Sunday, June 23, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ደረጃዎች ኤጀንሲ 493 ደረጃዎችን አፀደቀ

spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

– የጥበቃ አገልግሎት ደረጃ ይወጣለታል

ብሔራዊ የደረጃዎች ምክር ቤት 493 የምርትና አገልግሎት ደረጃዎችን በማፅደቅ ወደ ሥራ ማስገባቱን አስታወቀ፡፡ የጥበቃ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት የሚገዙበት የአገልግሎት ደረጃ ለማውጣት ጥናት መጀመሩ ተገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ ባለፈው ሐሙስ ይፋ እንዳደረገው ከፀደቁት ደረጃዎች ውስጥ 324 አዲስ ናቸው፡፡ 157 ደረጃዎች ደግሞ የተከለሱ መሆናቸው ተገልጿል፡፡ 12ቱ ደግሞ ከዚህ ቀደም ባሉበት እንዲቀጥሉ ተብሏል፡፡

በብሔራዊ ምክር ቤቱ ከፀደቁት ደረጃዎች ውስጥ 98ቱ በግብርና ምግብ ዘርፍ የተካተቱ ናቸው፡፡ 28ቱ ደግሞ በኬሚካልና በኬሚካል ውጤቶች፣ 27 በጨርቃጨርቅ፣ 79 በኮንስትራክሽን፣ 83 በኤሌክትሮሜካኒካል፣ 34 በመሠረታዊና አጠቃላይ ደረጃ፣ 44 በአካባቢና ጤና ደኅንነት ዘርፍ የተመደቡ ናቸው፡፡ በግብርና ምግብ የደረጃ ዝግጅት ዘርፍ 31 አዲስ፣ 55 የተከለሱ እና 12 ደረጃዎችን በማስቀጠል የተዘጋጀ ነው፡፡

በኬሚካልና ኬሚካል ውጤቶች የደረጃ ዝግጅት ዘርፍም 98 አዲስ፣ 30 በክለሳ የተዘጋጁ ደረጃዎች የኢትዮጵያ ደረጃዎች መስፈርት መሠረት ሥራ ላይ እንዲውሉ መወሰኑን የኤጀንሲው ዳይሬክተር ወ/ሮ አልማዝ ካሣዬ ገልጸዋል፡፡

የእነዚህ ደረጃዎች መውጣት ለማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪና ለንግድ የተወዳዳሪነትን አቅም ለማጎልበት ይረዳሉ፣ ለቴክኖሎጂ ሽግግር፣ ፈጠራና የዕውቀት ምንጭ በመሆን ክህሎትን ለማሳደግ ጉልህ ሚና ይኖራቸዋል ተብሏል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከኅብረተሰቡ ጤናና ደህንነት፣ ከአካባቢ ጥበቃና የሸማቾችን ጥቅም ከማስጠበቅ አኳያ ጉልህ አስተዋፅኦ ሊያበረክቱ እንደሚችሉም በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ተመልክቷል፡፡

እንደ ኤጀንሲው ኃላፊዎች ገለጻም አምራቾችና አስመጪዎች፣ የሕክምና ተቋማት፣ ተቆጣጣሪ መሥሪያ ቤቶችና በዝርዝሩ የተጠቀሱ ደረጃዎችን መጠቀም የሚፈልጉ መሥሪያ ቤቶችና ግለሰቦች ደረጃዎቹ መኖራቸውን አውቀው እንዲሠሩ አሳስበዋል፡፡ ደረጃዎቹን በመጠቀም የምርቶቻቸውን ጥራት በማሻሻልና ጥራታቸውን ያሟሉ ሸቀጦች ወደ አገር ውስጥ በማስገባት ወይም ወደ ውጪ በመላክ ይኖርባቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ በኮንስትራክሽንና ሲቪል ኢንጂነሪንግ የደረጃ ዝግጅት ዘርፍ 79 አዲስ የኢትዮጵያ ደረጃዎች ሥራ ላይ ይውላል ተብሏል፡፡ በኤሌክትሮ ሜካኒካል የደረጃ ዝግጅት ዘርፍ 22 አዲስ ኃላፊዎች ተቀርጸዋል፡፡ በክለሳ በድምሩ 83 የኢትዮጵያ ደረጃዎች በመሠረታዊና አጠቃላይ የደረጃ ዝግጅት ዘርፍ 26 አዲስ፣ ከእነዚህ ውስጥ ስምንቱ በክለሳ በድምሩ 34 የኢትዮጵያ ደረጃዎች ይኖራሉ፡፡ በአካባቢና ጤና ደህንነት የደረጃ ዝግጅት ዘርፍ 41 አዲስ ሦስት በክለሳ በድምሩ 44 የኢትዮጵያ ደረጃዎች እንደተዘጋጀ ተመልክቷል፡፡

ከፀደቁት ደረጃዎች መካከል የአካባቢ ብክለትን ከመከላከል አንፃር ከፍተኛ ሚና ሊጫወቱ የሚችሉ የዕቃ መያዥያ ፕላሲቲክ ከረጢቶች፣ የማዕድናትን ጥራትን በማስጠበቅ ወደ ውጭ ገበያ ገብተው ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ያስችላል፡፡ የተጣራ የወርቅ ደረጃን፣ የከሰል ማዕድን ደረጃዎች ከመካተታቸው ባሻገር በእጅ የተሠሩ የመሬት ምንጣፎች፣ ብረቶች፣ የተቀቀለ ጣውላ፣ ፋይዚት፣ በገመድ የሚጎተት የመጠጥ ውኃ ፓምፕና የመሳሰሉት ምርቶች ደረጃ ከወጣላቸው ውስጥ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ የስትራላይዜሽን፣ የማደንዘዥያ መድሃኒቶች መስጫ መሣሪያዎችን አያያዝ አስመልክቶ ማሟላት ያለባቸውን መሥፈርቶች ደረጃ ከወጣላቸው ውስጥ ተካትተዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በአሁኑ ወቅት በአገልግሎት ዘርፍ ከተሰማሩ ተቋማት ውስጥ የጥበቃ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሚገዙበት የአገልግሎት ደረጃ ሥራ ላይ ለማዋል ጥናት እየተደረገ ነው ተብሏል፡፡ የኤጀንሲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ይስማው ለሪፖርተር እንደገለጹት ደረጃ ይወጣላቸዋል ተብለው ከሚጠበቁት ውስጥ አንዱ የጥበቃ አገልግሎት ተቋማትን የሚመለከት ነው፡፡ ይህ ደረጃ ተቋሞቹ እንዴት እንደሚሠሩ የሚያመላክት ደረጃ ይሆናል፡፡ በአሁኑ ወቅትም ጥናቱ መጀመሩን ገልጸዋል፡፡

እየወጡ ባሉ ደረጃዎች መሠራቱን ለመከታተልና ለመቆጣጠር የሚችል አንድ ተቋም ይፈጠራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ 

አሁን የሚሠራው አሠራር ደረጃውን መሬት አውርዶ ሊያስፈጽም የሚችል አካል እየተገለጸበትና ኃላፊነት እየተሰጠው ደረጃዎቹ እንዲተገበሩ የንቅናቄ ሥራ ይሠራል፡፡

በተለይ ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ ቀዳሚ ክንውን ይሆናል ያሉት የሥራ ኃላፊዎቹ ኅብረተሰቡ የብሔራዊ ደረጃዎች ያሉባቸውን ምርቶች የመጠቀም ባህሉ እንዲዳብር ለመሥራት ታቅዷል፡፡  

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች