ዓለም አቀፍ የቡና ቀን በኢትዮጵያ ለማክበር እንቅስቃሴ ተጀመረ፡፡ ኢትዮጵያ የቡና መገኛ ምድር ብትሆንም ይህን የማስተዋወቅ ሥራ በበቂ ሁኔታ እንዳልተሠራና ማግኘት የሚገባትን ጥቅም እንዳላገኘች ይታወቃል፡፡ በኅዳር 2011 ዓ.ም. ‹‹ዓለም አቀፍ የቡና ቀንን በምድረ ቀደምት ምድር እናክብር›› በሚል መሪ ቃል የሚከበረው፣ በዓለም አቀፍ የቡና ጉባዔና ዓውደ ርዕይ ዝግጅት ጭምር ነው፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የቡናና ሻይ ባለሥልጣን፣ የቡና ላኪዎች ማኅበርና የኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት የቡና ቀንን በጋራ ተባብረው ለማክበር መሥራት መጀመራቸውን ማክሰኞ ሐምሌ 18 ቀን 2010 ዓ.ም. በኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪዬሽን አካዴሚ በተሰናዳ ዝግጅት ቡናን በመቅመስ ይፋ አድርገዋል፡፡
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -
ፌርማታ ፅሁፎች
ትኩስ ፅሁፎች
- Advertisement -
- Advertisement -