Saturday, May 25, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናበ74 ኢትዮጵያውያን ምክንያት ታንዛኒያና ኬንያ እየተወዛገቡ ነው

በ74 ኢትዮጵያውያን ምክንያት ታንዛኒያና ኬንያ እየተወዛገቡ ነው

ቀን:

– የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት መረጃ የለውም

ታንዛኒያ ውስጥ በሕገወጥ መንገድ ገብተዋል ተብለው ተፈርዶባቸው የእስር ጊዜያቸውን የጨረሱ 74 ኢትዮጵያውያንን፣ የታንዛኒያ መንግሥት በኬንያ ድንበር ግዛት ላይ በመበተኑ የኬንያ መንግሥት ባለሥልጣናትን አስቆጣ፡፡

የኬንያ የሚዲያ ተቋማት እንደዘገቡት በታንዛኒያ ፍርድ ቤት ተፈርዶባቸው የእስር ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን 74 ኢትዮጵያውያን ወደ ትውልድ ወይም የዜግነት አገራቸው መመለስ ሲገባቸው፣ ታንዛኒያንና ኬንያን በምታዋስነው የኬንያ ድንበር ግዛት በሆነችው ታኢታ ታቬታ የታንዛኒያ መንግሥት ባለፈው ማክሰኞ በትኗቸዋል፡፡

- Advertisement -

የኬንያ የስደተኞች ጉዳይ ኦፈሲር የታንዛኒያን ድርጊት ያወገዘ ከመሆኑም በላይ፣ ታንዛኒያ በዓለም አቀፍ ሕግ ያለባትን ተጠያቂነት ኬንያ የመሸከም ግዴታ የለባትም ብለዋል፡፡

የታኢታ ታቬታ ግዛት ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ሔንሪ ዋፋላ ለኬንያ ሚዲያ ተቋማት እንደገለጹት፣ ፖሊስና የስደተኞች ጉዳይ ሠራተኞች ኢትዮጵያውያኑ ካሉበት ቦታ አልፈው ወደ ኬንያ እንዳይገቡ በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያውያኑ በአሁኑ ወቅት በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ አይታወቅም፡፡ ጉዳዩን በተመለከተ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ተወልደ ሙሉጌታ ተጠይቀው መረጃ እንደሌላቸው ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ በታንዛኒያ እስካሁን ኤምባሲ አልከፈተችም፡፡ በመሆኑም በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ታንዛኒያንም ደርቦ እንደሚሠራ የተገኙት መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ በርካታ ኢትዮጵያውያን ወደ ደቡብ አፍሪካ በሚያደርጉት የስደት ጉዞ መሸጋገሪያ ከሆኑ አገሮች መካከል አንዷ ታንዛኒያ መሆኗ ይጠቀሳል፡፡

 

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የማዳበሪያ አቅርቦትና ውጣ ውረዱ

በቅፅል ስሙ “The Father of Chemical Warfare” እየተባለ የሚጠራው...

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የትርፍ ምጣኔውን ከ70 በመቶ በላይ አሳደገ

ከሁለቱ መንግሥታዊ ባንኮች መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ...