Thursday, February 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ አዲስ የመዋቅር ለውጥ ሰነድ ቀረበ

ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ አዲስ የመዋቅር ለውጥ ሰነድ ቀረበ

ቀን:

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ12 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ለአራተኛ ጊዜ ተግባራዊ ለማድረግ ያቀደው አዲስ መዋቅር፣ ባለፈው ዓርብ ሚያዝያ 7 ቀን 2008 ዓ.ም. ለካቢኔ አባላት ቀረበ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ አባላትና የሚመለከታቸው አካላት በዚህ ረቂቅ መዋቅር ላይ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ይወያያሉ ተብሏል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዲስ መዋቅር በፖለቲካ ተሿሚዎችና በባለሙያ ተቀጣሪዎች መካከል ላለው የተደበላለቀ የሥራ ድርሻ ድንበር እንዳበጀ ተገልጿል፡፡

በረቂቅ መዋቅሩ መሠረት ከንቲባውና ካቢኔያቸው በዋናነት የተቆጣጣሪነት ሚና ሲኖራቸው፣ የከተማው ዋና ሥራ አስኪያጅ ተቀጣሪ ባለሙያ ሠራተኛ ሆኖ አገልግሎት መስጫ አውታሮችን ይመራል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

‹‹በከንቲባውና በዋና ሥራ አስኪያጅ መካከል የሚኖረው ግንኙነት የቀጣሪና የተቀጣሪ ብቻ ነው፤›› በማለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አደረጃጀትና መዋቅር ጥናት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሰይፈ ፈቃዱ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባና ካቢኔያቸው በቀጥታ ተጠሪነቱ ለምክር ቤት ይሆናል፡፡ የሥራ ድርሻቸውም የሕዝብ ተመራጭና የፖለቲካ ተሿሚ እንደመሆናቸው የከተማውን ዕቅድ ማውጣት፣ ሕግና ደንቦች ማውጣት፣ እንዲሁም አፈጻጸማቸውን መቆጣጠር ይሆናል፡፡

ተጠሪነቱ ለከንቲባው የሚሆነው ዋና ሥራ አስኪያጅ ድርሻ ደግሞ፣ ማዘጋጃ ቤትና በከተማው የሚገኙ 84 የሚጠጉ መሥሪያ ቤቶችን መምራት ይሆናል፡፡

ይህ አሠራር ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዲስ እንደሆነ እየተነገረ ነው፡፡ ምክንያቱም አሁን ባለው አሠራር ሁሉም መሥሪያ ቤቶች ተጠሪነታቸው ለከንቲባው ነው፡፡ የከተማው ሥራ አስኪያጅ ብቻ ሳይሆን ባለሙያ የሚፈልጉ መስኮች ጭምር፣ በፖለቲካ ተሿሚዎች የተያዙ ናቸው በማለት ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ተናግረዋል፡፡ አዲሱ መዋቅር እነዚህን አሠራሮች በማስቀረት የከተማው አገልግሎት መስጫ ተቋማትን በሙሉ፣ በተቀጣሪ ባለሙያዎች የመምራት ዕድል ይፈጥራል ተብሏል፡፡

የአዲስ አበባ አደረጃጀትና መዋቅር ጥናት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ይህንን ጥናት ከ45 አገሮች ተሞክሮዎችን መውሰዱን፣ በዚህ ላይ ተመሥርቶ ባካሄደው ጥናት በከተማው 320 የአገልግሎት አሰጣጥ ክፍተቶች መኖራቸው ተገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ የመዋቅር ጥናት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱን ለማስተዋወቅ መስከረም 2008 ዓ.ም. በተጠራው ስብሰባ ላይ የመዋቅር ለውጡ ያስፈለገበትን ምክንያት ሲገልጹ፣ አዲስ አበባ በፈጣን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ላይ የምትገኝ በመሆኗ፣ ነገር ግን በከተማው አስተዳደር ፈጣኑን ዕድገት መሸከም የሚችል መዋቅር ባለመኖሩ ነው፡፡

‹‹አሁን ያለው መዋቅር ዕድገቱን ብቻ ሳይሆን ከዕድገቱ ጋር እየጨመረ ላለው የነዋሪዎች ፍላጐት ፈጣን ምላሽ መስጠት የሚችል አይደለም፤›› በማለት ከንቲባ ድሪባ በወቅቱ ተናግረዋል፡፡ ምክትል ከንቲባ አቶ አባተ ስጦታው በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት፣ የመዋቅር ለውጡ በጣም አስቸኳይ በመሆኑ እስከ ግንቦት 2008 ዓ.ም. ማለቅ እንዳለበት ተናግረው ነበር፡፡ በዚህ መሠረት በሚያዝያ ወር የመጨረሻው ረቂቅ መዋቅር ላይ ውይይቱ መካሄድ ጀምሯል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ጊዜያዊው አስተዳደር፣ በአቶ ኩማ ደመቅሳ የሥልጣን ዘመን፣ እንዲሁም ከወራት በፊት አሁን ባሉት አቶ ድሪባ ኩማ የሥልጣን ዘመን ሦስት ግዙፍ የመዋቅር ለውጦች በከተማው መካሄዳቸው ይታወቃል፡፡

አዲስ አበባ በአሁኑ ወቅት ለአራተኛ ጊዜ ግዙፍ የመዋቅር ለውጥ ለማድረግ እየተሰናዳች ነው፡፡     

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ የካቤኔ አባል የሆኑት አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሚያቀርቡትን ቅሬታ እያዳመጡ ነው] 

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር በእጅጉ ስላሳሰበኝ ነው በአካል...

የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔና የሶማሊያ ፕሬዚዳንት የፈጠሩት አምቧጓሮ

ባለፈው ቅዳሜና እሑድ በአዲስ አበባ የተካሄደው የአፍሪካ ኅብረት 37ኛው...

የብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ትግበራ የፈጠራቸው አሉታዊና አዎንታዊ ጎኖች

የአገሪቱ ንግድ ባንኮች በዓመት የሚሰጡት የብድር መጠን ላይ የኢትዮጵያ...

ቱግ ቱግ!

የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ ለመታደም የመጡ እንግዶችን ሸኝተን ከፒያሳ ወደ...