Tuesday, February 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናብአዴን አገራዊ የለውጥ ሒደቱን ሊያደናቅፉ ይችላሉ የሚላቸውን ከፍተኛ አመራሮች ለማጥራት ማቀዱ ተሰማ

ብአዴን አገራዊ የለውጥ ሒደቱን ሊያደናቅፉ ይችላሉ የሚላቸውን ከፍተኛ አመራሮች ለማጥራት ማቀዱ ተሰማ

ቀን:

የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) አዲስ የለውጥ ንቅናቄ በመላ አገሪቱ እንዲቀጣጠል በኢሕአዴግ ውስጥ ካሉ እህት ድርጅቶችና ለውጥ ፈላጊ ሕዝብ ጋር በመሆን ከፍተኛ ሚና ቢጫወትም፣ በውስጡ ያሉ አንዳንድ አመራሮቹ ለውጡን ከማስቀጠል ይልቅ ዳተኝነትና መደናገር የሚታይባቸው በመሆኑ በማጥራት ለመለየት ዕቅድ መንደፉ ታወቀ፡፡

የብአዴን ክልላዊ ፖለቲካዊ ጉዳዮች አደራጅ ኮሚቴ ‹‹ያለንበት ሁኔታ ዕድሎችና ተግዳሮቶች›› በሚል ርዕስ ያዘጋጀውን ወቅታዊ ሁኔታ የሚተነትን ሰነድ ባለፈው ሳምንት ውስጥ ለከፍተኛ የፓርቲው አመራሮች መላኩን፣ ሪፖርተር ያገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ ይኼንን ሰነድ መሠረት በማድረግ በቀጣዮቹ ሳምንታት ውስጥ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች እንደሚመክሩ፣ በዚህም መሠረት አመራሩን በማጥራትና በመለየት አገራዊና ክልላዊ የለውጥ ሒደቱ ሳይደናቀፍ እንዲቀጥል የመምራት፣ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በብቃት መመከት የሚችልና በራሱ ፀንቶ በሚቆም አመራር ብአዴን ለመገንባት አቅዷል፡፡

‹‹ብአዴን በራሱ ውስጥም ሆነ በኢሕአዴግ አባልነቱ ተሃድሶው መሠረት እንዲይዝ፣ እውነተኛ ለውጥ እንዲኖርና ችግሮች እንዲፈቱ በፅናት ታግሏል፡፡ በዚህም አገርን የመታደግ ኃላፊነቱን ተወጥቷል፡፡ ስለሆነም አሁን በአገር አቀፍ ደረጃ ለመጣው ለውጥ ያበረከተው አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነው ቢባል ድፍረት አይሆንም፤›› ሲል ብአዴን የነበረውን ሚና ሰነዱ ያትታል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ከጥቂት ሳምንታት በፊት በበርካታ የክልሉ ከተሞች በዋነኛነትም በባህር ዳር ለውጡን ለመደገፍ አደባባይ የወጣው የሕዝብ ማዕበል የዚህ ትግል ውጤት ፈንቅሎት እንጂ፣ ‹‹እንደ ከዚህ ቀደሙ እኛ  ውጣ ብለነው አይደለም፤›› ይላል፡፡

እውነቱ ይህ ሆኖ ሳለ የብአዴን አመራር ለውጥ እንዲመጣ የሠራውን ያህል የለውጡ ባለቤት ለመሆን ግን ፈራ ተባ ሲል መታየቱን ሰነዱ ይገመግማል፡፡

‹‹ለምሳሌ በየአካባቢው የተካሄዱ የድጋፍ ሠልፎችን ብንመለከት አመራሩ ፈቃጅና ከልካይ፣ ሕዝቡ ደግሞ በአንፃሩ ጠያቂና ባለቤት ሆኗል፡፡ በዚህ ምክንያትም በጋራ ቤታችን የበይ ተመልካች አለዚያም ተጋባዥ እንግዳ ሆነናል፤›› ሲል ይተቻል፡፡ በሌላ በኩል ‹‹ውግዘት ይደርስብኛል፣ እዘለፋለሁ በሚል ፍርኃትና ጥርጣሬ ከሕዝብ ፊት ለመቆም ድፍረት የተሳናቸው አመራሮች ታይተዋል፡፡ ይህ በእውነቱ ለብአዴን ውድቀት ነው፤›› በማለት የነበረውን ድርጊት በከፍተኛ ደረጃ ያወግዛል፡፡

በአመራሩ ላይ የታየው ይህ መደናገርና ፍርኃት ፈጽሞ ተቀባይነት እንደሌለው የሚገልጸውና ወቅታዊ ፖለቲካ ሁኔታዎችን በመዳሰስ የተሰናዳው ይህ ሰነድ፣ ለውጡን በመደራጀት ተናቦ መምራት ካልተቻለ ወደሌላ አቅጣጫ ሊገፋ እንደሚችል ያስረዳል፡፡ በመሆኑም የተደራጀ፣ አንድነት ያለው፣ እርስ በርስ የሚናበብና ድርጊትን ከአስተዋይነት ጋር የተጎናጸፈ ሆኖ ፓርቲው መደራጀት እንደሚገባው አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡

‹‹በአመራራችን ውስጥ ያለውን ዥንጉርጉር አስተሳሰብ እያጣራን ለውጡን በትክክል ተረድቶትና ደግፎ የሚሠራውንና ለውጥ አደናቃፊውን እየለዩ መምራት ያስፈልጋል፤›› በማለት ቀጣይ አቅጣጫውን ግልጽ አድርጓል፡፡

ወቅታዊ ሁኔታዎችን በሚዳስሰው በዚህ ሰነድ ላይ የተመሠረተ ከከፍተኛ እስከ ታችኛው አመራር ድረስ ጥልቅ ውይይት በቀጣዮቹ ሳምንታት እንደሚደረግም የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...