Monday, December 5, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊየአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ሠራተኞችን እያሰናበተ ነው

  የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ሠራተኞችን እያሰናበተ ነው

  ቀን:

  የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ኮሚቴዎችን አዋቅሮ ባጠናው ጥናት መሠረትና ከተጠቃሚዎች ኅብረተሰብ አገኘሁት ባለው መረጃ መሠረት፣ የአመራርና የአሠራር ችግሮች አሉባቸው ባላቸው ሠራተኞች ላይ ዕርምጃ እየወሰደ መሆኑን ዋና ሥራ አስኪያጁ አቶ አወቀ ኃይለ ማርያም ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

  ስድስት ኮሚቴዎች ተዋቅረው በተጠናው ጥናት መሠረት የአመራርና የአሠራር ችግር አለባቸው በተባሉ 34 አመራሮችና ባለሙያዎች ላይ የማሰናበትና ከኃላፊነት የማንሳት ዕርምጃዎች ተወስደዋል፡፡ በእነዚህ ሠራተኞች ላይ ዕርምጃው የተወሰደው በጥናቱ በተገኙ ተጨባጭ ማስረጃዎች እንደሆነ አቶ አወቀ አስረድተዋል፡፡

  ኮሚቴዎቹ አሁንም በቢሾፍቱ ከተማ ጥናታቸውን እያጠናቀቁ በመሆኑ፣ በመጨረሻ ከሃምሳ የማይበልጡ ሠራተኞች እንደሚሰናበቱ ገልጸዋል፡፡ ከመልካም አስተዳደር ችግሮች ጋር በተያያዘ በሠራተኞች ላይ ተመሳሳይ ዕርምጃ በወሰዱ የመንግሥት ተቋማት እንደሆነው፣ ሠራተኞችን ካሰናበተ በኋላ ሳይሆን ክፍት የሚሆኑ ቦታዎችን ታሳቢ በማድረግ ባለሥልጣኑ በአሁኑ ወቅት የ100 ሠራተኞችን ቅጥር እንዳጠናቀቀ ጠቁመዋል፡፡

  አቶ አወቀ እንደሚሉት ጥናቱ ሲጠናቀቅ በቀጥታ ወደ ዕርምጃ ከመገባቱ በፊት ከሠራተኞች፣ ከኅብረተሰብ ፎረምና ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጋር ውይይት ይደረጋል፡፡ ይህ የሚሆነው ደግሞ ሠራተኞች በሚወሰደው ዕርምጃ ማመን ስላለባቸው ነው፡፡ ‹‹ሠራተኛው መማር ስላለበት ውይይት ያስፈልጋል፡፡ ዝም ብሎ ዕርምጃ ቢወሰድ ከፖለቲካ ግብዓትነት አይዘልም፤›› ብለዋል አቶ አወቀ፡፡

  እሳቸው በኮሚቴዎች በተደረጉት ጥናቶች ተገኙ የተባሉትን ችግሮች ከመግለጽ ቢቆጠቡም፣ የትልልቅ ተቋማት ክፍያዎች ዝቅተኛ እንዲሆን ማድረግና መሰል ሕገወጥ ተግባራት ዋነኞቹ መሆናቸውን የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል፡፡

  ኅብረተሰቡ በተደጋጋሚ በሚያሰማው የመልካም አስተዳደር ችግር ምክንያት በአሁኑ ወቅት መንግሥት መልካም አስተዳደር ቀዳሚው አጀንዳዬ ነው እያለ ነው፡፡ እንደ መሬት፣ ውኃ፣ የኤሌክትሪክ ኃይልና ሌሎችም የከተማ አገልግሎቶችን በሚሰጡ የመንግሥት ተቋማት የአሠራር ክፍተቶችን ለማስተካከል ዕርምጃ እየወሰደ መሆኑ በተደጋጋሚ እየተዘገበ ነው፡፡ ለአብነት ከመሬት አስተዳደር ዘርፍ 672 አመራሮችና ሠራተኞች ላይ፣ 595 የፖሊስ አባላት ላይ ከማዕረግ ማንሳት እስከ ማባረር ዕርምጃ መወሰዱን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

  ከዚህም ባሻገር በትራንስፖርት፣ በገቢና ንግድን በሚመለከቱ ዘርፎች ላይ ተመሳሳይ ዕርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀቱን መንግሥት እየገለጸ ነው፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ዳግም ነፍስ የዘራው የተማሪዎች ማርች ባንድ

  የሙያው ፍቅር ያደረባቸው ገና በልጅነታቸው ነው፡፡ በ1970ዎቹ መጀመርያ፣ ለቀለም...

  በስንደዶና ሰበዝ የተቃኘው ጥበብ

  በአንዋር አባቢ ተወልዳ ያደገችው መሀል አዲስ አበባ አራት ኪሎ ነው፡፡...

  አዲስ ጥረት የሚጠይቀው  ኤችአይቪ  ኤድስን  የመግታት  ንቅናቄ

  ‹‹ኤችአይቪ በመላው ዓለም  በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን የሚያጠቃ ዋነኛ የሕዝብ...

  የኅትመት ብርሃን ያየው ‹‹የቃቄ ወርድዎት›› ቴአትር

  ከአራት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መድረክ ላይ ይታይ...