Sunday, February 5, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትእግር ኳስ ፌዴሬሽን በአዲስ ስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ መወያየት ጀምሯል

እግር ኳስ ፌዴሬሽን በአዲስ ስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ መወያየት ጀምሯል

ቀን:

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ላለፉት 50 ቀናት  ሲያስጠናው የቆየውን ስትራቴጂክ ዕቅድ በዘርፍ በዘርፍ በመመደብ ከባለድርሻዎችና ከየዘርፉ ልዩ ልዩ አካላት ጋር እየተወያየበት ይገኛል፡፡ የተናጠል ውይይቱ ዓርብ ነሐሴ 4 ቀን 2010 ዓ.ም. ያበቃል ተብሏል፡፡

በአቶ ኢሳያስ ጂራ የሚመራው አዲሱ የፌዴሬሽኑ አመራር የተቋሙን የወደፊት አካሄድ መስመር እያስያዘና አቅጣጫውን እያመላከተ ለመጓዝ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ የሚደግፉት እንዳሉ ሁሉ፣ የሚተቹትም አልታጡም፡፡ አመራሩ በስትራቴጂክ ዕቅድ ለመመራት ቁርጠኛ መሆኑ ብቻም ሳይሆን፣ በየዘርፉ ማለትም የሙያተኞች ምደባን ጨምሮ በቴክኒክ፣ በዳኞች እንዲሁም ልዩ ልዩ ንዑስ ኮሚቴዎች፣ የገበያና ፕሮሞሽን ወዘተ. ክፍሎችን አሠራርና የወደፊት አካሄድ አጥንቶ ዕቅድ መዘርጋቱ እንደሚደገፍ የሚስማሙት አካላት፣ በአንፃሩ በዚህ ሁናቴ አዲስ አመራር በመጣ ቁጥር የሥራ መጀመርያውን የስትራቴጂ ጥናት ላይ ሲያደርግ መቆየት የተለመደ አካሄድ ነበር፡፡ አዲሱ የፌዴሬሽኑ አመራርም በዚሁ ነባር አዙሪት ውስጥ መጋባቱ ብዙዎችን አላስደሰተም፡፡

በዚህ አካሄድ ላይ ቅሬታ ያላቸው አካላት እንደሚሉት ከሆነ፣ የአዲሱን ሥራ አስፈጻሚ በዚህ መነሻ ብቻ ከወዲሁ ለመተቸት መቻኮል ቢመስልም፣ አጀማመሩ ግን ከተለመደውና ከአሰልቺው ለውጥ አልባ አካሄድ ተርታ እንዳይሆን ስለሚያሠጋ ቅሬታቸውን ይገልጻሉ፡፡

በዚህ ረገድ አካሄዱ ቀደምቶቹ የመጡበትም ቢመስልም፣  የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጂራ በዚህ ጉዳይ ላይ በቅርቡ ከሪፖርተር ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ ‹‹ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ብዙዎች ከውጪ እንደሚመለከቱት ሳይሆን፣ ውስጡ ለአሠራር የማይመቹ እጅግ በጣም ውስብስብ ችግሮች የበዙበት ነው፡፡ ሥራ አመራሩ ከጽሕፈት ቤቱ፣ ጽሕፈት ቤቱ በሥሩ ካሉ ልዩ ልዩ ዲፓርትመንቶችና ንዑስ ክፍሎች ጋር ያላቸው የሥራ ኃላፊነትና ድርሻ  የተደበላለቀ ነው፡፡ በዚያ ላይ እግር ኳሱ ሰፊ የሕዝብ ፍላጎት ያለበት ነው፡፡ ይህን የሕዝብ ፍላጎት ለማሟላትም ደግሞ ተቋሙ ደረጃውን የጠበቀ መዋቅራዊ ቅርፅና ይዘት ሊኖረው ግድ ይላል፡፡ ለዚህም ሲባል በአገሪቱ ከሚገኙ ዩኒቨርሰቲዎች በቢኤችዲ ደረጃ ያሉ ሙያተኞች የተካተቱበት የጥናት ቡድን በማቋቋም አዲስ ስትራቴጂክ ዕቅድ በማስጠናት ላይ ነን፣›› ማለታቸው ይታወሳል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን ጨምሮ በአገሪቱ ከሁለት አሥርታት በላይ ይቆጠሩ ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ ከዚህ በመነሳት የአብዛኛው የኅብረተሰብ ክፍል ትኩረት እንዳለው የሚነገርለት እግር ኳሱ፣ በእያንዳንዱ ዲፓርትመንት ለቦታው የሚመጥን የባለሙያ ክፍተት እንዳለበት ይታመናል፡፡ በሌላ በኩል በወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ዘርፉን በሚመራው ክፍል ውስጥ ግን በመቶዎች የሚቆጠሩ ከፍተኛ ባለሙያዎች መኖራቸው ብቻም ሳይሆን ይህ ሁሉ ባለሙያ ስፖርቱን በመደገፍ ተጨባጭ ለውጥ እንዲመጣ የሚያስችል ሥራ ስለመሥራቱ ጥያቄ እየቀረበ ይገኛል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በጦርነቱ የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ የመገንባቱ ውጥን

በኢትዮጵያ በሰሜኑ ክፍል በሦስት ዙር ተካሄዶ በነበረው ጦርነት ምክንያት...

በርካታ ሰዎችን እያጠቁ የሚገኙት የሐሩራማ አካባቢ በሽታዎች

ትኩረት የሚሹ የትሮፒካል /ሐሩራማ በሽታዎች በአብዛኛው ተላላፊ ሲሆኑ፣ በዓይን...

ስለአገር ኢኮኖሚ ማሰብ የነበረባቸው ጭንቅላቶች በማያባሩ ግጭቶች ተነጥቀዋል!

አገራችን ኢትዮጵያ ውጪያዊና ውስጣዊ ፈተናዎቿ መብዛት ብዙ ዋጋ እያስከፈላት...