Friday, September 29, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

​አገር በቀሏ ግሬደር

ትኩስ ፅሁፎች

ከአዲስ አበባ 130 ኪሎ ሜትር ርቀት፣ ደብረ ብርሃን ከተማ በሚገኘው በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን፣ የኮንስትራክሽንና ኢንጂነሪንግ ማሽነሪ ኢንዱስትሪ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁሉንም ማቴሪያል በአገር ውስጥ በመጠቀም የተሠራችው ግሬደር

*************************

         …ኦባማ ባደንቅህ

የፍቅር አደራጅ ÷ የሰላም አጋጅ
የተድላ የደስታ ዋና ተመራጭ
የዲሞክራሲ መርሕ ÷ የነፃነት አዋጅ
ዋና ፈላጭ ቆራጭ ÷ ቀና ነገረ ፈጅ
ኦባማ ባደንቅህ ÷ እወቅስህም እንጂ
ዓለም በጦርነት እርስ በእርስ ሲፋጅ
ባይተዋር በሆነች በገዛ አንድ እጅህ።
በሰላም ጥረትህ ÷  ከፊል ፋኖነትህ
ኦባማ ባደንቅህ ÷ እወቅስህም እንጂ
ለሥጋ ላይጠቅምህ ÷ ለነፍስም ላይበጅህ
ንፁሑን መኝታ ባቆሸሸች እጅህ።
ከምሥራቅ መካከል ÷ ለ‘ሥራኤል ሳትወግን
ለህልውናዋ ምን እንኳ ቅን ብትሆን
ለሰሜን ኮርያ ጀርባ እንደሰጠህ
ኢራንን ሸመገልህ÷ ካለም እንዳትገለል
ኩባን ተወዳጀህ ÷ ካሣ እንዳትከፍል
ኦባማ እንዳደንቅህ ÷ በዚህ ብትታደል።
ኦባማ የማደንቅህ አፌ እንደተሳለ
ካንተ በፊት የለ ÷ ካንተም ኋላ የለ
በቃል ኪዳን ምድር መባረክ የቻለ።
የጠጣኸው ቡና ÷ የቀመስኸው ቁርስ
ጥሎ እንዳይጥልህ ÷ በራሺያ ላይ ዞረህ
ኢትዮጵያን ጎበኘህ ÷ ርጥባንም ጣልህ
ራቧን አልይ ብልህ
ኦባማ እንዳደንቅህ ÷ የምወቅስህ ሳለህ
የምወቅስህ ሳለህ።

                                               ኃይለ ልዑል ካሣ

አዲስ አበባ
         መጋቢት 26/2008 ዓ/ም

**********************

በአፍጋኒስታን እግሯን ያጣችው ውሻ ከፍተኛ ደረጃ ያለው ሜዳሊያ ተሰጣት

በአፍጋኒስታን ቤት ሠራሽ ቦንብ ስታነፈንፍ አንድ እግሯን ያጣችው የአሜሪካ ባህር ኃይል ውሻ ሉካ ሜዳሊያ መሸለሟን መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ፡፡

የኤቢሲ ዘገባ እንደሚያመለክተው ሉካ እግሯን ካጣች ሦስት ዓመታት የተቆጠሩ ሲሆን፣ አገልግሎት ላይ እያለች ግን 400 ተልዕኮዎችን ፈጽማለች፡፡ ለዚህ አገልግሎቷ የተሰጣት ሜዳሊያ ደግሞ በውትድርና ዓለም ከፍተኛ ቦታ ያለው ነው፡፡

ለሉካ ዕውቅና የሰጣት ግን የእንግሊዝ ተቋም ሲሆን፣ ተቋሙ እንዳስታወቀው ለሉካ የተሰጠው ሜዳሊያ በወታደራዊ አገልግሎት የተሳተፈ እንስሳ ሊያገኘው የሚችለው የመጨረሻው ትልቁ ዕውቅና እንደሆነ ገልጿል፡፡ ተቋሙም እ.ኤ.አ. ከ1943 ጀምሮ ይህንን ዕውቅና የሰጠው 66 ጊዜ መሆኑን ጠቁሟል፡፡

*************************

ማን የማን ባለቤት  እንደሆነ መለየት ባለመቻላቸው መንትዮችን ያገቡት መንትዮች የፊት ቀዶ ሕክምና ሊያደርጉ ነው

ቻይና ሻንዚ ግዛት ውስጥ የሆነ ነው፡፡ መንትያ ወንድማማቾች መንትያ እህትማማቾችን ያገባሉ፡፡ ከዚያው ከሠርጋቸው ዕለት ጀምሮ ማን የማን እንደሆነ መለየት በማስቸገሩ እያንዳንዱ እንቅስቃሴ በከፍተኛ ጥንቃቄ ሊደረግ የግድ እንደሆነ የዘ ታይም ዘገባ ያመለክታል፡፡

ሁኔታውን አስቸጋሪ ያደረገው የመንትዮቹ አካላዊ መመሳሰል ብቻ አይደለም፡፡ ድምፃቸው ሲያወሩ የሚያደርጉት አካላዊ እንቅስቃሴና በገጽታቸው የሚያሳዩት ነገር ሁሉ እጅግ ተመሳሳይ ነው፡፡ ስለዚህም ነው የፊት ቀዶ ሕክምናው ያስፈለጋቸው፡፡

በጥንዶቹ መካከል እየተፈጠረ ያለውን ግራ መጋባትና መደነጋገር ለማስወገድ ቀዶ ሕክምናው እንደሚያስፈልግ የሆንግኮንግ ሆስፒታል ዶክተሮችም መክረዋል፡፡

  

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች