Sunday, June 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በመከላከያ የበላይነት ተጠናቀቀ

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በመከላከያ የበላይነት ተጠናቀቀ

ቀን:

ፌዴሬሽኑ 1.2 ሚሊዮን ብር ወጪ አድርጓል

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በበላይነት ከሚመራቸው መርሐ ግብሮች መካከል በየዓመቱ የሚከናወነው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተጠቃሽ ነው፡፡ ዘንድሮ ለ45ኛ ጊዜ ከሚያዝያ 12 እስከ 16 ቀን 2008 ዓ.ም. ድረስ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ሻምፒዮና የመከላከያ አትሌቲክስ ክለብ 362 ነጥብ በማግኘት ውድድሩን በበላይነት አጠናቋል፡፡

ለተከታታይ አምስት ቀናት ሲካሄድ በሰነበተው የኢትዮጵያ አትሌቲከስ ሻምፒዮና በርካታ የሜዳና የመም (የትራክ) ተግባራት አከናውኗል፡፡ በዚሁ መሠረት በሻምፒዮናው መክፈቻ ዕለት በተከናወነው የሴቶች 10,000 ሜትር የኦሮሚያ ፖሊሷ ሹሬ ደምሴ በአሸናፊነት አጠናቃለች፡፡ አትሌቷ ርቀቱን ለማጠናቀቅም 33 ደቂቃ 24.47 ሰከንድ ሲወስድባት፣ ሁለተኛና ሦስተኛ በመሆን አሁንም ከኦሮሚያ ፖሊስ 33፡26.36 እና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አያንቱ ኢደሳ 33፡31.04 ተከታትለው በመግባት የሜዳልያ ባለቤት ሆነዋል፡፡ በዕለቱ ፍጻሜ ካገኙ የሜዳ ተግባራት መካከል የመከላከያዋ አመለ ይበልጣል በአሎሎ ውርወራ የወርቅ ሜዳሊያ ያገኘችበት ይጠቀሳል፡፡ በወንዶች ሥሉስ ዝላይም የመከላከያው ኦዲር ጉር አሸናፊ ሲያሸንፍ በሴቶች ከፍታ ዝላይ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አርአያት ዲቦ እንዲሁም በወንዶች ጦር ውርወራ የመከላከያ ኤቶ ኡኬሎ አሸናፊዎች ሆነዋል፡፡

በሁለተኛው ቀን የውድድር መርሐ ግብር ደግሞ የሜዳ ተግባራትን ጨምሮ ስምንት የውድድር ዓይነቶች ፍፃሜ ያገኙ ናቸው፡፡ በዚሁ መሠረት በስፖርት ቤተሰቡ ዘንድ ትልቅ ግምት ተሰጥቶት በነበረው የወንዶች 10,000 ሜትር ሲሆን፣ ከትራንስ ኢትዮጵያ ክለብ ያልተጠበቀው አባዲ ሐዲስ በርቀቱ ለመጀመሪያ ጊዜ አሸናፊ የሆነበትን ውጤት አስመዝግቧል፡፡ አትሌቱ ርቀቱን ለማጠናቀቅ የወሰደበት ጊዜም 28፡43.11 ሆኗል፡፡ በውድድሩ ታዋቂዎቹ ኢብራሂም ጄይላንና ኢማና መርጊያ ተሳታፊዎች ነበሩ፡፡

ውድድሩን ሁለተኛ በመሆን ያጠናቀቀው ደግሞ ከተክለብርሃን አምባዬ አትሌቲክስ ክለብ የቀረበው ፍቃዱ ሐፍቱ 28፡49.00 ሲሆን፣ ከኦሮሚያ ክልል የተወከለው በንሳ ዳዲ ደግሞ 28፡49.72 በሆነ ጊዜ አጠናቆ ሦስተኛ በመሆን ገብቷል፡፡ በዕለቱ በተደረጉ ሌሎች የፍጻሜ ውድድሮች በ800 ሜትር ወንዶች ከብሔራዊ ቡድን ባጫ ሞርካ በ1፣48፣00 በሴቶች ትዕግስት ከተማ ከኦሮሚያ 2፡04.65 የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡  በ100 ሜትር ሴቶች ጽጌ ከበደ ከኦሮሚያ (12፡09 ሰከንድ) በወንዶች በድሩ መሐመድ ከመከላከያ (10፡48) አሸናፊ ሆነዋል፡፡ በሜዳ ተግባራት ደግሞ በሴቶች ርዝመት ዝላይ ኝቦሎ ኡግዳ ከመከላከያ፣ በወንዶች ዲስከስ ውርወራ ከሲዳማ ቡና ማሙሽ ታየ፣ በወንዶች ምርኩዝ ዝላይ ከመከላከያ ሳምሶን በሻህ የወርቅ ሜዳዲያ ባለቤቶች ሆነዋል፡፡

በውድድሩ የሦስተኛ ቀን ውሎ በ400 ሜትር ሴቶች ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ትዕግስት ታማኙ፣ በወንዶች ደግሞ የኦሮሚያው አብዱራህማን አብዱ አሸናፊዎች ሲሆኑ፣ በአራተኛ ቀን ውሎው  በ3,000 ሜትር መሰናክል ሴቶች ከፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ወይንሽት አንሳ በአሸናፊነት አጠናቃለች፡፡ ሁለተኛና ሦስተኛ በመሆን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብርቱካን አዳሙና ከአማራ ክልል አገሬ በላቸው ሆነዋል፡፡ የተወዳዳሪዎቹ ሰዓት በዳኞች  ምክንያት ለጊዜው መግለጽ እንዳልተቻለ ነው የተነገረው፡፡ በውድድሩ አምስተኛ ቀን ውሎ በርከት ያሉ የፍጻሜ ውድድሮች ተከናውነዋል፡፡ በዋናነት ከተደረጉት በሁለቱም ጾታ የ5,000 ሜትር፣ የ1,500 ሜትርና በወንዶች 3,000 ሜትር መሰናክል ተጠቃሽ ናቸው፡፡ በዚሁ መሠረት በወንዶች 3,000 ሜትር መሰናክል ከመከላከያ ታፈሰ ሰቦቃ፣ ከኦሮሚያ ጫላ ባዩና ጅግሳ ቶሎሳ ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ አጠናቀዋል፡፡ የውድድሩ ሰዓት አልተገለጸም፡፡

በወንዶች 5,000 ሜትር የመከላከያው ጌታነህ ሞላ፣ ከኦሮሚያ ደጀን ደበላና ከደቡብ ክልል ሰለሞን ቢረጋ የውድድሩ አሸናፊዎች ሆነዋል፡፡ በሴቶች መካከል በተደረገው ተመሳሳይ ፉክክር ደግሞ ከኦሮሚያ ዳራ ዴዳ 16፤09.06፣ ከመስፍን ኢንጂነሪንግ ቅዱሳን ዓለማ 16፡15.72 እና ከኦሮሚያ ፖሊሰ መስከረም ማሞ 16፡17.14 ተከታትለው በመግባት ያጠናቀቁ አትሌቶች ናቸው፡፡

በ1,500 ሜትር ሴቶች በሱ ዳዶ 4፡08.16 ፋንቱ ወርቁ 4፡11.50 እና አዳነች አንሳ 4፡11.74 ሦስቱም ከኦሮሚያ ክልል ተከታትለው በመግባት አሸናፊዎች ሆነዋል፡፡ በወንዶች መካከል በተደረገው ተመሳሳይ ፉክክር ደግሞ ከኦሮሚያ ፖሊስ አማን ወጤ 3፡40.32፣ ተሬሳ ቶሎሳ ከኦሮሚያ ክልል 3፡40.81 እና ከአማራ ክልል ዘመኑ አዲስ 3፡41.15 አሸናፊዎች ናቸው፡፡ ውድድሩን በበላይነት የሚመራው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለሻምፒዮናው ከ1.2 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ማድረጉም ተመልክቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አወዛጋቢው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ጉዳይ

በኢትዮጵያ የሕገ መንግሥት ማሻሻል ጉዳይ ከፍተኛ የፖለቲካ ውዝግብ የሚቀሰቀስበት...

 መፍትሔ  ያላዘለው  የጎዳና  መደብሮችን  ማፍረስ

በአበበ ፍቅር ያለፉት ስድስት ዓመታት በርካቶች በግጭቶችና በመፈናቀሎች በከፍተኛ ሁኔታ...

የተናደው ከቀደምቱ አንዱ የነበረው የአዲስ አበባ ታሪካዊ ሕንፃ

ዳግማዊ አፄ ምኒልክ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ መናገሻ ከተማቸውን...

የአከርካሪ አጥንት ሕክምናን ከፍ ያደረገው ‘ካይሮፕራክቲክ’

በአፍሪካ ከጀርባ ሕመም ጋር በተያያዘ በርካታ ሰዎች ለከፍተኛ የአካል...