በካዛኪስታን ሜዳማ አካባቢ ላይ የሚኖረው ሴይጋ አንቴሎፕ ከዝርያዎች ልዩ የሚያደርገው አንድ ነገር አለ፡፡ አፍንጫው ያገኘውን አየር እየሳበ ወደ ውስጥ ከማስገባት ይልቅ፣ ቀዝቃዛውንም ሙቀቱንም ተቀብሎ ሙቀቱን አመጣጥኖ ነው ወደ ውስጥ የሚልከው፡፡ የማሽተትና የሙቀት የማመጣጠን ሥራ ደርቦ የሚሠራ አፍንጫ ባለቤት የሆነው ይህ አንቴሎፕ በቀላሉ በሰዎች ዕይታ ውስጥ የማይገባና የመጥፋት አደጋ የተጋረጠበት ነው፡፡