የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ ከሰጡት መግለጫ የተወሰደ፡፡ ሚኒስትሩ ሰኞ ሐምሌ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. በሰጡት መግለጫ፣ ሰሞኑን በሶማሌ ክልል ለደረሰው ችግር ተጠያቂዎች ለሕግ እንደሚቀርቡ፣ የመከላከያና የፌዴራል ፖሊስ ሰላም ለማስፈን መሰማራታቸውን አስታውቀዋል፡፡ የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ መሐመድ ዑመር (አብዲ ኢሌ) ከሥልጣናቸው ተነስተው፣ በምትካቸውም አቶ አህመድ አብዲ ተተክተዋል፡፡ በተፈጠረው ቀውስ የደረሰውን ጉዳት የሚያጣራ ኮሚቴ በፌዴራል ደረጃ መቋቋሙን ሚኒስትሩ ገልጸው፣ ውጤቱ በቅርቡ ለሕዝብ ይፋ ይሆናል ብለዋል፡፡