Friday, December 2, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ስፖርትፅንፈኝነት የነገሠበት እግር ኳስ

  ፅንፈኝነት የነገሠበት እግር ኳስ

  ቀን:

  የኢትዮጵያ እግር ኳስ ‹‹ፕሪሚየር ሊግ›› የሚለውን መጠሪያ ይዞ ከተቋቋመ እነሆ ሁለት አሠርታትን ለመድፈን ከጫፍ ደርሷል፡፡ እስካሁን ባለው ሒደቱም ከዕድገቱ ይልቅ ውድቀቱ፣ ከአዝናኝነቱ ይልቅ የሁከት መንስኤነቱ ሚዛን ደፍቶ ስለመገኘቱ ብዙዎች የሚስማሙበት ሐቅ ከሆነም ሰነባብቷል፡፡

  በተለይም በአሁኑ ወቅት በፕሪሚየር ሊግ ደረጃ 14 ክለቦች፣ በሱፐር ሊግ ደረጃ 32 ክለቦች እንዲሁም በብሔራዊ ሊግ ደረጃ ደግሞ ከሰባ በላይ ቡድኖች እግር ኳሱን በመላ አገሪቱ ለማስፋፋት ይችሉ ዘንድ ኃላፊነት ወስደው እየተንቀሳቀሱ ይገኛል፡፡ ከእነዚህ በታችም እንደየደረጃው የሊግ ስያሜ ተሰጥቷቸው በሚወጣላቸው የውድድር መርሐ ግብር መሠረት እየተወዳደሩ የሚገኙ በርካታ መኖራቸውን ይታመናል፡፡

  በጣት ከሚቆጠሩ ጥቂት ክለቦችና ቡድኖች በስተቀር በአብዛኛው ከመንግሥት ቋት በሚሰጥ በጀት የሚተዳደሩ ስለመሆናቸውም የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ ይኼ ሁሉ መዋለ ነዋይ እየፈሰሰበት የሚገኘው የአገሪቱ እግር ኳስ በተለይም ከጥቂት ዓመታት ወዲህ የአዲስ አበባ ስታዲየምን ጨምሮ በሁሉም አካባቢዎች የጽንፈኝነትና የሁከት መናኸሪያ እየሆኑ መታየቱ በተለይ ለሰላማዊው የእግር ኳስ ቤተሰብ ሥጋት ሆኗል፡፡ ስታዲየሞችና የእግር ኳስ ሜዳዎች ወጣቶች በስፖርታዊ ጨዋነት በአግባቡ ቡድናቸውን የሚያበረታቱበት ሰላማዊ መድረኮች መሆናቸው ቀርቶ ጎራ ለይተው እንኪያ ሰላምታ የሚገጥሙበት፣ ከዚያም ሲያልፍ የሕዝብና የመንግሥት ንብረቶች ያለአግባብ ለጉዳት የሚዳረጉበት፣ የሰዎች ሰብአዊ መብት የሚረገጡበት ከሆኑም ዓመታት መቆጠራቸው ይነገራል፡፡

  አቶ ወንድምኩን እሸቴ ‹‹ሳይቃጠል በቅጠል›› የሚለውን የአበው ብሂል በማስቀደም ይህንኑ በእግር ኳሱ አካባቢ የሚስተዋለውን የስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል አምርረው ከሚኮንኑ ይጠቀሳሉ፡፡

  እንደ አስተያየት ሰጪው፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ ክለቦች፣ የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎችና ሌሎችም የሚመለከታቸው አካሎች የችግሩን አሳሳቢነት ግምት ውስጥ በማስገት አቅጣጫ ሊያስቀምጡለት እንደሚገባም ይናገራሉ፡፡ ‹‹ተመልካቾችና የክለብ ደጋፊዎች የስታዲየም ውበት ናቸው፤›› እየተባለ በሚነገርበት በዚህ ወቅት አሁን ባለው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ተመልካቾች የሚበዙበትን ጨዋታ እሳቸውን ጨምሮ በስታዲየም ታድሞ ለመከታተል ፈጽሞ የማይቻልበት ሁኔታ መፈጠሩን በመግለጽ ሥጋታቸውን ያክላሉ፡፡

  ከሰሞኑ በተከናወኑ የሁለተኛ ዙር የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች የአዲስ አበባ ስታዲየም የሚስተዋለው ሁከትና ብጥብጥ እግር ኳሳዊ ይዘቱን እየለቀቀ ስለመምጣቱ ጭምር ይናገራሉ፡፡ በስታዲየሙ ለመቀመጫነት የተቀመጡ የፕላስቲክ ወንበሮች በተመልካቾች መካከል በሚፈጠር ሁከት የአገልግሎት ጊዜያቸው እያበቃለት ከመሆኑ ጎን ለጎን፣ ተመልካቾች የሚደባደቡባቸው እየሆኑ መምጣቱን የሚናገሩት አቶ ወንድምኩን፣ ይኼ ጅምር በሚመለከታቸው አካሎች ከወዲሁ መፍትሔ ካልተበጀለት መጨረሻው እንደማያምር ያስረዳሉ፡፡

  ብሔራዊ ፌዴሬሽኑና ክለቦች በጋራ ለሚያወጡዋቸው መመሪያዎችና ደንቦች ተገዥ መሆን ብቻ ሳይሆን፣ መድረኮችን በመፍጠር ስታዲየሞች ሕፃናትና ሴቶች እንዲሁም በዕድሜ የገፉ አረጋውያን የሚታደሙበት ይሆኑ ዘንድ አበክረው ሊሠሩ እንደሚገባ ጭምር ይናገራሉ፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

  ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው አዋሽ ባንክ የ43 ቢሊዮን...

  አቢሲኒያ ባንክ ካለፈው ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

  አቢሲኒያ ባንክ ከቀደሚ የሒሳብ ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው...