Monday, July 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናፕሬዚዳንታዊ ሜዳሊያ ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ

ፕሬዚዳንታዊ ሜዳሊያ ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ

ቀን:

ማክሰኞ ሐምሌ 17 ቀን 2010 ዓ.ም. የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ ርዕሰ መዲና አቡዳቢ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) እና የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ፣ በአልጋ ወራሽ ሼክ መሐመድ ቢን ዛይድ አል ነሃያን በአገሪቱ ከፍተኛው የተባለው ፕሬዚዳንታዊ ሜዳሊያ ተበርክቶላቸዋል፡፡ ‹‹ዘ ኦርደር ኦፍ ዛይድ›› የተባለው ፕሬዚዳንታዊ ሜዳሊያ ለሁለቱ መሪዎች የተበረከተላቸው፣ በሁለቱ አገሮች መካከል ሰላም እንዲሰፍን ላከናወኑት ተግባር መሆኑን አልጋ ወራሹ ተናግረዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ ኢትዮጵያና የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ በሚኖራቸው ሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ ብቻ ሳይሆን፣ በአካባቢው ጂኦ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩ ለማወቅ ተችሏል፡፡ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ ኢትዮጵያና ኤርትራ ሰላም በማውረዳቸው ምክንያት ለሁለቱ መሪዎች ከፍተኛ ሜዳሊያ ማበርከቷና ከሁለቱም አገሮች ጋር የጠበቀ ግንኙነት መመሥረቷ፣ በአካባቢው ላይ ወደፊት እንዲኖራት ለምትፈልገው ተፅዕኖ ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት ይነገራል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሐምሌ 21 እስከ 23 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በአሜሪካ የሚያደርጉት ጉብኝት እንዲሳካ ዝግጅቱ መቀጠሉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡ በአሜሪካ ጉብኝታቸው በዋሽንግተን፣ በሎስ አንጀለስና በሚኒሶታ ለመጀመርያ ጊዜ በሰሜን አሜሪካ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር ይወያያሉ፡፡ እንደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የውይይት መርሐ ግብሮች በአሜሪካ ቢዘጋጁም፣ በመላው ዓለም የሚኖሩ የዳያስፖራ ማኅበረሰቦች የመርሐ ግብሮቹ አካል እንደሚሆኑ ይበጠቃል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሚዲያው በሕዝብ የህሊና ችሎት ከተዳኘ በቂ ነው!

መሰንበቻውን ድንገት ሳይታሰብ ያለ ማስጠንቀቂያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ...

የባህር በር ጉዳይ

በታምሩ ወንድም አገኘሁ ድሮ ድሮ ገና ልጅ ሆኜ ፊደል እንደቆጠርኩ...

አገሩ ፖለቲካዊ ስክነትና መደማማጥ ያስፈልገዋል

በንጉሥ ወዳጀነው    ኢትዮጵያ የሁላችንም የጋራ ቤት ነች፡፡ ‹‹ጥያቄዬ ተመለሰልኝ››፣...

የመንግሥት የሰብዓዊ መብት ተቋም ለምን የመንግሥት ሚዲያን ማስተማር አቃተው

በገነት ዓለሙ የአገራችን የ2016 የበጀት ዓመት መሰናበቻና የአዲሱ የ2017 በጀት...