Sunday, March 26, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየማኅበራዊ ተጠያቂነት ዕርምጃ

የማኅበራዊ ተጠያቂነት ዕርምጃ

ቀን:

የኢትዮጵያ ማኅበራዊ ተጠያቂነት ፕሮግራም ኢሳፕ2 በተመረጡ 223 ወረዳዎች ላለፉት ሦስት ዓመታት ባከናወነው መሠረታዊ አገልግሎቶችን የማሻሻል ሥራ ለውጥ መታየቱን አስታወቀ፡፡ በዘጠኙም ክልሎችና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች በጤና፣ በውኃና አካባቢ ንፅህና፣ በትምህርት፣ በግብርና እንዲሁም በገጠር መንገዶች የሚታዩ ክፍተቶችን ለመመለስ ያደረገው እንቅስቃሴ ውጤት ማሳየቱን አስታውቋል፡፡ 25 ሚሊዮን ዶላር በጀት ተይዞለት ሲሠራ የቆየው ፕሮጀክቱ ሁለተኛው ምዕራፍ መጠናቀቁን ያለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ በካፒታል ሆቴል ‹‹የማኅበራዊ ተጠያቂነት ውጤቶችና ተሞክሮዎች›› በሚል ባዘጋጀው የሁለት ቀናት ኮንፈረንስ ላይ አስታውቋል፡፡

የመሠረታዊ አገልግሎቶች ማሻሻያ አካል የሆነው የማኅበራዊ ተጠያቂነት ፕሮግራም በሚያስተባብረው መሥሪያ ቤት የአንድ ሥራ ክፍል ኃላፊ አቶ ጤናው መንግሥት እንደሚሉት፣ ፕሮግራሙ በወረዳዎች ላይ ይታይ የነበረውን የመሠረታዊ አገልግሎቶች ክፍተት ምላሽ ለመስጠት ተንቀሳቅሷል፡፡ በትምህርት ዘርፍ ባደረገው ተሳትፎም የላቀ ውጤት አስመዝግቧል፡፡

ማኅበረሰቡ፣ መንግሥት፣ የግሉ ዘርፍና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማትን በጋራ እንዲንቀሳቀሱ በማድረግ በወረዳዎቹ በሚገኙ 197 ትምህርት ቤቶች ይታይ የነበረውን የመማሪያ ክፍሎች እጥረት፣ የተማሪዎች መቀመጫ ወንበር እጥረት፣ የመምህራን እጥረት፣ የመፀዳጃ ቤት ችግር፣ የመጠጥ ውኃ አለመኖር፣ የትምህርት መርጃ ቁሶች፣ ቤተ ሙከራዎችና ሌሎችም በመማር ማስተማሩ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድሩ የነበሩ ክፍተቶችን ለመሙላት ጥሯል፡፡

በጤናው ዘርፍም እንዲሁ በ103 ወረዳዎች ለቲቢና ሌሎች የሕክምና አገልግሎቶች የሚሆኑ ተጨማሪ ክፍሎችን ግንባታ፣ እድሳት፣ ጄነሬተርና የላቦራቶሪ ግዢ ዕቃዎች፣ መድኃኒት አቅርቦትና ሌሎች ድጋፎችን ማድረግ መቻሉን በዕለቱ በቀረበው ሪፖርት ማወቅ ተችሏል፡፡

በዚህም በጤና አገልግሎት ውስንነት እንግልት ይገጥማቸው የነበሩ በአማራ ክልል አዴት ከተማ የሚገኙ የኤችአይቪ ሕሙማን መረዳታቸውን ገልጸዋል፡፡ ከዚህ ቀደም የሲዲፎር መጠናቸውን ለማስለካት በአካባቢያቸው አገልግሎቱን የሚሰጥ ሆስፒታል ባለመኖሩ ለሰዓታት መጓዝ ይጠበቅባቸው ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ማኅበራዊ ተጠያቂነት ፕሮግራም ኢሳፕ2 የክልሉ የጤና ቦርድ ስለጉዳዩ እንዲያውቅና ቫይረሱ በደማቸው የሚገኝ በአዴት ጤና ጣቢያ ውስጥ የተሟላ የጤና አገልግሎት እንዲያገኙ አስችሏል፡፡

‹‹የፕሮግራሙ ዓላማ የዜጐችን ተሳትፎ ማሳደግና ጠያቂ ትውልድ መፍጠር፣ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትና የመንግሥት አካላትን ተጠያቂ እንዲሆኑ ማድረግ ነው፤›› የሚሉት አቶ ጤናው የፕሮግራሙ ዓላማ ከሞላ ጐደል መሳካቱን፣ አገልግሎት ሰጪውም የኅብረተሰቡን ጥያቄ እንዲመልስ ማስቻሉን ተናግረዋል፡፡

የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በበላይነት የሚከታተለው ፕሮግራሙ ከዲኤፍ አይዲ፣ ከአውሮፓ ኅብረት፣ ከአይሪሽ ኤይድ፣ ከዓለም ባንክና ከሌሎችም ተቋማት ጋር በጋራ ይሠራል፡፡ ይሁን እንጂ የበጀት እጥረት እንደሚያጋጥመው አቶ ጤናው ይገልጻሉ፡፡ ‹‹የአንዳንድ ወረዳ ነዋሪዎች በርካታ ጥያቄዎች ያነሱ ነበር፡፡ ብዙዎች ሆስፒታል እንዲገነባ፣ መንገድ እንዲሠራላቸው ጠይቀውናል፡፡ ነገር ግን ካለው የበጀት ውስንነት አኳያ የጠየቁትን ሁሉ ምላሽ መስጠት አልቻልንም፤›› ይላሉ፡፡

በቀጣይ የ18 ወራት የሽግግር ወቅት እንዳለ፣ በዚህም የተጀመሩ ሥራዎችን የማጠናቀቅ፣ ቀጣይ ፕሮግራም የመቅረጽ፣ አገልግሎቱንም በመላው አገሪቱ ተደራሽ የማድረግ እንደሚሠራ አቶ ጤናው ተናግረዋል፡፡ ለማኀበረሰቡ ጥያቄ በተገቢው መጠን ምላሽ ለመስጠት የመንግሥትና የለጋሽ ድርጅቶች ድጋፍ ወሳኝ መሆኑንም አክለዋል፡፡

ኢሳፕ2 ከዓመታት በፊት በዘጠኙም ክልሎች በሚገኙ በ86 ወረዳዎች ላይ በተመሳሳይ ዘርፎች በጤና፣ በትምህርት፣ በእርሻ፣ በውኃና በአካባቢ ንፅህና ዙሪያ የሙከራ ትግበራ ሠርቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን...