Friday, June 9, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበኦሮሚያ እስራቱ መቀጠሉን መድረክ አስታወቀ

በኦሮሚያ እስራቱ መቀጠሉን መድረክ አስታወቀ

ቀን:

የሕዝብ ሰላማዊ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች በመልካም አስተዳደር ዕጦት ላይ ብቻ ተሳብበውና ተድበስብሰው ሊቀሩ አይገባም ያለው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ)፣ በኦሮሚያ ክልል እስራት ተባብሶ መቀጠሉን አስታወቀ፡፡

መድረክ ይህን ያስታወቀው የፓርቲው አመራሮች ዓርብ መጋቢት 23 ቀን 2008 ዓ.ም. ስድስት ኪሎ አካባቢ በሚገኘው ዋና ጽሕፈት ቤት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ነው፡፡

መልካም አስተዳደር አሳጥተዋል የሚላቸው ባለሥልጣናት ከአንዱ ሥልጣን ወደ ሌላ እየተሸጋሸጉ ናቸው የሚለው የመድረክ መግለጫ፣ ‹‹በሕዝቡ ላይ ወንጀል የፈጸመውን ተኩሶ ገዳይ ኃይልም ሆነ አስተዳደራዊ በደል እየፈጸመ ያለውን ሙሰኛ ለሕግ አቅርቦ ሳያስቀጣ፣ ይቅርታና አጥፍተናል በሚሉ ቃላት መሸንገል ዓላማው የምዕራቡን ለጋሽ አገሮች ቀልብ ለመሳብ ነው፤›› በማለት በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፓርላማ ይቅርታ እንደሚጠይቁ ያስታወቁበትን ሐሳብ አጣጥሎታል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፓርላማ መግለጫ ከሰጡ በኋላ፣ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞ ባሰሙ ባላቸው 2,627 የመድረክ አባላትና ደጋፊዎች ላይ በኦሮሚያ ክልል የተፈጸሙ እስራቶችን ዋቢ በማድረግ ተቃውሞውን አሰምቷል፡፡

‹‹ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ዜጎች ከየሥራ ቦታቸውና ከመኖሪያ ቤታቸው በገፍ ታፍሰው አብዛኛዎቹም ቤተሰቦቻቸውና ዘመዶቻቸው በማያውቋቸው አካባቢዎች ተወስደው ታስረዋል፡፡ በአሁኑ ወቅትም የሚገኙበትን ሁኔታ ለማወቅ አስቸጋሪ ሆኗል፤›› በማለት በመግለጫው አትቷል፡፡

‹‹ኢሕአዴግ በአደባባይ ባመነበት ብልሹ አስተዳደሩ ላይ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞአቸውን በማሰማታቸው ምክንያት በግፍ ያሰራቸውን አባሎቻችንና ደጋፊዎቻችን፣ እንዲሁም ሌሎች ሰላማዊ ዜጎች በአስቸኳይ እንዲፈቱ፤›› ሲል ጠይቋል፡፡

‹‹በተጨማሪም በሰላማዊ መንገድ በተቃውሞ እንቅስቃሴ የተሳተፉትን ዜጎች በግፍ የገደሉ በገለልተኛ አጣሪ አካል ተጣርቶ ለፍርድ እንዲቀርቡ፣ እንዲሁም በሕዝቡና በንብረቱ ላይ ለደረሰው ጉዳት መንግሥት ኃላፊነት ወስዶ ለተጎጂዎችና ለቤተሰቦቻቸው ተገቢውን ካሳ እንዲከፍል፤›› በማለት መድረክ ጠይቋል፡፡

‹‹መንግሥት ከመድረክና ከሌሎች ሀቀኛ ፓርቲዎች ጋር የፖለቲካ ምኅዳሩን ነፃ፣ ፍትሐዊና ተዓማኒ ለማድረግ በአስቸኳይ እንዲደራደር በአፅንኦት እንጠይቃለን፤›› በማለት መድረክ በመግለጫው አሳስቧል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ