Monday, July 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልሁለተኛው የሆሄ ሥነ ጽሑፍ ሽልማት የመጨረሻ ዕጩ መጻሕፍት ይፋ ሆኑ

ሁለተኛው የሆሄ ሥነ ጽሑፍ ሽልማት የመጨረሻ ዕጩ መጻሕፍት ይፋ ሆኑ

ቀን:

ለሁለተኛ ጊዜ በነሐሴ የመጀመርያ ሳምንት የሚዘጋጀው የሆሄ የሥነ ጽሑፍ ሽልማት 2009 .ም. ምርጥ መጻሕፍት ዕጩዎች ይፋ ሆኑ፡፡

ዓመታዊው የሆሄ የሥነ ጽሑፍ ሽልማት አዘጋጁ ኖርዝ ኢስት ኤቨንትስ ለሪፖርተር በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ የሽልማት ዝግጅቱ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ ከተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተውጣጡ የሥነ ጽሑፍ ምሁራን ታዋቂ ደራስያን እንዲሁም የሥነ ጽሑፍ ባለሙያዎች የተውጣጣ የዳኞች ኮሜቴ በማዋቀር ለውድድሩ የተመዘገቡ መጻሕፍትን ሲገመግም ሦስት ወራት ቆይቷል፡፡

ለዘንድሮው የሆሄ ሽልማት፣ 2009 .ም. የታተሙ በረዥም ልብወለድ ዘርፍ 20 መጻሕፍት፣ በልጆች መጻሕፍት ዘርፍ 17፣ እንዲሁም በግጥም መጻሕፍት ዘርፍ 24 መጻሕፍት ለውድድር ተመዝግበው ከእያንዳንዱ ምድብ አምስት አምስት ምርጥ መጻሕፍትን ለመለየት በዳኞች ግምገማ መካሄዱን ተቋሙ አስታውቋል፡፡

በዚህም መሠረት በረዥም ልብወለድ ምርጥ ተብለውተመረጡት ስማርድ (ንጉሴ መኮንን)፣ አለመኖር (ዳዊት ወንድማገኝ)፣ ጌርሳሞ (ዘርዓሰብ ሣጌጥ)፣ ዘር ቆርጣሚው (ዓለማየሁ በላይ)፣ በፍቅር ስም (ዓለማየሁ ገላጋይ)፤ በግጥም የተገለጡ ዓይኖች (ሰለሞን ሞገስ)፣ የማለዳ ድባብ (በዕውቀቱ ሥዩም)፣ ከሴተኛ አዳሪ የተኮረጀ ሳቅ (በላይ በቀለ ወያ)፣ የሀገሬ ንቅሳት (ሙሉዓለም ተገኘወርቅ)፣ ነፋስ ያነሳው ጥላ (ብርሃነ ሥላሴ ከበደ)፤ በልጆች ዘርፍ፡ የጎመጀ ጅብ (ዓለም እሸቱ)፣ ቴዎድሮስ (ዳንኤል ወርቁ)፣ አባባ ትልቁ እና ሌሎች ትምህርታዊ ተረቶች (የሺመቤት ካሳ)፣ ልዋም (ሰላማዊት ሐጎስ)፣ አሻንጉሊቴ (ዓለም እሸቱ) ናቸው፡፡

ከየዘርፉ አንደኛ የሚወጡትን የመጨረሻዎቹን አሸናፊዎች ለመለየት በዳኞች ከሚደረገው ዳግም ምዘና በተጨማሪ ከአንባቢያን የሚሰበሰበው ድምፅ ከአጠቃላይ ውጤቱ 20 በመቶ የሚይዝ ሲሆን፣ አንባቢያን በአጭር የስልክ ቁጥር 8240 ላይ ‹ha› የሚለውን ኮድ በማስቀደም አሸናፊ መሆን ይገባዋል የሚሉትን መጽሐፍ ርዕስ እስከ ነሐሴ 5 ቀን 2010 .ም. ድረስ መላክ ይችላሉ፡፡

የሽልማት መርሐ ግብሩ ነሐሴ 7 ቀን 2010 .ም. 1100 ሰዓት ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር እንደሚካሄድ፣ በመሰናዶው ከመጻሕፍቱ በተጨማሪ ለሥነ ጽሑፍ ዕድገትና ለንባብ ባህል መዳበር የላቀ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ግለሰቦችና ተቋማት እውቅና እንደሚሰጣቸው፣ ሥነሥርዓቱም በኢቢኤስ ቴሌቪዥን እንደሚተላለፍ ተገልጿል፡፡

ዓምናነሐሴ ወር በተካሄደው የመጀመሪያው የሆሄ የሥነ ጽሑፍ ሽልማት የአዳም ረታ የስንብት ቀለማት በረዥም ልብ ወለድ፣ የአበረ አያሌው ፍርድ እና እርድ በግጥም፣ እንዲሁም የአስረስ በቀለ የቤዛ ቡችላ በልጆች መጻሕፍት ዘርፍ አሸናፊ የነበሩ ሲሆን፣ የሕይወት ዘመን ሽልማቱን አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መሸለማቸው ይታወሳል፡፡

ዓመታዊው የሆሄ የሥነ ጽሑፍ ሽልማት ኖርዝ ኢስት ኤቨንትስ  ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ኤጄንሲ ጋር በመተባበር የሚያዘጋጀው ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሚዲያው በሕዝብ የህሊና ችሎት ከተዳኘ በቂ ነው!

መሰንበቻውን ድንገት ሳይታሰብ ያለ ማስጠንቀቂያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ...

የባህር በር ጉዳይ

በታምሩ ወንድም አገኘሁ ድሮ ድሮ ገና ልጅ ሆኜ ፊደል እንደቆጠርኩ...

አገሩ ፖለቲካዊ ስክነትና መደማማጥ ያስፈልገዋል

በንጉሥ ወዳጀነው    ኢትዮጵያ የሁላችንም የጋራ ቤት ነች፡፡ ‹‹ጥያቄዬ ተመለሰልኝ››፣...

የመንግሥት የሰብዓዊ መብት ተቋም ለምን የመንግሥት ሚዲያን ማስተማር አቃተው

በገነት ዓለሙ የአገራችን የ2016 የበጀት ዓመት መሰናበቻና የአዲሱ የ2017 በጀት...