Friday, December 8, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትብሔራዊ ቡድኑ ከአዲሱ አሠልጣኝ ጋር ዝግጅቱን በነሐሴ ይጀምራል

ብሔራዊ ቡድኑ ከአዲሱ አሠልጣኝ ጋር ዝግጅቱን በነሐሴ ይጀምራል

ቀን:

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ አዲሱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ በይፋ አስተዋወቀ፡፡ አሠልጣኝ አብርሃም መብራቱ ዋሊያዎቹን ለመጪዎቹ ሁለት ዓመታት ለመምራት ተስማምተዋል፡፡

ሰኞ ሐምሌ 23 ቀን 2010 ዓ.ም. የስምምነቱን ይዘት በዝርዝር ይፋ ያደረገው ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ፣ የወደፊት የቤት ሥራዎችን በተመለከተም ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ለረዥም ጊዜ ያለ አሠልጣኝ መቆየቱን ተከትሎ፣ ዝግጀቱን ከነሐሴ 1 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ሐዋሳ ከተማ መካሄድ እንደሚጀምር አሠልጣኝ አብርሃም አስታውቀዋል፡፡

ነሐሴ 1 ቀን 2010 ዓ.ም. የሚያደርገውን የወዳጅነት ጨዋታ በተመለከተም በቅርቡ ከኤርትራ ብሔራዊ ቡድን ጋር ሊደረግ ከታቀደው የወዳጅነት ጨዋታ በተጨማሪ ከሁለት የምዕራብ አፍሪካ አገሮች ጋር ጨዋታ ለማድረግ ማቀዳቸውን አዲሱ አሠልጣኝ ተናግረዋል፡፡

በየመን ከአሥር ዓመታት በላይ በአሠልጣኝነት የሠሩት አሠልጣኝ አብርሃም፣ የስልክ ወጪያቸውን ጨምሮ በወር 125 ሺሕ ብር እንደሚከፈላቸው ተገልጿል፡፡

በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ወቅት አዲሱ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ እንደተናገሩት ከሆነ፣ እ.ኤ.አ. እስከ 2020 የቻን ውድድር ድረስ ጠንካራና ተፎካካሪ ቡድን መመሥረት የስምምነቱ ቀዳሚ ዕቅድ ነው፡፡

አሠልጣኙ በመን ሊግ መቆየታቸውንና ልምድ ማካበታቸውን ተከትሎ የተጨዋች ምርጫ ላይ ‹‹አይቸገሩም ወይ?›› የሚል ጥያቄ ተነስቶላቸው ሲመልሱ፣ ለኢትዮጵያ ሊግ ቅርበት እንዳላቸው፣ አዲስ የሚመርጧቸው የምክትል አሠልጣኞች ዕገዛና ብሔራዊ ቡድኑ በውጭ ያደረጋቸውን ጨዋታዎች (የቪዲዮ ቅጅዎች) በመመልከት ምርጫ እንደሚያከናውኑ አብራርተዋል፡፡

አሠልጣኙ ምክትል አሠልጣኞቻቸው በመጪዎቹ ጥቂት ቀናት ውስጥ ይፋ እንደሚያደርጉ የገለጹ ሲሆን፣ በአዲሱ አሠልጣኝ መዋቅር ውስጥ የምግብ ባለሙያ፣ የሚዲያ ባለሙያ፣ የአካል ብቃት አሠልጣኝና የቪዲዮ ተንታኝ ይካተታሉ ተብሏል፡፡ ለዚህም ፌዴሬሽኑ አወንታዊ ምላሽ መስጠቱ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጳጉሜን ላይ የሚያደርገውን የአፍሪካ ዋነጫ ሁለተኛ የምድብ ጨዋታ ከዚህ ቀደም ዓለም አቀፍ ጨዋታዎች ላይ ልምድ ያላቸው ተጨዋቾችና ወጣቶችን በማካተት ዝግጅታቸውን ሐዋሳ ላይ እንደሚጀምሩ አሠልጣኙ አስታውቀዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...