‹‹በዓልቲ መነፀር ህበይ››
‹‹ማንበብ ጎበዝ ያደርጋል፡፡ የተወደዳችሁ ሕፃናት ካልበላችሁ ካልጠጣችሁ በሕይወት ለመኖር እንደማትችሉ ሁሉ፣ ማንበብም እንደዚያ ነው፡፡ የማያነብ ሰው ጎበዝ አይሆንም፡፡ የሚያነብ ሰው ግን ዕፁብ ድንቅ ንግግር ለማድረግ፣ ለማሰብ፣ ለመሥራት ይችላል፤›› የሚል ምክር የያዘውን ‹‹በዓልቲ መነፀር ህበይ›› የተሰኘውን የሕፃናት መጽሐፍ በትግርኛ ያዘጋጀው ኣዲስ ዓለም ሓጎስ ነው፡፡
‹‹ነገር በምሳሌ፣ ጠጅ በብርሌ፣ መዝሙር በሃሌ›› እንዲሉ ሕፃናት በአዕምሮ እንዲጎለምሱ በእንስሳት ባሕርያት በተረትና ምሳሌ እያዋዛ የቀረበው መጽሐፍ ዘጠኝ ተረቶችን ይዟል፡፡
ደራሲው ከሕፃናት መጽሐፉ ሌላ ‹‹ወይዘሪት ኢትዮጵያ 2020››፣ የአጫጭር ልቦለድ መድበል ‹‹መወዳእታ መዓልቲ›› እና ‹‹ማሕበር ምውታን›› እንዲሁም ‹‹ባሕታዊ በጊዕ›› የተሰኘ የሕፃናት ተውኔት አሳትሟል፡፡