Monday, December 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ፍሬከናፍርፍሬ ከናፍር

ፍሬ ከናፍር

ቀን:

‹‹ዛሬ በዚህ ስፍራ [ጉባ] የተገኛችሁ ታዳሚዎች ልባችሁ እዚህ እንደቀረ እምነቴ የፀና ነው፡፡››

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ፣ የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ የተጀመረበት አምስተኛ ዓመት በዓል በግንባታው ሥፍራ ጉባ ሲከበር  ከተናገሩት የተወሰደ፡፡ መጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም. የመሠረት ድንጋይ ተጥሎ ሥራው የተጀመረው ግንባታ ከ50 በመቶ በላይ መከናወኑ በተነገረበት የመጋቢት 24 ቀን 2008 ዓ.ም. መሰናዶ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም እንዳሰመሩበት፣ የግንባታው ሒደት የዘመናት ቁጭትን የመመለስና ፀረ ድህነት ትግሉን የማጠናከሩ ሒደት ጥሩ ምዕራፍ ላይ ለመድረሱም ማሳያ ነው ብለዋል፡፡ ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያውያን ዘርና ሃይማኖት፣ ዕድሜና ፆታ ሳይገድባቸው በአንድነት እንዲሠለፉ ማድረጉንም ሳይናገሩ አላለፉም፡፡ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ እያንዳንዳቸው 375 ሜጋ ዋት ኃይል ማመንጨት የሚችሉ 16 ዩኒቶች ያሉት ሲሆን፣ ግንባታው ሲጠናቀቅም በአጠቃላይ ስድስት ሺሕ ሜጋ ዋት እንደሚያመነጭ ይጠበቃል፡፡ ለግድቡ ግንባታ ባለው ሒደት 12 ቢሊዮን ብር ቃል መገባቱንና እስካሁን ከሕዝቡ ስምንት ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር መሰብሰቡ ታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...