Monday, March 4, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልበ‹ቄጠላ› ሥነ ሥርዓት የታጀበው ጉብኝት

በ‹ቄጠላ› ሥነ ሥርዓት የታጀበው ጉብኝት

ቀን:

የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሁለት ቀናት ጉብኝታቸው አዲስ አበባና ሐዋሳን ያማከለ ነበር፡፡ ሐምሌ 7 ቀን 2010 ዓ.ም. ከተደረገላቸው አቀባበልና መስተንግዶ ቆይታ በኋላ ወደ ሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ያደረጉት ጉብኝት የሲዳማውን በዩኔስኮ የዓለም ወካይ ቅርስነት የተመዘገበው የፊቼ ጫምባላ በዓል እሴቶች የተንፀባረቀበት ነበር፡፡

የፊቼ ጫምባላላ በዓል በርካታ ባህላዊ ክንዋኔዎችን በውስጡ የያዘ ነው፡፡ በዓሉ የሲዳማ ብሔር የአዲስ ዘመን መቀበያ ከመሆኑም ባሻገር በዓሉ ዘመዳሞች የሚገናኙበትና የሚጠያየቁበት፣ በተለያዩ አጋጣሚዎች የተፈጠሩ አለመግባባቶች ተፈተው ዕርቅ የሚወርድበት ነው፡፡ ይህንን ትውፊታዊ እሴት ለሃያ ዓመታት በጠብ ግድግዳ በራቸውን ዘግተው የነበሩት ኢትዮጵያና ኤርትራ ዕርቀ ሰላም ማውረዳቸውን ተከትሎ እንደ ‹‹አዲስ ዓመት›› ፊቼ ጫምበላላ አስበው የቄጠላ ሥነ ሥርዓቱን ፈጽመዋል፡፡

የሐዋሳ ከተማና አካባቢዋ ሕዝብ ውብ ከሆነው የቄጠላ ሥነ ሥርዓት ጀምሮ ያደረገላቸው አቀባባል ልክ ለፊቼ በዓል በቀባዶ በሳምንቱ የመጀመርያ ቀን በሲዳማ የሳምንት መጀመርያና የቀናት ሁሉ ታላቅ ቀን ተደርጎ እንደተሰየመ አምሳያ የሁለቱ መሪዎች ጉብኝትን አስተሳስረውበታል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ባህላዊ መሪዎች አዋጅ ሲያውጁ ሲዳማ የተከበረ የፊቼ በዓልህ ደርሷል አክብር፣ በተከበረ ቀንህ ቂም በቀል አትያዝ፣ የተጣላህ ታረቅ፣ በውስጥህ ያለውን ደሃ ዕርዳ፣ በውስጥህ የሚኖሩትን ሌሎች ሕዝቦች አትንካ፣ አብላቸው፣ አጠጣቸው፣ ፈጣሪህን ፍራ፣ አካባቢህን ጠብቅ፣ ጉዱማሌህን ጠብቅ፣ ፊቼህን ጠብቅ፣ ባህልህን አትርሳ፣ የበላኸው ይባረክልህ፣ የጠጣኸው ይባረክልህ፣ ፈጣሪ ከአደጋና ከፈተና ይጠብቅህ ብለው ኅብረተሰቡን ይመርቃሉ፡፡ ይህንኑ የምርቃት ሥነ ሥርዓት ኢንዱስትሪ ፓርኩን እንደ ጉዱማሌ ቆጥረው ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድና ለፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ያስተጋቡት፡፡

ዘመኑ የሰላምና የበረከት እንዲሆን የአገር ሽማግሌዎቹ ተመኝተዋል፡፡ አባቶች ፈረስ ጋልበው፣ ጎንፋ ሴማ (ቡሉኮ) ጋቢ፣ ለብሰው በእጃቸው በትር (ሲቆ) ጦር (ኡርዴ) ጋሻ (ዎንቆ) ይዘው ሥርዓቱን ፈጽመዋል፡፡ 

የአገር ሽማግሌዎች ተሰብስበው በሲዳማ አዋቂ ወንዶች ጭፈራ (ቄጣላ) ታጅበው ዘመኑ የሰላምና የበረከት እንዲሆን ፊቼ ጄጂ. . . ፊቼ ጄጂ (ፊቼ ከእኛ ጋር ከዘመን ዘመን ዝለቅ፣ እደግ ተመንደግ) ብለውም መርቀዋል፡፡

ለፕሬዚዳንት ኢሳያስና የልዑካን ቡድናቸውሐዋሳ በተዘጋጀው የእራት ግብዣ ላይ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ ‹‹በሲዳማ ሽማግሌዎች የሚከናወነው ባህላዊ የቄጠላ ሥነ ሥርዓት ልብን የሚገዛ ነው፤›› ብለዋል፡፡ ለሁለቱም መሪዎች የጌድኦና የሲዳማ ባህላዊ ኮትና ቡሉኮ ተበርክቶላቸዋል፡፡

በፕሬዚዳንት ኢሳያስ የተመራው ልዑክ አዲስ አበባ ሲደርስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይን ጨምሮ የክልል ፕሬዚዳንቶች፣ ሚኒስትሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና ከያንያን አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡ ከቦሌ ኤርፖርት እስከ ብሔራዊ ቤተ መንግሥት በነቂስ የወጣው ሕዝብም ከልሂቅ እስከ ደቂቅ የሁለቱን አገሮች ሰንደቅ ዓላማ ይዞ በተለያዩ ባህላዊ ጭፈራዎች እየታጀበ ነበር አቀባበሉን ያደረገው፡፡ በኤርፖርትም ሆነ በብሔራዊ ቤተ መንግሥት በነበረው መሰናዶም በባህላዊው ቀንደ መለከት መሣሪያ እየተነፋ የአቀባበሉን ድባብ ልዩ አድርጎት ነበር፡፡

እሑድ (ሐምሌ 8 ቀን) በሚሌኒየም አዳራሽ ከ20 ሺሕ በላይ ታዳሚ በተገኘበት ‹‹የኢትዮጵያና የኤርትራ ሰላም ማብሰሪያ›› መድረክ ላይ ከያንያን የሙዚቃ ሥራቸውን አቅርበዋል፡፡

‹‹ታላላቆቹ የሙዚቃ ጥበበኞች የሁላችንን ድምፅ ባስተባበረ ጥበባዊ ቋንቋ ደስታችንን ለዓለም ተናግረውልናል›› ያሉት የሙዚቃ ዝግጅት ኮሚቴ አባል አቶ ሠርፀ ፍሬ ስብሐት ናቸው፡፡ አቶ ሠርፀ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው እንዳወሱት፣ በዕለቱ መድረክ ላይ ከቀረቡት ሥራዎች ያልቀረቡት ይበዙ ነበር፡፡ አብርሃም ገብረ መድኅን፣ ታደለ ገመቹ፣ ጌታቸው ይለማርያም፣ ጸጋዬ ስሜ፣ ታደለ ሮባን የመሳሰሉ ተወዳጅ ድምፃውያን ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቢግ ባንድ ሙዚቀኞች ጋር በቂ የመድረክ ልምምድ አድርገው፣ በፕሮግራም መደራረብና በምሽቱ መግፋት ምክንያት ሥራዎቻቸውን ሳያቀርቡ ቀርተዋል ብለዋል፡፡

‹‹እንደ ዝግጅት ኮሚቴ አባልነቴ፤ በግሌ ለዚህ ትልቅ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡ የቻልነውን ሁሉ ብናደርግም፣ የዝግጅታችንን 50 ከመቶ እንኳ ሳናቀርብ በተጠቀሱት ምክንያቶች የሐሳባችንን ልክ ሳንከውን መድረኩ ተዘግቷል፤›› ሲሉም አክለዋል፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር ሲጨምር የሚኒባስ ታክሲዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ሊታሰብበት ይገባል

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ የሚባለውን ድርሻ...

ሃምሳ ዓመታት ያስቆጠረው አብዮትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጣ ውረድ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች የዴሞክራሲ ለውጥ ጥያቄ የሚነሳው ከፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተፈጸመው ሕገወጥ ተግባር ምንድነው?

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ፣...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ውሳኔ ተላለፈ

ፕሬዚዳንቷና ዋና ጸሐፊው ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል ከአዲስ አበባ ንግድና...