Monday, October 3, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - ማስታወቂያ -
  - ማስታወቂያ -

  የፋሲካ ግብይት በግዙፉ የሰሜን ሸዋ ገበያ

  - ማስታወቂያ -

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  በፋሲካ በዓል ዋዜማ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ገበያተኞች ኮቱ ከተማ በሚገኘው የኮቱ ገበያ የከብት በረት በመገኘት ከፍተኛ ቀጥር ያላቸው የእርድ እንስሳት ግብይት ሲፈጽሙ ታይተዋል፡፡ በሳምንት ሰኞ ቀን የሚቆመው የኮቱ ገበያ፣ በሰሜን ሸዋ ዞን ከአዲስ አበባ 107 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ የኮቱ ገበያ በዞኑ ከሚገኙ ገበያዎች መካከል ከምንጃር ቀጥሎ ሁለተኛው ግዙፉ ገበያ ነው፡፡ ከአዳማ፣ ከአዲስ አበባ፣ ከሀገረ ማርያም፣ ከደብረ ብርሃንና ከሌሎችም አካባቢዎች በሚመጡ ገብያተኞች ዕውቅና አለው፡፡ በተለይ በቀንድ ከብት ግብይት ትልቅ ቦታ ያለው ይህ ገበያ፣ በዋጋ ረገድ ከአዲስ አበባ ብዙም ያልራቀ ጥሪ የሚጠራበት ነው፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች ሰሞኑን ከፋሲካ በዓል ጋር በተያያዘ የዋጋ ለውጥ መኖሩን ይናገራሉ፡፡ ከሰንጋ ገበያ በተጨማሪ በግ፣ ፍየል፣ ዶሮ፣ ቅቤ፣ እንቁላል፣ ጥራጥሬና አዝርዕት፣ አረቄ፣ አልባሳትና የሌሎችም በርካታ ሸቀጦች ግብይት ማካሄጃ ነው፡፡ ኮቱ ገበያ ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ጊዜ ጀምሮ ግብይት ሲካሄድበት የቆየ ግዙፍ ገበያ ሲሆን፣ የሸቀጣ ሸቀጥና የከብት ግብይት የሚካሄድባቸው ሁለት የገበያ ቦታዎችን የያዘ ትልቅ የገበያ ሥፍራ ነው፡፡ ገበያው በሚቆምበት ቀንም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ገበያተኛ ይገኛል፡፡ የኮቱ ገበያን አጠቃላይ የፋሲካ በዓል ዋዜማ ግብይት በተመለከተ የተጠናቀረውን ዘገባ ለመመልከት እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡

  - Advertisement -spot_img

  የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

  - ማስታወቂያ -