Monday, June 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

‹‹ውሻ በአንቀልባ!›› በአዲስ አበባ ጎዳና

ትኩስ ፅሁፎች

…መኖር ሰዉ ፈራ
               በኃይለ ልዑል ካሣ
መኖር ሰዉ ፈራ÷መፈጠሩን ጠላ።
መታፈር መከበር÷መደጋገፍ ተራ
መዋረድ መደፈር÷በዓለም እየደራ።
ድንበር ተደፈረ÷ወሰን አጋጅ ቀረ።
መንጋው በበረቱ እየተሸበረ
የቀድሞው ህላዌ÷እጅ እግሩ ታሠረ።
በቀል ቂም አርግዞ÷ልቡ ሁሉ ሻከረ
ደሙ እንደ በረዶ÷እየተጋገረ።
መኖር ሰዉ ፈራ÷መፈጠሩን ጠላ።
መታፈር መከበር÷መደጋገፍ ተራ
መዋረድ መደፈር÷በዓለም እየደራ።
በከንቱ ተግባሩ÷በታካቹ አዋሉ
ጥሩ አነጋገሩ÷ቢለይ ኅብረ ቃሉ
ሰዉ በማበሩ÷ሕዝቡ በመኖሩ
ባ‘ዘን በደስታ÷ይሸመጋገሉ
ባ‘ለም በመከራ÷ይቅር ይባባሉ።
ምክንያቱም
እግዜርን ‘ሚፈሩ÷ድንበሩን አይዘሉ።
የመሰናሰሉ÷የመቻቻል ባህሉ
እኩል ሳለ ጥቅሙ
የድንበሩ አጥሩ÷የአጥሩ ችካሉ
ግና መነቅነቁ÷ግና መነቀሉ
ዳሩ ተመሀሉ÷ኧረ ምን በደሉ?
         ሚያዝያ 9 ቀን 2008 ዓ.ም.
                አዲስ አበባ

************

ምግብ እንጂ ዕፅ አነፍንፈው የማይዙት የአውሮፕላን ማረፊያ ውሾች

1.7 ሚሊዮን ዶላር የወጣባቸው የማንችስተር አውሮፕላን ማረፊያ አነፍናፊ ውሾች፣ አይብና ሥጋ እንጂ አደንዛዥ ዕፅ በመያዝ ጐበዝ እንዳልሆኑ የሮይተርስ ዘገባ ያመለክታል፡፡ የተጠቀሰው ከፍተኛ ገንዘብ የፈሰሰባቸው ስድስት አነፍናፊ ውሾች ላይ ለሰባት ወራት የተደረገ ክትትል እንደሚያሳየው ውሾቹ እንደ ሔሮይንና ኮኬይን ያሉ ዕፆችን አነፍንፎ ከመያዝ ይልቅ ምግብ መያዝ ይቀላቸዋል፡፡

ውሾቹ እንዲሠለጥኑ የሚደረገው እንደዚሁ ሳይሆን ዕፅ፣ ትምባሆ (ቶባኮ)፣ ገንዘብና ሥጋ እየተባለ የተጠቀሱትን ነገሮች በመለየት ልዩ ችሎታ እንዲኖራቸው ተደርጎ ነው፡፡ ቢሆንም ግን በዓመት 22 ሚሊዮን መንገደኞች በሚጠቀሙት ማንችስተር አውሮፕላን ማረፊያ የሚገኙት እነዚህ ስድስት ውሾች አነፍንፈው ማስያዝ የቻሉት 46 ኪሎ ግራም ሲጋራና 18 ኪሎ ግራም ሥጋ ሲሆን ምንም ዓይነት አደንዛዥ ዕፅ ይዘው አያውቁም፡፡

************

ውሻውን ለማዳን የ13ኛ ፎቅ ጠርዝ ላይ ለሰዓት የተንጠለጠለ

በኮሎምቢያ በሚገኝ አፓርትመንት ላይ ነዋሪ የሆነው ዳቪላ ውሻውን ለማዳን ሲል 13ኛ ፎቅ ጠርዝ ላይ ለሰዓት ያህል ተንጠልጥሎ መቆየቱን ዩፒአይ ዘግቧል፡፡

ጄሚኒዝ ውሻው ከጎረቤቱ ግድግዳ ጠርዝ ላይ ቆማ ለመውረድም፣ ወደቤቱ ለመመለስም ተቸግራ ነበር ድንገት ያያት፡፡ በመሆኑም ቤቱ ከምድር ያለውን ርቀት ከግምት ሳያስገባ ጠርዝ እየተቆናጠጠ ውሻዋ ጋር ደርሶ በእጁ ደግፎ ይይዛታል፡፡

ሁኔታውን ከምድር ሆነው የተመለከቱ መንገደኞች እየጯጯሁ ፍራሽ የዘረጉ ሲሆን፣ እጮኛውም በድርጊቱ ተናዳ ስትቆጣ ነበር፡፡ ጄሚኒዝ በጎረቤቱ የበረንዳ ጠርዝ በኩል ለአንድ ሰዓት ያህል በመንጠላጠልና ውሻውን ደግፎ በመያዝ፣ የውሻውን ሕይወት አትርፏል፡፡ ጎረቤቱ ከአንድ ሰዓት ቆይታ በኋላ በስፍራው ተገኝተው በግድግዳው በኩል ያለውን መስኮት በመክፈት እንዲገባ በማድረጋቸው የሁለቱም ሕይወት ሊተርፍ ችሏል፡፡ ጄሚኒዝ እንደሚለው፣ ውሻው ከፎቁ ጫፍ ላይ ሆና መጨነቋን እንጂ በእሱ ላይ ምን ሊደርስ እንደሚችል በወቅቱ አልታየውም ነበር፡፡

‹‹ክስተቱ ካለፈ በኋላ በአዕምሮዬ የተመላለሱት ሐሳቦች ነበሩ፡፡ ማንም ሰውም ባደረግኩት ሥራ አላደነቀኝም፡፡ በተለይ እናቴ ነቅፋኛለች፤›› ብሏል፡፡

**************

በተወለደበት ያረፈው ዊልያም ሼክስፔር 400ኛ ልደት

ዊልያም ሼክስፒር (እ.ኤ.አ. 1564-1616) መቼ እንደተወለደ አነጋጋሪ የነበረ ቢሆንም ከረዥም ጊዜ ወዲህ ተቀባይነትን ያገኘው ኤፕሪል 23 ቀን ነው፡፡ እንዳጋጣሚ ዕለቱ ያረፈበትም ነበር፡፡ እንዲሁም ዕለቱ በኢንግላንድ የአገሪቱ ‹‹ጠባቂ ቅዱስ›› (Patron Saint) ቅዱስ ጊዮርጊስ መታሰቢያ ነው፡፡ ባለፈው ቅዳሜ ሚያዝያ 15 ቀን 2008 ዓ.ም. የሼክስፔር አራት መቶኛ ዓመት ዕረፍቱ በአገሪቱ የተዘከረው ውርስና ቅርሱን በማስተንተን ነበር፡፡ ገጣሚ፣ ጸሐፌ ተውኔትና ተዋናይ የነበረው እንግሊዛዊው ሼክስፒር ከወንዙ አልፎ ዝናው በዓለም የናኘለትን በርካታ ሥራዎቹን ትቶ አልፏል፡፡ የተለያዩ አገሮች በየራሳቸው ቋንቋዎች ከተውኔቱ፣ ከግጥሙ እየዘገኑ ተርጉመዋል፡፡ ከነዚህም መካከል ኢትዮጵያ ትገኝበታለች፡፡ አማርኛና ትግርኛ ቋንቋዎች ከሼክስፒር ትሩፋቶች ተቋዳሽ መሆናቸው የሚያሳዩ መጻሕፍትን ተመልክተናል፡፡ ፀጋዬ ገብረመድኅን፣ ከበደ ሚካኤል፣ በቀለ ተገኝ፣ ሳራ ወርቅነህ፣ ወደ አማርኛ፤ ኪዳኔ ወልደየሱስ፣ ሚካኤል ገብረሕይወት፣ ኃይለመለኮት መዋዕል ወደ ትግርኛ ተርጉመዋል፡፡ ጸሐፌ ተውኔትና ባለቅኔ ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድኅን ከተረጐማቸውና ከተመደረኩት መካከል ኦቴሎ፣ ማክቤዝ፣ ሐምሌት ይጠቀሳሉ፡፡ የጸሐፌ ተውኔትና ባለቅኔው ከበደ ሚካኤል ሮሚዎና ዡልየት፣ የበቀለ ተገኝ ዩልዮስ ቄሳር  ትርጉሞችም ይነሳሉ፡፡

የተለያዩ የአውሮፓና የአሜሪካ ገጣሚያንን ሥራ ከየልሳናቸው ወደ አማርኛ የመለሰው ዳዊት ዘኪሮስ (በሁለተኛ ስሙ የከበደ ሚካኤል አድናቂ ነበርና ‹‹ከበደ ዳግማዊ›› ተብሎ ይጠራ ነበር) ከተረጐማቸው የሼክስፒር ግጥሞች መካከል ሶኔቶች (መወድሶች) ይጠቀሳሉ፡፡ ሶኔት 116 የሼክስፒር ሶኔት ማደናቀፍ ይቅር እውነተኛ ልቦች ሲጋቡ ተፋቅረው (Sonnet 116 Shakespeare’s Sonnets: Let me not to the marriage of true minds) አንዱ ነው፡፡

ማደናቀፍ ይቅር እውነተኛ ልቦች ሲጋቡ ተፋቅረው

ፍቅር አይሆን ፍቅር የሚለዋወጠው

ለውጥ አገኘሁ ብሎ የሚቀባጥር

ካንፏቃቂው ጋራ አብሮ የሚዞር

ዘላቂ መሪ ነው፤ መች እንዲህ ሆነና ማዕበል አየሁ ብሎ ፍንክች ይላትና

ላፈቀደው ቅርፊት ኮከቡ ይሆናል

ቁመቱም ቢለካ ዋጋስ ይኖዋል?

ፍቅር አይሞኝም፤ የጊዜ ሞኝ አይደል

ቀይ ከንፈሮችና ጉንጮች አየሁ ብሎ ስለማይታለል

በጥቂት ሰዓታት ወይም በቀኖችስ መች ይለዋወጣል

እስከምፅአት ድረስ ታግሶ ይዘልቃል፡፡

ቢመሰከርብኝ ስህተት ሆኖ ይህም፤

እኔም አልጻፍኩኝም፤ ሰው ፍቅር አያውቅም፡፡

  • ሔኖክ መደብር
- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች