Tuesday, November 28, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊኤርፖርት ውስጥ የሚያዘው የኮኬይን መጠን መጨመሩ ተገለጸ

ኤርፖርት ውስጥ የሚያዘው የኮኬይን መጠን መጨመሩ ተገለጸ

ቀን:

ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ውስጥ እየተያዘ ያለው ኮኬይን በከፍተኛ መጠን እየጨመረ እንደሆነ ተገለጸ፡፡ የፌዴራል ፖሊስ የአደገኛ ዕፅ መቆጣጠሪያ ክፍል ኃላፊ ኮማንደር ፀጋዬ ወልደ ሕይወት ባለፈው ሳምንት በተካሄደ የውይይት መድረክ ላይ ነው ይህንን የገለጹት፡፡

በሌሎች አገሮች በባህር ትራንስፖርት አማካይነት በወደብ በኩል በሚገባው መጠን ልክ፣ በሻንጣና በተለያዩ መንገዶች የኢትዮጵያ አየር መንገድን በመጠቀም ለማስገባት ሲሞከር እየተያዘ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ እ.ኤ.አ. ከ2011 በፊት የኮኬይን መጠን ብዙም ችግር እንዳልነበር፣ በተለይም ከተጠቀሰው ጊዜ በኋላ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የብራዚል ሳኦፖሎ በረራን ተከትሎ ቦሌ ኤርፖርት የሚያዘው የኮኬይን መጠን በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ኮማንደር ፀጋዬ ጠቁመዋል፡፡

እሳቸው እንደገለጹት የአየር መንገዱን የደቡብ አሜሪካ በረራ ተከትሎ ኢትዮጵያ ከደቡብ አሜሪካ ወደ አውሮፓና እስያ ኮኬይን ለማስተላለፍ በወንጀለኞች ተመራጭ መተላለፊያ መስመር እየሆነች ነው፡፡ ‹‹ከ2011 በፊት ግን እንደዚህ ተመራጭ መተላለፊያ አልነበረችም፤›› ብለዋል፡፡

ይህ ከፍተኛ የኮኬይን መጠን ሥጋት እየፈጠረ እንዳለና ከተጠቀሰው ጊዜ ጀምሮ የአገር ውስጥ የኮኬይን ሥርጭትም መጨመሩ ተገልጿል፡፡ ኮኬይን በማዘዋወር በቁጥጥር ሥር ከሚውሉ የውጭ አገር ዜጐች አብላጫውን ቁጥር የሚይዙት ናይጄሪያውያን መሆናቸውን ኮማንደር ፀጋዬ ተናግረዋል፡፡ እ.ኤ.አ. በ2014 ብቻ 66 የውጭ አገር ዜጐች በቁጥጥር ሥር ውለው 141 ኪሎ ግራም ኮኬይን እንደተያዘ ገልጸዋል፡፡ እ.ኤ.አ. በ2016ም 42 የሚሆኑ ጉዳዮች በማጋጠማቸው ከፍተኛ መጠን ያለው ኮኬይን ተይዟል፡፡

በሌላ በኩል ኮማንደሩ እንደገለጹት፣ በአገር ውስጥ ካናቢስን በስፋት በማብቀል የገቢ ምንጭ የማድረግ እንቅስቃሴም አሳሳቢ ሆኗል፡፡ ይህም የአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ገበያን ዒላማ ያደረገ ነው ተብሏል፡፡ ካናቢስን በተለያዩ ዘዴዎች በፖስታ ቤት የመላክ እንቅስቃሴዎች እየታዩ መሆናቸውን፣ ላኪዎች የተቀባዩን ትክክለኛ አድራሻ በማስፈር የራሳቸውን ግን ሐሰተኛ ስለሚያደርጉ እነሱን ተጠያቂ ማድረግ አስቸጋሪ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

በመድረኩ ተሳታፊ የነበሩ የአዕምሮ ሕክምና ባለሙያዎች፣ ቀደም ባሉት ዓመታት ብዙም ያጋጥም ያልነበረው የኮኬይን ጉዳይ በአሁኑ ወቅት እየበዛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር መስፍን አርዓያ፣ ‹‹ለብዙ ዓመታት በአዕምሮ ሕክምና አሳልፌያለሁ፡፡ በኮኬይን ጉዳይ ግን ተቸግሬ አላውቅም ነበር፤›› በማለት አደገኛው ዕፅ በዜጐች የአዕምሮ ጤና ላይ እያደረሰ ያለውን ተፅዕኖ አስረድተዋል፡፡

የተሻሻለው የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ አንቀጽ 525 አደገኛ ዕፅ ወደ አገር ውስጥ ለማስገባትም ሆነ ለማስወጣት መሞከር ከአሥር ዓመት የማያንስ ጽኑ እስራትና ከ200,000 ብር የማይበልጥ መቀጮ እንደሚያስቀጣ ያስረዳል፡፡   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለሲኒመር ትሬዲንግ አ/ማ አባላት በሙሉ የጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪ

ለሲኒመር ትሬዲንግ አ/ማ አባላት በሙሉ የጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪ ሲኒመር ትሬዲንግ...

የባህር በር በቀጣናዊ ተዛምዶ ውስጥ

በበቀለ ሹሜ መግቢያ በ2010 ዓ.ም. መጋቢት ማለቂያን ይዞ ዓብይ አህመድ በጠቅላይ...

ሥጋት ያስቀራል ተብሎ የሚታሰበው የጫኝና አውራጅ መመርያ

በአዲስ አበባ ከተማ በሕገወጥ መልኩ በመደራጀት ማኅበረሰቡ ላይ እንግልትና...

ማወቅ ወይስ አለማወቅ – ድፍረት ወይስ ፍርኃት?

በአሰፋ አደፍርስ ወገኖቼ ፈርተንም ደፍረንም የትም አንደርስምና ለአገራችን ሰላምና ክብር...