Friday, December 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -

ጉማሬ

ቀን:

ጉማሬ ባብዛኛው ውኃ ውስጥ በመኖር ይታወቃል፡፡ ሰውነቱን ሙሉ ለሙሉ ውኃ ውስጥ ዘፍቆ ለ15 ደቂቃ ያህል መቆየትም ይችላል፡፡ በእነዚህ ጊዜያት አፍንጫውን ዘግቶ የመቆየት አቅምም አለው፡፡ በውኃ ውስጥ ሲሄድም አፍንጫውን ዘግቶ ነው፡፡

በቆዳቸው ላይ ፀጉር ከሌላቸው እንስሳ የሚመደበው ጉማሬ፣ ሙቀት በሚሆንበት ጊዜ ከፀሐይ የሚከላከለው ዘይት መሰል ቅባት በቆዳው ላይ አለው፡፡

 እስከ ሦስት ቶን የሚመዝን ሲሆን፣ በአንድ ምሽትም እስከ 40 ኪሎ ግራም ድረስ ይመገባል፡፡ የሚመደበውም ከቅጠላ ቅጠል በሊታዎች ነው፡፡

ቀን ላይ ሙቀትን ለመከላከል በውኃ ውስጥ የሚያሳልፍ ሲሆን፣ ምግቡን ለማግኘት ከውኃ የሚወጣው ምሽት ላይ ነው፡፡

በምድር ላይ ከሚኖሩ እንሰሳት ከዝሆንና ከአውራሪስ በመቀጠል በትልቅነቱ ይታወቃል፡፡ ጥንታዊ ግሪኮች ‹‹የወንዝ ፈረስ›› በሚል ቅፅል ስም የሚጠሩት ጉማሬ፣ በአፍሪካ በተለይም ከሰሃራ በታች በሚገኙ አገሮች የሚኖር ሲሆን፣ ሁለት ሊጠፉ የደረሱ ዝርያዎችም አሉት፡፡

አንድ ጉማሬ መውለድ የምትችለው በዓመት አንዴ ከውኃ ውጪ ነው፡፡ የመኖር ዕድሜያቸውም ከ40 እስከ 50 ይደርሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...