Tuesday, December 5, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ከሥራ መታገዳቸው ታወቀ

የኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ከሥራ መታገዳቸው ታወቀ

ቀን:

የኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በግልጽ ባልታወቀ ምክንያት ከሥራ መታገዳቸውን የሪፖርተር ምንጮች ገለጹ፡፡

እንደ ምንጮቻችን ገለጻ ከአሥር በላይ የሚሆኑ የኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ የሥራ አመራሮች ከሐምሌ 3 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ከሥራ ታግደዋል፡፡

ከታገዱት መካከል የኢትዮ ቴሌኮም የኢንተርፕራይዝ ዲቪዥን የፐብሊክ ሰርቪስ ኢንተርፕራይዝ ዘርፍ ኃላፊ፣ የአውቶሜሽን ዘርፍ ከፍተኛ ኦፊሰር፣ የኢትዮ ቴሌኮም መሠረተ ልማት የፊዚካል ሴኪዩሪቲ ዘርፍ ኃላፊ እንደሚገኙበት ምንጮች ገልጸዋል፡፡

ከተገለጹት የሥራ ኃላፊዎች በተጨማሪ በተመሳሳይ የኃላፊነት ደረጃ በሌሎች ዘርፎች የተመደቡ፣ በአጠቃላይ 13 ኃላፊዎች በግልጽ ባልታወቀ ምክንያት መታገዳቸው ተገልጿል፡፡

መታገዳቸውን የሚገልጸው ደብዳቤ ምክንያቱን እንደማይጠቅስ ምንጮች የገለጹ ሲሆን፣ ተፈርሞ የወጣውም ከሳምንት በፊት ከኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚነት በተነሱት አንዷለም አድማሴ (ዶ/ር) መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የቀድሞው ዋና ሥራ አስፈጻሚ 13 ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ከሥራ የሚያግድ ደብዳቤ በሰጡ ከሳምንት በኋላ፣ እሳቸው ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) እንደደረሳቸው ታውቋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በእሳቸው ምትክ ወ/ት ፍሬሕይወት ታምሩን በዋና ሥራ አስፈጻሚነት እንደሾሙ መዘገባችን ይታወሳል፡፡

የቀድሞው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ደግሞ የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አድርገው ሾመዋቸዋል፡፡

የሥራ ኃላፊዎቹ የታገዱት ሰኔ 16 ቀን 2010 በመስቀል አደባባይ የድጋፍ ሠልፍ የቦምብ ጥቃት ከተፈጸመ በኋላ፣ በአካባቢው የስልክ ኔትወርክ ከመጥፋቱ ጋር በተገናኘ እንደሆነ የሪፖርተር ምንጮች ቢገልጹም ማረጋገጥ ግን አልተቻለም፡፡

ጉዳዮን በተመለከተ መረጃ እንዲሰጡ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የኢትዮ ቴሌኮም የኮርፖሬት ሕዝብ ግንኙነት ከፍተኛ ኦፊሰር አቶ አብዱራሂም አህመድ መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...