Friday, December 8, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየኢትዮጵያ የአውሮፕላን አደጋ ምርመራ ቢሮ ገለልተኛ ሆኖ ሊቋቋም ነው

የኢትዮጵያ የአውሮፕላን አደጋ ምርመራ ቢሮ ገለልተኛ ሆኖ ሊቋቋም ነው

ቀን:

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ሥልጣን የነበረው የአውሮፕላን አደጋ ምርመራ ራሱን በቻለ ገለልተኛ ቢሮ እንዲደራጅ የሚያደርግ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ፡፡

የአውሮፕላን አደጋ ምርመራ ቢሮ በአሁኑ ወቅት የሚሰጠው በሲቪል አቪዬሽን በመሆኑና የሲቪል አቪዬሽን ተቋም የአቪዬሽን ሥራዎች ፈቃጅና ተቆጣጣሪ ስለሆነ፣ የአውሮፕላን አደጋ ምርመራን ለማከናወን ኢትዮጵያ አባል ከሆነችበት ዓለም አቀፍ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ይሁንታን አለማግኘቱ የረቂቅ አዋጁ አባሪ ማብራሪያ ያስረዳል፡፡

በመሆኑም ከሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን አስተዳደርና ቁጥጥር ውጪ ራሱን ችሎ ስለሚቋቋምበት አደረጃጀት እንዲያጠና የተቋቋመ ቡድን፣ የአውሮፕላን አደጋ ምርመራ በቢሮ ደረጃ ተዋቅሮ በፌዴራል ትራንስፖርት ሚኒስቴር ሥር እንዲቋቋም ባቀረበው ሐሳብ መሠረት ረቂቁ መዘጋጀቱን ያስረዳል፡፡

በረቂቅ አዋጁ እንደተመለከተው የሚቋቋመው ቢሮ የሚመለከተው በኢትዮጵያ የግዛት ክልል በሚደርስ የሲቪል አየር ትራንስፖርት አደጋና ከባድ የአደጋ አጋጣሚዎችን ብቻ ነው፡፡

የአውሮፕላን አደጋና ከባድ የአደጋ አጋጣሚ በሚከሰትበት ወቅት፣ በኢትዮጵያ ግዛት ክልል ውስጥ ያለና ስለአደጋው መረጃ ያለው ማንኛውም ዜጋ በአካባቢው ለሚገኝ አግባብነት ላለው መንግሥታዊ አካል ሪፖርት የማድረግ ግዴታ እንዳለበት በረቂቁ ተመልክቷል፡፡

የአውሮፕላን አደጋ ወይም ከባድ የአደጋ አጋጣሚ በአገር መከላከያ በተከለሉ ወታደራዊ ሥፍራዎች ውስጥ የደረሰ ከሆነ፣ ምርመራው የሚከናወነው የመከላከያ ሚኒስቴር ሲፈቅድ እንደሆነ በረቂቁ ሰፍሯል፡፡

የአገሪቱ የፖሊስና የአስተዳደር አካላት የአውሮፕላን አደጋና ከባድ የአደጋ አጋጣሚ ክስተት የተፈጠረበትን ቦታና አካባቢ፣ እንዲሁም ተያያዥነት ያላቸው ማናቸውንም ማስረጃዎች ባሉበት ሁኔታ ፈጥኖ የሕግ ከለላና ጥበቃ የማድረግ፣ የቢሮው መርማሪዎች በቦታው ሲደርሱ የማስረከብ ግዴታም በረቂቁ ተመልክቷል፡፡

ፓርላማው ረቂቅ አዋጁን ተመልክቶ ለዝርዝር ዕይታ ለትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቶታል፡፡   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...