Thursday, July 25, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህል‹‹ራህማቶ››

‹‹ራህማቶ››

ቀን:

‹‹በፍቅርና በጥላቻ መሀል ምን ይኖራል?

በተራራና በሜዳ መሀል ምን ይታያል?

በዝምታና በጩኸት መሀል ምን ይሰማል?

ጨለማና ብርሃንን…

ጦርነትና ሰላምን…

ሞትና ሕይወትን… የሚያስተሳስራቸውና የሚነጣጥላቸውን በየመሀላቸው ያለው ታላቁ ኃይል ምንድነው?››

መሰንበቻውን ለአራተኛ ጊዜ የኅትመት ብርሃን ያገኘው የሠዓሊና ገጣሚ አሰፋ ጉያ ‹‹ራህማቶ›› ልቦለድ ገፀ ባሕሪ ራህማቶ ዘወትር የሚያሳስበውና የሚያስጨንቀው ብሎ ያሠፈረው ኃይለ ቃል ነው፡፡ የራህማቶ የሥዕል ፍልስፍና በሁለት ተቃራኒ ነገሮችና ክስተቶች መሀል ስላሉ ልዩ ምስጢሮች መመርመር መጀመሩን ያሳያል፡፡

‹‹ማን ይናገር የነበረ ማን ያርዳ የቀበረ እንዲሉ የኪነ ጥበብንና የፍቅርን ግጭት፣ የእምነትንና የስሜትን ፍጭት፣ ኪናዊ ውጤቱንና የተራ ሕይወት ውልደቱን በረቀቀ ምናባዊ ስሌት እየተነተነ፣ በተባ ብዕሩና በተመልካችነት ሳይሆን በተሳታፊነት በዳበረ ልምዱ እየከሸነ ‹የብሩሿን ሕይወት› ባለብሩሹ ሊያስነብበን፣ ገበናዋን ገልጦ ሊያሳየን ተዘጋጅቷልና ፈረሱም ሜዳው ይኸው፤ የሚለውን ጽሑፍ በጀርባ ሽፋን ላይ ያኖረው ቴዎድሮስ ፍሥሐ ነው፡፡ ከሦስት አሠርታት በፊት የመጀመሪያው ኅትመቱ የወጣው ራህማቶ ያሁኑ ዋጋው 75 ብር ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

“ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የማደርገውን በረራ እንዳሳድግ ተጠይቄ ነበር” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያሳድግ የሚጠይቅ...
00:06:46

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...