Tuesday, March 5, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበጋምቤላ የተቀሰቀሰውን ግጭት ለማብረድ ሕዝባዊ ስብሰባዎች እየተካሄዱ ነው

በጋምቤላ የተቀሰቀሰውን ግጭት ለማብረድ ሕዝባዊ ስብሰባዎች እየተካሄዱ ነው

ቀን:

– 41 የደቡብ ሱዳን ስደተኞች በቁጥጥር ሥር ውለዋል

በጋምቤላ ክልል ውስጥ ሰሞኑን በነዋሪዎች ላይ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች በፈጸሙት ግድያ ምክንያት የተቀሰቀሰውን ግጭት ለማብረድ፣ የተለያዩ ሕዝባዊ ስብሰባዎች በመካሄድ ላይ ናቸው፡፡

የደቡብ ሱዳን ስደተኞች በጋምቤላ ክልል ነዋሪዎች ላይ በፈጸሙት ግድያ የተቆጣውንና ለበቀል የተነሳሳውን ሕዝብ የክልሉ መንግሥት፣ የፌዴራል ፖሊስና መከላከያ ሠራዊት በማረጋጋት የበቀል ዕርምጃ እንዳይፈጸም እየተደረገ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ መሰንበቻውን በጋምቤላ ክልል በተፈጸሙት ግድያዎች የተቆጣውን ሕዝብ ለማረጋጋትና በክልሉ የነገሠውን ውጥረት ለማርገብ፣ የፌዴራልና የክልሉ ባለሥልጣናት ሕዝባዊ ስብሰባዎችን ተመራጭ አድርገዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በጋምቤላ ክልል በጀዊ ስደተኞች ካምፕ የሚኖሩ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ሚያዝያ 13 ቀን 2008 ዓ.ም. በኢትዮጵያውያን ላይ ግድያ መፈጸማቸውን መዘገቡ ይታወሳል፡፡ በእነዚህ ዜጎች ላይ የተፈጸመው ግድያ ፍፁም ተቀባይነት የሌለው በመሆኑ፣ ሚያዝያ 16 ቀን 2008 ዓ.ም. የጋምቤላ ነዋሪዎች በከፍተኛ ቁጣ ለበቀል ተነስተው ነበር፡፡

ነገር ግን የክልሉ መንግሥት፣ የፌዴራል ፖሊስና የመከላከያ ሠራዊት በደቡብ ሱዳን ስደተኞችና በጋምቤላ ከተማ ነዋሪዎች መካከል በመግባት ሕዝቡን ማረጋጋታቸውን ከአካባቢው የወጡ መረጃዎች አመልክተዋል፡፡

የመከላከያ ሠራዊቱ ድርጊቱን የፈጸሙትን ለሕግ የሚያቀርብ መሆኑን በመግለጽ፣ የተቆጣውን ሕዝብ በማረጋጋቱ የከፋ ግጭት ሳይቀሰቀስ መቅረቱን ከሥፍራው የተገኙ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

የጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጋትሉዋክ ቱት ጉዳዩን በማስመልከት በሰጡት መግለጫ፣ አደጋው እንደደረሰ የተጠረጠሩ 41 ስደተኞች በቁጥጥር ሥር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ ነው፡፡

‹‹ሰሞኑን ከተፈጠረው ሁኔታ ጋር ተያይዞ በአካባቢው የታየውን አለመረጋጋት ወደ ነበረበት ለመመለስና ሰላምን ለማጠናከር፣ የክልሉ መንግሥት ከፌዴራል ፖሊስና ከመከላከያ ሠራዊት ጋር እየሠራ ነው፤›› በማለት አቶ ጋትሉዋክ አስረድተዋል፡፡

መንግሥት በጋምቤላ የተፈጠረውን አለመረጋጋት ለማብረድ ከወሰዳቸው ዕርምጃዎች መካከል የተለያዩ ስብሰባዎችን ማካሄድ አንዱ ነው፡፡

በዚህ መሠረት ከሚያዝያ 16 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ ከአገር ሽማግሌዎች፣ ከክልሉ አመራሮች፣ ከመንግሥት ሠራተኞችና ከነዋሪዎች ጋር የተለያዩ የሰላም ውይይቶች በመካሄድ ላይ ናቸው፡፡

ውይይቶቹን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፀጥታ አማካሪ አቶ ፀጋዬ በርኼን ጨምሮ፣ የፌዴራል መንግሥትና የክልሉ ባለሥልጣናት በመምራት ላይ ይገኛሉ፡፡

ከአካባቢው የወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት፣ ለችግሩ መፈጠር መንስዔው የአመራሮች ድክመት መሆኑን ተሰብሳቢዎች በመግለጽ ላይ ናቸው፡፡

አሁንም ቢሆን በክልሉ መሥሪያ ቤቶችና ትምህርት ቤቶች ከመዘጋታቸውም በላይ፣ የትራንስፖርትና የንግድ እንቅስቃሴ ተቀዛቅዟል፡፡ በጋምቤላ ክልል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተፈጠረው ውጥረት ምክንያት ሕዝቡም ዘላቂ መፍትሔ እንዲሰጠው እየጠየቀ ይገኛል፡፡

ሚያዝያ 7 ቀን 2008 ዓ.ም. ከደቡብ ሱዳን ተነስተው ድንበር አቋርጠው የገቡ የሙርሌ ታጣቂዎችና ሚያዝያ 13 ቀን 2008 ዓ.ም. ደግሞ በጋምቤላ የሚኖሩ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች በበርካታ ኢትዮጵያውያን ላይ ግድያ፣ ዘረፋና እገታ መፈጸማቸው ይታወሳል፡፡

አቶ ጋትሉዋክ እንደገለጹት፣ የሴቭ ዘ ችልድረን የውኃ ማጓጓዣ ቦቴ ተሽከርካሪ በሁለት ስደተኞች ሕፃናት ላይ ያደረሰው ድንገተኛ አደጋ ምክንያት ሆኖ ግጭቱ ተነስቷል፡፡

‹‹የተሽከርካሪ አደጋ በማንኛውም ሁኔታ በየትኛውም ቦታ ሊከሰት የሚችል ነው፡፡ መንግሥት ከአገራቸው ተሰደው ለመጡ ደቡብ ሱዳናውያን ሰብዓዊ ድጋፍና እንክብካቤ እያደረገ ባለበት ወቅት ይህ ጭፍጨፋ መከሰቱ አሳዛኝ ነው፤›› በማለት ተናግረዋል፡፡

በሙርሌ ታጣቂዎች ላይ እስካሁን ድረስ ከበባ መደረጉን ከሚያመለክተው መረጃ ውጪ፣ የታገቱት 108 ሕፃናት ዕጣ ፈንታን በተመለከተ ምንም የወጣ አዲስ መረጃ የለም፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር ሲጨምር የሚኒባስ ታክሲዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ሊታሰብበት ይገባል

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ የሚባለውን ድርሻ...

ሃምሳ ዓመታት ያስቆጠረው አብዮትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጣ ውረድ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች የዴሞክራሲ ለውጥ ጥያቄ የሚነሳው ከፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተፈጸመው ሕገወጥ ተግባር ምንድነው?

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ፣...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ውሳኔ ተላለፈ

ፕሬዚዳንቷና ዋና ጸሐፊው ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል ከአዲስ አበባ ንግድና...