- 1 ኩባያ ዓሣ ተቀቅሎ የተፈጨ
- 2 የሾርባ ማንኪያ የፉርኖ ዱቄት
- 1 ኩባያ ድንች ተቀቅሎ የተፈጨ
- 1 ዕንቁላል በመጠኑ የተመታ
- 1 የሻይ ማንኪያ ሽንኩርት የተከተፈ
- ¼ የሻይ ማንኪያ ጨው
- 1 የሻይ ማንኪያ የሎሚ ጭማቂ
- 1 ኩባያ ቅቤ
- ቁንዶ በርበሬ
አሠራር
- ዓሣ ሽንኩርት፣ የሎሚ ጭማቂ፣ ጨው፣ ቁንዶ በርበሬና ድንች በጎድጓዳ ሳህን ማደባለቅ፡፡
- በተራ ቁጥር 1 የተዘጋጀውን በክቡ አድቦልቡሎ ዱቄት እላዩ ላይ መነስነስ፡፡
- መጥበሻ ላይ ቅቤ አቅልጦ የተዘጋጀውን የዓሣ ድብልቅ አገላብጦ መጥበስ፡፡ አራት ሰው ይመግባል፡፡
– ጽጌ ዕቁባሚካኤል ‹‹የእናት ጓዳ›› (1984)