Tuesday, February 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልየምሥራቅ አፍሪካ የካቶሊክ ጳጳሳት ጉባዔ በአዲስ አበባ

የምሥራቅ አፍሪካ የካቶሊክ ጳጳሳት ጉባዔ በአዲስ አበባ

ቀን:

‹‹በአሁኑ ጊዜ የተለያዩ ዓይነት ሁከትና ጠቦችን እያየን እንገኛለን፣ ስለሆነም ቤተክርስቲያን በጠብ ምክንያት የተፈጠሩትን ቁስሎች የመፈወስና የነቢይነት ሚናዋን የመጫወት ተልዕኮ አለባት፡፡  በዚህ ቀጣና ቤተክርስቲያን  በሰላም ግንባታ፣ በፍትሕና እርቅ ውስጥ ያላት ሚና  እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡››

ይህ ኃይለ ቃል የተስተጋባው በአዲስ አበባ ከተማ በረዳኢተ ክርስቲያን ማርያም ቤተክርስቲያን ሐምሌ 8 ቀን 2010 ዓ.ም. በተከፈተው 19ኛው የምሥራቅ አፍሪካ የካቶሊክ ጳጳሳት ጉባዔዎች ኅብረት (አመሰያ) ጉባዔ ላይ፣ ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ ሊቀ ጳጳስ ዘካቶሊካውያን፣የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባዔ ፕሬዚዳንትና የአመሰያ ሊቀመንበር ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ነው፡፡

ኢትዮጵያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኬንያና ሌሎች በምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና ውስጥ የሚገኙ አገሮች በተለያዩ ዘርና ነገዶች መካከል  በሚከሰት  ግጭት ምክንያት እንደሚሰቃዩ ያስታወሱት ካርዲናሉ፣ ብዙ ሥልጣኔዎች፣ የሰው ልጅ አዕምሮአዊና ቴክኖሎጂያዊ ዕድገቶች  በሚታዩባት ዓለም ውስጥ እንዲህ አይነት አስከፊ ሁኔታ ማየት እጅግ አሳሳቢ ነው ብለዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

 እንደ አንድ የሕያው ብዝኃነት፣ የሰብዓዊ ክብርና ሰላማዊ አንድነት የምታስፋፋ አካል ቤተክርስቲያን በዚህ ሁኔታ ውስጥ የእኔ ሥራ ምን ይሆን ብላ ራሷን እየጠየቀች መሆኑን፣  የካቶሊክ ቤተክርስቲያን  ኢትዮጵያን ጨምሮ በቅርብ ጊዜያት ግጭቶች በታዩባቸው አገሮች ሰላም ማውረድ እንደሚቻል ታምናለች ያሉት ካርዲናሉ፣ በፖለቲካ መሪዎችና በመላው ኅብረተሰብ ዘንድ እውነተኛና ከልብ የመነጨ ውይይት ከእልህና ትምክህት አመለካከት ነጻ በሆነ መንገድ እንዲካሄድ ተማፅነዋል፡፡ 

ካርዲናል ብርሃነየሱስ አያይዘው እንደተናገሩት፣ በኤርትራና ኢትዮጵያ የተወሰደው ሰላማዊ ዕርምጃ አፍሪካውያን ችግሮቻቸውን በራሳቸው የመፍታት ጥበብ እንዳላቸው ማሳያ ነው፡፡  የአመሰያ አገሮችም ከዚህ የሰላም ሒደት መውሰድ የሚችሉ ትምህርት እንዳለ እምነታቸው መሆኑን የገለጹት አቡኑ፣ በሁለቱ ወንድማማች ህዝቦች መካከል ሰላምና አንድነት ለማምጣት ብርቱ ጥረት ስታደርግ መቆየቷንም አስታውሰዋል።

ከሐምሌ 9 ቀን ጀምሮ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ኢሲኤ) አዳራሽ ‹‹በእግዚአብሔር ላይ የተመሠረተ ሕያው ብዝኃነት ሰብዓዊ ክብርና ሰላማዊ አንድነት ለምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት›› በሚል መሪ ቃል  እየተካሄደ ያለው ጉባዔው በምሥራቅ አፍሪካ ዘላቂ ሰላምና ስምምነት ማምጣት በሚቻልበት ስልት ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚመክር ታውቋል፡፡

በጉባዔው ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ለምታከናውናቸው ሐዋርያዊና ማኅበራዊ ሥራዎች ብዝኃነትን ማስተናገድ እንዲቻል በቀጣናው ያሉ ነባራዊ ሁኔታዎችን የሚዳስሱ ጥናታዊ ጽሑፎች በሊቃውንት እየቀረቡ መሆኑ ተገልጿል።

በተጨማሪም ቤተክርስቲያኒቱ በምሥራቅ አፍሪካ ዘላቂ ሰላምና ትብብር ለመፍጠር ከሌሎች የእምነት ተቋማት፣ ከመንግሥታትና ከአፍሪካ ኅብረት ጋር  መሥራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይም ጉባዔው እንደሚመክር ታውቋል፡

በ57 ዓመት ታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ያለውና 300 በላይ ተሳታፊዎች የተገኙበት ጉባዔ በኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ ሲካሄድ፣ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያኗ አጋጣሚውን በመጠቀም አገሪቱ ያላትን የሰላምና የመከባበር ባህል ከሌሎች ወንድሞና እህቶች ጋር ለመካፈል የምትጠቀምበት አጋጣሚ መሆኑን ተገንዝባ፣ የአስተናጋጅ ኃላፊነቱን መቀበሏን ቀደም ሲል መግለጿ ይታወሳል፡፡

የአመሰያ ጉባዔ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት በሚሌኒየም አዳራሽ እንደሚካሄድ አስቀድሞ ተገልጾ የነበረ ቢሆንም አዳራሹ በሌላ መሰናዶ ምክንያት እንዲቀየር መደረጉን ቤተ ክርስቲያኒቱ መግለጿ ይታወሳል፡፡

አመሰያ በሚለው ምኅፃረ ቃል በሰፊው በሚታወቀው ኅብረት ውስጥ ዘጠኝ አገሮች ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ኬንያ፣ ኡጋንዳ፣ ታንዛኒያ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ማላዊና ዛምቢያ አባላት  ሲሆኑ፤ ጂቡቲና ሶማሊያ ተባባሪ አባላት ናቸው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የካቲት አብዮት – ጥያቄዎችሽ ዛሬም እየወዘወዙን ነው!

በበቀለ ሹሜ አጭር መግቢያ የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ ከ1960ዎች ወጣቶች ርዝራዦች አንዱ...

የሰሞኑ የ“መኖሪያ ቤቶች” የጨረታ ሽያጭ ምን ዓይነት ሕጋዊ መሠረት አለው?   

በዳዊት ዮሐንስ ሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ አየር ላይ ከሚንሸረሸሩ ዜናዎች...

ሁለቱ ወጎች፡ ከሰማየ ሰማያት አድርሶ መላሹ ቋንቋ! እስከ በዓሉ ቤርሙዳ

በተክለ ጻድቅ በላቸው ሰማየ ሰማያት አድርሶ መላሹ ቋንቋ! ከሁለት ሦስት ዓመት...

ለትግራይ ክልል ድርቅ ተፈናቃዮች አፋጣኝና ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እንዲደረግ ተጠየቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዩች ቋሚ...