ዋንጫውን ያነሳውና ሁለተኛ ሆኖ ያጠናቀቀው ቅዱስ ጊዮርጊስ ደግሞ ማግኘት የነበረበትን 35 ነጥብ በሽንፈት ወይም በአቻ ውጤት አጥቷል፡፡

ሐምሌ 9 ቀን 2010 ዓ.ም. ፍጻሜውን ባገኘው የውድድር ዓመቱ መርሐ ግብር በአዲስ አበባ ቅዱስ ጊዮርጊስና ሐዋሳ ከተማ ተገናኝተዋል፡፡ በውጤት ቀውስ ሲታመስ የከረመውን የክለቦች የፉክክር አቅም መውረድ ዓመቱን ሙሉ ያላስጨነቃቸው የክለብ አመራሮችና ደጋፊዎች እንዲሁም ተመልካቾች በ11ኛው ሰዓት የሚያነሷቸው የፍትሕና መሰል ጥያቄዎች ዋንጫን እንደ መጨረሻ ግብ አድርጎ ከመሻት ባለፈ ለክለቦቹም ሆነ  ለእግር ኳሱ ትርጉም እንደሌለው የሚያምኑ አሉ፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው ይቆይና በአኅጉር ደረጃ ከመጨረሻዎቹ ተርታ የሚገኘው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ውጤት የአደባባይ ምስጢር ሆኖ በሚገኝበት በአሁኑ ወቅት፣ ለዚህ ውጤት በግብዓትነት የሚጠቀሱት ክለቦች ለእግር ኳሱ ዕድገት በሚሊዮኖች ከሚመድቡት በጀት ይልቅ ለአካባቢያዊ ስሜትና ለትንንሽ ነገሮች ተገዥ መሆናቸው ብዙዎችን ግራ ያጋባ ክስተት ሆኖ እያነጋገረ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመርያውን ዋንጫ ያነሳው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ነው፡፡ በ1991 እና 1992 ዓ.ም. ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ በ1993 ዓ.ም. ኢትዮ ኤሌክትሪክ፣ በ1994 እና 1995 ዓ.ም. እንደገና ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ በ1996 ዓ.ም. ሐዋሳ ከተማ፣ በ1997 እና 1998 ዓ.ም. ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ በ1999 ዓ.ም. ሐዋሳ ከተማ፣ ከ2000  እስከ 2002 ዓ.ም. ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ በ2003 ዓ.ም. ኢትዮጵያ ቡና፣ በ2004 ዓ.ም. ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ በ2005 ዓ.ም. ደደቢት፣ ከ2006 እስከ 2009 ዓ.ም. ለተከታታይ አራት ዓመታት ቅዱስ ጊዮርጊስ ሲያነሳ የዘንድሮውን ደግሞ ለፕሪሚየር ሊጉን አዲስ የሆነው  ጅማ አባ ጅፋር ከፍ አድርጓል፡፡ በዚህም ውጤት ጅማ አባ ጅፋር በቀጣዩ ዓመት ኢትዮጵያን በመወከል በአፍሪካ የክለቦች ሻምፒዮንስ ሊግ ተካፋይ ይሆናል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...

‹‹ደስታ›› የተባለችው አማርኛ ተናጋሪ ሮቦት በሳይንስ ሙዚየም

‹‹እንደ ሮቦት ዋነኛው አገልግሎቴ ውስብስብ የሆኑ የቴክኖሎጂ ውጤቶችንና አሠራሮችን...