ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም. የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የሥራ እንቅስቃሴዎችን ለመደገፍ በወጡ ሠልፈኞች ላይ በደረሰው የቦምብ ጥቃት ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር የዋሉ ግለሰቦች ላይ እየተካሄደ የነበረው ምርመራ መጠናቀቁን፣ የፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቡድን ለፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት አስታወቀ፡፡
ዓርብ ሐምሌ 27 ቀን 2010 ዓ.ም. የወንጀል ምርመራ ቡድኑ እንዳስታወቀው ምርመራውን አጠናቅቆ መዝገቡን ለጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ሰጥቷል፡፡
ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግም መዝገቡን መቀበሉን ለፍርድ ቤት አረጋግጦ፣ ‹‹በጣም ሰፊና ውስብስብ በመሆኑ በሕጉ መሠረት የ15 ቀናት የክስ መመሥረቻ ጊዜ እንዲሰጠን፤›› ብሎ በመጠየቁ ተፈቅዶለታል፡፡