Thursday, July 25, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናአቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሳ ከዳሸን ቢራ ቦርድ አባልነት ተሰናበቱ

አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሳ ከዳሸን ቢራ ቦርድ አባልነት ተሰናበቱ

ቀን:

የዳሸን ቢራ ፋብሪካ የቦርድ አባል የነበሩት አቶ በረከት ስምኦን፣ አቶ ታደሰ ካሳና አቶ ወንድወሰን ከበደ ከቦርድ አባልነት መሰናበታቸው ይፋ ተደረገ፡፡

የዳሸን ቢራ ፋብሪካ የቦርድ ሰብሳቢ ሚስተር ዴቪድ ሃምፒሻየር ሐሙስ ሐምሌ 19 ቀን 2010 ዓ.ም. ይፋ ባደረጉት መሠረት፣ ሦስቱ የቦርድ አባላት መሰናበታቸው ተረጋግጧል፡፡

ፋብሪካው ባወጣው መግለጫ ተሰናባቾቹን የቦርድ አባላት የተኩት አዳዲሶቹ አባላት ማንነት ታውቋል፡፡ በዚህም መሠረት የቀድሞ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር የአሁኑ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አቶ አህመድ አብተው፣ በቅርቡ የብሔራዊ ባንክ ገዥ የሆኑት ይናገር ደሴ (ዶ/ር)፣ እንዲሁም የቀድሞ የአማራ መልሶ ማቋቋም ድርጅት ዋና ዳይሬክተርና የአሁኑ የጥረት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አምላኩ አስረስ (ዶ/ር) ናቸው፡፡

የቀድሞው የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ሚኒስትር  አቶ በረከት ስምኦን፣ የቀድሞ የጥረት ኮርፖሬት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታደሰ ካሳና አቶ ወንድወሰን ከበደ ከስድስት ዓመታት የቦርድ አባልነት ቆይታ በኋላ መሰናበታቸው ተገልጿል፡፡

ሚስተር ሃምፒሻየር ለአዲሶቹ የቦርድ አባላት ባስተላለፉት መልዕክት፣ የአዲሶቹ የቦርድ አባላት ምርጫ የፋብሪካው ባለቤቶች ለወራት በዓለም አቀፍ ደረጃ ባለተሰጥኦ የሆኑና ልምድ ያካበቱ ተወዳዳሪዎችን ሲፈልጉ ከቆዩ በኋላ የተሳካ መሆኑን መናገራቸው በመግለጫው ተመልክቷል፡፡ በአመራር ክህሎታቸው የላቁ ሦስት የቦርድ አባላት በመገኘታቸውም ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው መግለጻቸው በመግለጫው ተካቷል፡፡

አዲሶቹ የቦርድ  አባላት ከዚህ ቀደም ከነበሩት የቦርድ አባላት ማለትም ሚስተር ሔንሪ ጋባይ፣ ጃኪስ ፈርጊስና ፔድሮ ሎታ ጋር ድርጅቱን እንዲመሩ በይፋ መሾማቸው ተገልጾ፣ እ.ኤ.አ. ከሜይ 14 ቀን 2018 ጀምሮ የቦርድ አባልነታቸው ተግባራዊ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የዳሸን ቢራ ፋብሪካ 49 በመቶ የተያዘው በአማራ ክልል በባህር ዳር በብአዴንና በ25 አባላቱ በተመሠረተው በጥረት ኮርፖሬት ሲሆን፣ የእንግሊዝ የኢንቨስትመንት ኩባንያ ዱኤት ደግሞ 51 በመቶ ድርሻ አለው፡፡ በ1992 ዓ.ም. በጎንደር የመጀመርያ ፋብሪካውን የመሠረተው ዳሸን ቢራ፣ በ2007 ዓ.ም. ሁለተኛ ፋብሪካውን በደብረ ብርሃን ማስመረቁ ይታወሳል፡፡ ከፍተኛ ባለድርሻ የሆነው የእንግሊዝ ኩባንያ ዱኤት የዳሸን ቢራን ቦርድ አብላጫ ድርሻ ከመያዙም በላይ ሰብሳቢውም የኩባንያው ወኪል ናቸው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

“ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የማደርገውን በረራ እንዳሳድግ ተጠይቄ ነበር” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያሳድግ የሚጠይቅ...
00:06:46

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...