Friday, December 2, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ስፖርትኢትዮጵያውኑ የደመቁበት ቦስተን ማራቶን

  ኢትዮጵያውኑ የደመቁበት ቦስተን ማራቶን

  ቀን:

  የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር (አይኤኤኤፍ)፣ በወርቅ ደረጃ ከሚመድባቸው ታላላቅ የማራቶን ውድድሮች አንዱ የቦስተኑ ማራቶን ከትናንት በስቲያ ሚያዝያ 10 ቀን 2008 ዓ.ም. ተካሂዷል፡፡ ኢትዮጵያውያኑ በሁለቱም ጾታ አሸናፊ ሆነዋል፡፡ በሴቶች አፀደ ባይሳ በበላይነት ስታጠናቅቅ፣ በወንዶች ደግሞ ለሚ ብርሃኑ ድል ቀንቶታል፡፡

  በመጪው ነሐሴ በብራዚል ሪዮ ዴጄኔሮ በሚካሄደው 31ኛው ኦሊምፒያድ እየተቃረበ ባለበት በዚህ ወቀት፣ በቦስተን በድል የደመቁት ኢትዮጵያውኑ አትሌቶች ከወዲሁ ትልቅ ግምት እንዲሰጣቸው አድርጓል፡፡ ከወንዶቹ ዘግይቶ በጀመረው የሴቶች ውድድር አፀደ ባይሳ ርቀቱን 2 ሰዓት 29 ደቂቃ ሰከንድ ጊዜ 19 በሆነ ሰዓት ስታጠናቅቅ፣ ሌላዋ የአገሯ ልጅ ትርፊ ፀጋዬ በበኩሏ 2፡30፡03 ተከታዩን ሁለተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች፡፡ የኢትዮጵያውያኑ የምንጊዜም ተቀናቃኝ ኬንያዊቷ ጆሲ ቼፕኩሪያ ደግሞ ርቀቱን 2፡30፡50 አጠናቃ የነሐስ ሜዳሊያ ባለቤት ሆናለች፡፡

  እንደ ዘገባው ከሆነ፣ በቦስተን ማራቶን ድል የተቀዳጀችው አፀደ ባይሳ የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊት ስትሆን በ2002 ዓ.ም. በተደረገው ተመሳሳይ ውድድር ጠይባ ኤርኬሶ ሦስተኛ በመሆን ማጠናቀቅ የቻለችበት ታሪክ መኖሩ ተጠቅሷል፡፡

  በወንዶች በተደረገው ተመሳሳይ ውድድር ግምት ያልተሰጠው ለሚ ብርሃኑ ርቀቱን 2 ሰዓት ከ12ደቂቃ 45 ሰከንድ በሆነ ጊዜ አጠናቆ አሸናፊ ሲሆን፣ ሌላው ሌሊሳ ዴሲሳና የማነ ፀጋዬ ርቀቱን 2፡13፡32 እና 2፡14፡ 02 አጠናቀው ተከታትለው በመግባት አይበገሬነታቸውን አረጋግጠዋል፡፡ ኬንያዊው የ2004 ዓ.ም. አሸናፊ ዌስሊ ኮሪር ርቀቱን 2፡14፡05 አጠናቆ አራተኛ ሆኖ ማጠናቀቁ ታውቋል፡፡

  የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለ2016 የሪዮ ኦሊምፒክ መደበኛ ዝግጅቱን እያደረገ ይገኛል፡፡ ኢትዮጵያን ወክለው ለሚቀርቡ ተወዳዳሪዎች ከ400 ሜትር ጀምሮ እስከ ማራቶን አትሌቶች ለኦሊምፒክ የሚያበቃቸውን ሚኒማ የሚያሟሉበት ቀነ ገደብ አስቀምጧል፡፡ በዚሁ መሠረት በተለይም በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ የውድድር ትኩረት እያጣ መምጣቱ የሚነገርለት፣ ሆኖም ኢትዮጵያውያኑ ደግሞ በሁለቱም ጾታ በውጤታማነታቸው የሚታወቁበት የ10,000 ሜትር ተወዳዳሪዎች ለሚኒማ የሚያበቃቸውን ውድድር ራሱ ፌዴሬሽኑ አፈላልጎ እስከ ሰኔ 24 ቀን 2008 ዓ.ም. ድረስ ጊዜ እንደሚሰጥ አስታውቋል፡፡

  ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ከኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ጋር በመሆን መደበኛውንና ዋናውን ዝግጅት እያደረገ ይገኛል፡፡ ለሚኒማ በተቀመጠው ቀነ ገደብ መሠረት ከ800 እስከ 500 ሜትር ሐምሌ 4 ቀን 2008 ዓ.ም. ድረስ፣ ለ5000 ሜትር ደግሞ ሰኔ 24 ቀን መሆኑንም ይፋ አድርጓል፡፡ ቀነ ገደቡ ካለፈ በኋላ የሚመዘገቡ ሚኒማዎች ዋጋ ቢስ መሆናቸውንም አስታውቋል፡፡ የማራቶን ቀነ ገደብ በሚቀጥለው ሳምንት ሚያዝያ 16 ቀን 2008 ዓ.ም. ያበቃልም ተብሏል፡፡

  በሌላ በኩል እስካሁን ባለው መረጃ መሠረት ኢትዮጵያ በብራዚል የሪዮ ዴጄኔሮ ኦሊምፒክ በሦስት የስፖርት ዓይነት ማለትም በአትሌቲክስ፣ በውኃ ዋናና በብስክሌት በአንድ ወንድ ብቻ የምትወከል ሲሆን፣ አገሪቱ ትወከልበታለች ተብሎ ቅድመ ግምት ተሰጥቶት የቆየው ቦክስ በቅርቡ በሞሮኮ በተደረገው ማጣሪያ ሳይሳካ መቅረቱም ታውቋል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

  ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው አዋሽ ባንክ የ43 ቢሊዮን...

  አቢሲኒያ ባንክ ካለፈው ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

  አቢሲኒያ ባንክ ከቀደሚ የሒሳብ ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው...