የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ሀብታሙ ተገኝ (ኢንጂነር) የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው መሾማቸው ታወቀ፡፡ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ አርዓያ ግርማይ ደግሞ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው እንዲያገለግሉ መሾማቸው ታውቋል፡፡
ለአቶ ሀብታሙ የተጻፈላቸው ደብዳቤ ከሐሙስ ሐምሌ 12 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በአዲሱ የኃላፊነት ቦታ እንዲያገግሉ የሚረጋግጥ መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል፡፡
አቶ አርዓያም በተመሳሳይ ሁኔታ በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ፊርማ የወጣው ደብዳቤ በትራንስፖርት ሚኒስቴር በሚኒስትር ዴኤታ ኃላፊነት እንዲያገለግሉ መሾማቸው ታውቋል፡፡
በዚሁ ሹመት መሠረት የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን አዲስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እንደሚሾምለት ይጠበቃል፡፡