Friday, June 9, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየአርቲስት ፍቃዱ ተክለ ማርያም ቀብር ተፈጸመ

የአርቲስት ፍቃዱ ተክለ ማርያም ቀብር ተፈጸመ

ቀን:

ማክሰኞ ሐምሌ 24 ቀን 2010 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው የቴአትር ባለሙያው ፍቃዱ ተክለ ማርያም የቀብር ሥነ ሥርዓት ሐሙስ ሐምሌ 26 ቀን 2010 ዓ.ም. በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል፡፡

ባለፉት 40 ዓመታት በኢትዮጵያ ቴአትርና የቴሌቪዥን ድራማዎች ላይ አሻራውን ማሳረፉ የሚመሰከርለት ፍቃዱ፣ ሁለቱም ኩላሊቶቹ ሥራ በማቆማቸው ሕክምና እንዲያገኝ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችና መንግሥት ከፍተኛ ጥረቶችን ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡ ይሁንና፣ ለሕክምናው የተዋጣውን ገንዘብ  በተመሳሳይ ሕመም ለምትሰቃይ የ18 ዓመት ወጣት ሕክምና እንዲውል ሰጥቶ ነበር፡፡ ሆኖም መንግሥት ሙሉ በሙሉ የሕክምና ወጪውን ችሎ ለማሳከም መዘጋጀቱን አስታውቆ ነበር፡፡

ይሁንና ሕይወቱ እስካረፈበት ጊዜ ድረስ ኩላሊቶቹን የማስቀየር ሕክምና እንዳልጀመረ ተነግሯል፡፡

አርቲስት ፍቃዱ በወልዲያ የሚገኝ ቤተ ክርስቲያን ጸበል ለመጠመቅ ሄዶ በዛው ማረፉና አስከሬኑም ወደ አዲስ አበባ ተጭኖ መምጣቱም ታውቋል፡፡ የቀብር ሥነ ሥርዓቱ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ከመፈጸሙ አስቀድሞ በብሔራዊ ቴአትር የክብር አሸኛኘት የተደረገለት ሲሆን፣ በዚህም ዝግጅት ላይ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና የሙያ አጋሮቹ ተገኝተዋል፡፡

በቅድስት ሥላሴ በነበረው የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይም በተመሳሳይ በርካታ ሰዎችና የሙያ አጋሮቹ የተገኙ ሲሆን፣ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና የኃይማኖት አባቶችም ተገኝተዋል፡፡

አርቲስት ፍቃዱ በ1948 ዓ.ም. ተወልዶ፣ በ62ዓመቱ አርፏል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ