Tuesday, November 28, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ሥነ ፍጥረትከወቅት ጋር ፀጉሩ የሚቀያየረው ሽኮኮ

ከወቅት ጋር ፀጉሩ የሚቀያየረው ሽኮኮ

ቀን:

ያማርኛ መዝገበ ቃላት ሽኮኮን ሲፈታ ያውሬ ስም፣ በጐሬ በየቋጥኙ ሥር የሚኖር የጥንቸል ዐይነት ይለዋል፡፡ በሌላ በኩል ስለዱር እንስሳት የሚያወሳ አንድ ድርሳን፣ሽኮኮን ዘራይጥ አስተኔ ይለዋል፡፡ ከተለያዩ ዝርያዎች አንዳንዱ በዛፍ ውስጥ የሚኖር፣ አንዳንዱ በመሬት ላይ የሚቆይ ዓይነት አለ ሲልም ያክላል።

በስሚዝሶኒያን ናሽናል ሙዝየም ኦፍ ሂስትሪ እንደተጻፈው፣ ሽኮኮ ፅድ በሞላባችው ደኖች ውስጥ በብዛት ይገኛል። እንስሳው ረጅምና ፀጉራም በሆነው ጭራው በቀላሉ ይታወቃል። ፀጉሩ በክረምት ወቅት ቀይና ቡናማ ዓይነት ሲሆን፣ በበጋ ወቅት አመድማ ነጭ ይሆናል። ፍራፍሬና ተክሎች የሚመገብ ቢሆንም፣ ጫጩቶችንና የአዕዋፍ እንቁላል ሊበላ ይችላል። ክብደቱ እስከ ሁለት ኪሎ ግራም አካባቢ ይመዝናል።

የሽኮኮ ጆሮዎች ክብና ትንንሽ ሲሆኑ፣ እግሮቹ ደግሞ አጫጭር ናቸው። ይህ ትንሽ እንስሳ የሚኖረው አለታማ በሆኑ አካባቢዎች ነው። ከፍተኛ የማየት ችሎታ ያለው መሆኑ ጠላቶቹን ከርቀት ለመለየት ያስችለዋል። አለታማ በሆነው መኖሪያው ያሉት ጉድጓዶችና ስንጥቆች ደግሞ ከጠላቶቹ መሸሸጊያ ናቸው። ሽኮኮዎች በርከት ብለው አንድ ላይ መኖራቸው በጠላቶቻቸው እንዳይደፈሩ የሚረዳቸው ከመሆኑም በላይ በክረምት ወራት እርስ በርስ ለመሟሟቅ ይረዳቸዋል፡፡ ከስድስት እስከ አሥር ዓመት ይኖራሉ፡፡

በአማርኛ ብሂል ውስጥ ‹‹የሸኮኮ ጸሎት›› ይገኛል፡፡ መንስዔውንም መዝገበ ቃላቱ እንደሚለው፣‹‹ማታ በጨለማ ሲጸልይ የሚያልቅስ ይመስላል፣ ከጩኸቱም በኋላ ይነፋነፋል፣ ስለዚህ የሸኮኮ ጸሎት ይባላል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለሲኒመር ትሬዲንግ አ/ማ አባላት በሙሉ የጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪ

ለሲኒመር ትሬዲንግ አ/ማ አባላት በሙሉ የጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪ ሲኒመር ትሬዲንግ...

የባህር በር በቀጣናዊ ተዛምዶ ውስጥ

በበቀለ ሹሜ መግቢያ በ2010 ዓ.ም. መጋቢት ማለቂያን ይዞ ዓብይ አህመድ በጠቅላይ...

ሥጋት ያስቀራል ተብሎ የሚታሰበው የጫኝና አውራጅ መመርያ

በአዲስ አበባ ከተማ በሕገወጥ መልኩ በመደራጀት ማኅበረሰቡ ላይ እንግልትና...

ማወቅ ወይስ አለማወቅ – ድፍረት ወይስ ፍርኃት?

በአሰፋ አደፍርስ ወገኖቼ ፈርተንም ደፍረንም የትም አንደርስምና ለአገራችን ሰላምና ክብር...