የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ግዙፍ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ወደ ግል እንዲዛወሩ በወሰነው መሠረት፣ መንግሥትን የሚያማክር 21 አባላት ያሉት አማካሪ ምክር ቤት በጠቅላይ ሚኒስት ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ተቋቋመ፡፡
ምክር ቤቱም ሒደቱ ተጠያቂነትና ግልጽነት በነገሠበት ሁኔታ እንዲከናወን የማድረግ ኃላፊነት ተጥሎበታል፡፡
በዚህም መሠረት የአማካሪ ምክር ቤቱ አባላት እንዲሆኑ የተመረጡት አቶ ኢየሲስ ወርቅ ዛፉ፣ አቶ ዘላለም መለሰ፣ ዓለማየሁ ሥዩም (ዶ/ር)፣ ወ/ሮ መዓዛ ብሩ፣ አቶ በቀለ ጉለታ፣ አቶ አበበ አዕምሮ ሥላሴ፣ አቶ ልደቱ አያሌው፣ በየነ ጴጥሮስ (ፕሮፌሰር)፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ ወ/ሮ ሳራ አበራ፣ ዓይናለም መገርሳ (ዶ/ር)፣ ጣሰው ወልደ ሃና (ፕሮፌሰር)፣ ፀጋዬ በርሄ (ዶ/ር)፣ ተገኘወርቅ ጌቱ (ዶ/ር)፣ አቶ ካሲ ከበደ፣ አቶ ግርማ ሰይፉ፣ አቶ ሌንጮ ባቲ፣አብርሐም ተከስተ (ዶ/ር)፣ ይናገር ደሴ (ዶ/ር)፣ አቶ ተክለወልድ አጥናፉና አምባሳደር ግርማ ብሩ ናቸው፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ በትዊተር ገጻቸው የምክር ቤቱን መቋቋም አረጋግጠዋል፡፡