Tuesday, July 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህል‹‹ዜና መዋዕል›› ነባሩ የታሪክ መዘክር

‹‹ዜና መዋዕል›› ነባሩ የታሪክ መዘክር

ቀን:

ከድንጋይ ላይ ጽሑፍ በመነሳት ሁለት ሺሕ ዓመታት ግድም ያስቆጠረው የግዕዝ ሥነ ጽሑፍውስጡ ከያዛቸው የጽሑፍ ዓይነቶች አንዱ ሪክ አጻጻፍ ሥልትን የተከተለው ዜና መዋዕል ነው፡፡

በግዕዝ ሥነ ጽሑፍ ታሪክ ውስጥ ሁነኛ ሥፍራ ያለው የነገሥታት ውሎና ጉዞ የሚያትተው ዜና መዋዕል በተለይ ከ14ኛው ምዕት ጀምሮ ከሙያ መዋሉ ይገለጻል፡፡ ይሁን እንጂ ቀደም ባሉት ዘመናት በአክሱም ከመጀመርያ መቶ ዘመን ወዲህም ታሪክ ጠቀስ ጽሑፎች በድንጋይ ላይም ሆነ በብራና ላይ ለመጻፋቸው ማስረጃዎች አሉ፡፡

 የንጉሥ ኢዛና የድንጋይ ላይ ጽሑፎች በዘመኑ የተደረጉ ጦርነቶች፣ ገድሉን በንጉሡ ሥር የሚተዳደሩ አካባቢዎችና ኅብረተሰቡ ገዳይና፣ ምርኮው ሁሉ ተጽፈው ይታያሉ፡፡ እነዚህም የድንጋይ ላይ ጽሑፎች እንደ መጀመርያዎቹ ዜና መዋዕሎች የሚጠቅሷቸው ምሁራን አሉ፡፡

በሌላ በኩልም በቅዱስ ያሬድ ድርሰቶች በተለይም በድጓ ውስጥ ከዘመኑ የአገሪቱና የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጋር የተያያዙ ነጥቦች አሉበት፡፡ በአክሱምና በዛጉዌ ዘመነ መንግሥት ስለነበሩ ነገሥታት የተጻፉት እንደ ገድለ አብርሃ ወአጽብሐ፣ ገድለ ላሊበላና ገድለ ነአኩቶ ለአብ እንዲሁ ከታሪክ ጋር ተዘምዶ አላቸው፡፡

 የታሪክ ጽሑፍ ከጥንት ጀምሮ የነበረ ቢሆንም ታሪክን የሚጽፍ ሰውን በመመደብና ‹‹ጸሐፌ ትዕዛዝ›› በማለት ከሌሎች የጽሕፈት ሥራዎች ጋር ደርቦ የነገሥታቱን ታሪክ የሚጽፍ ክፍል የተቋቋመው በ14ኛው ምዕት ዓመት በነበሩት አፄ ዐምደ ጽዮን አማካይነት መሆኑም ይወሳል፡፡ ለኢትዮጵያ ታሪክ በምንጭነት የሚጠቀሱት ዜና መዋዕሎች እስከ 20ኛው ምዕት ድረስ በግዕዝ ተጽፈዋል፡፡ በ19ኛው ምዕት በአፄ ቴዎድሮስ፣ በአፄ ዮሐንስና በአፄ ምኒልክ ዘመን በአማርኛም ተጽፏል፡፡

 በግዕዝ የተጻፉት ዜና መዋዕሎች በዋና ዋና የአውሮፓ ቋንቋዎች (ፖርቱጋልኛ፣ ጣሊያንኛ፣ ጀርመንኛና ፈረንሣይኛ ወዘተ.) ከተተረጎሙ ዘመናትን አስቆጥረዋል፡፡ ከአፄ ዐምደ ጽዮን አንስቶ በርካታ ነገሥታት ዜና መዋዕላቸው በግዕዝ ቋንቋ ተጽፎላቸዋል፡፡ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን የጥንት ጽሑፎች ከፍተኛ ባለሙያ በነበሩት አቶ ዓለሙ ኃይሌ ትጋት ከ1998 ዓ.ም. ወዲህ ወደ አማርኛ አምስት ዜና መዋዕሎችን ተተርጉመዋል፡፡ እነሱም የአፄ ገላውዴዎስ፣ የአፄ ሠርፀ ድንግል፣ የአፄ ሱስንዮስ፣ የአፄ ዘርዐ ያዕቆብና የአፄ በዕደማርያም ናቸው፡፡

ዜና መዋዕል ጥንተሪክ በተመለከተ በተመራማሪዎች ‹‹ሪክ ጽሑፍ በኢትዮጵያ የተጀመረው 14ኛው ምዕት ዓመት በኋላ ነው›› የሚለውን አስተያየት የማይቀበሉ ምሁራን አሉ፡፡

ከነዚህም አንዱ አምባቸው ከበደ (/ር) ሲገልጹ ‹‹14ኛው ምዕት ዓመት በፊት የተጻፉ ዜና መዋዕሎች ባይገኙምሪክ ነክ ጽሑፎች ያለመኖራቸውን የሚያረጋግጥ አይመስለኝም፡፡ በዚያ ወቅት የተጻፉ ዜና መዋዕሎች የጊዜን ፈተና መቋቋም አቅቷቸው ወይም በሰው ሠራሽ አደጋዎች ጠፍተውንደሆነስ?›› ብለው ይጠይቃሉ፡፡

ከጥንዊት ኢትዮጵያስከ ዘመናችን የዘለቁ የጽሑፍ መረጃዎች የድንጋይ ላይ ጽሑፎችና ገድሎች ሲመረመሩ አክሱማውያንና ዛጉዬዎች ሪክ ጽሑፍ ባዕድንዳልነበሩ የሚያስረዱት አምባቸው (/ር)፣ በአክሱም ዘመን የተቀረፁ የድንጋይ ላይ ጽሑፎች በተለይም የኢዛና የድንጋይ ላይ ጽሑፎች ጠቃሚ ታሪካዊ መረጃዎችን የያዙና በአቀራረባቸውም በመካከለኛው ዘመን ከተጻፉት ዜና መዋዕሎች ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው መሆኑን ይጠቁማሉ፡፡

ጽሑፎቹ ያጻፈውን ንጉሥ ስመ መንግሥት፣ በሥሩ የሚተዳደሩትን ሕዝቦችና አገሮች፣ ያደረጋቸውን ጦርነቶች፣ የማረካቸውን ሰዎችና ንብረት ብዛትና ዓይነት የመሳሰሉና ሌሎች ጉዳዮችን በዝርዝር ይገልጻሉ፡፡

ዜና መዋዕል በብራና ጽሑፍ ላይ ለመጀመርያ ጊዜ የተገኘው በአፄ ዐምደ ጽዮን ዘመነ መንግሥት ነው፡፡ አፄው ዙፋን ላይ እንደወጣ የነገሥ~ ሪክ ንዲጻፍና በክብርንዲቀመጥ በመንግሥት አስተዳደር መዋቅር ውስጥ የነገሥቱን የጊዜያቸውንሪክ የሚጽፍ ‹‹የጸሐፌ ዛዝ›› ክፍልንዲቋቋም አድርጓል፡፡

የጸሐፌ ዛዙ ሥራ የንጉሡን ማኅተም መያዝ፣ ዛዞችንና ደብዳቤዎችን መጻፍና የነገሥቱን ዜና መዋዕሎች ማዘጋጀትንደሆነና በሥሩም የበታች ጸሐፊዎች ይገኙ ነበር፡፡

በአፄ ዐምደ ጽዮን ዘመን (1307 እስከ 1337) በንቡረ ዕድ ይስሐቅና በረዳቶቹ የተጻፈው ‹‹ክብረ ነገሥት›› ሪክ አንፃር ለመካከለኛው ዘመን ለኢትዮጵያሪክ ጸሐፊዎች የርዕዮተ ዓለምና የአጻጻፍ መመርያ ሆኖ ማገልገሉን አጥኚው ይገልጻሉ፡፡

በዘመነ ዐምደ ጽዮን የተጻፈው ዜና መዋዕል የንጉሡን የጦርነትሪክ የሚገልጽ ነበር፡፡ በዚህ ዘመን የተጀመረው የዜና መዋዕል መጻፍ ሥራ አንዳንዴ ለጥቂት ጊዜ ከመቋረጡ ሌላስከ ሃያኛው ምዕት ዓመት ድረስ ዘልቋል፡፡

በመጀመርያ የወጡት ዜና መዋዕሎች በማንንደተጻፉ የሚጠቁም ነገር በውስጣቸው አልያዙም፡፡ የደራሲን ስም ሳይገልጹ መጻፍ ሪክ ሥራዎች ላይ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ድርሰቶች ላይ የሚ ጉድለትንደነበር ያወሱት አጥኚው 16ኛው ምዕት ዓመት አጋማሽ ጀምሮ በመጠኑ እየተለወጠ በመሄዱ የአንዳንድ ዜና መዋዕል ደራሲዎች ስም ወቅ እንደቻለ በመጥቀስ ስሞቻቸውን ዘርዝረዋል፡፡

የአፄ ልብነ ድንግልን ዜና መዋዕል ሥነ ክርስቶስና ዘጰራቅሊጦስ የአፄ ሱስንዮስን አባ ምህርካ ድንግልና አዛዥ ጢኖ የአዕላፍ ሰገድ ዮሐንስን አዛዥ ሐዋርያ ክርስቶስ፣ የአድያም ሰገድ ኢያሱን አዛዥ ሐዋርያ ክርስቶስ፣ ዘወልደ ማርያምና ጸሐፌ ትዕዛዝ ሲኖዳ የአፄ በካፋን ጸሐፌ ትዕዛዝ ሲኖዳና ክንፈ ሚካኤል ናቸው፡፡  

የኢትዮጵያ ዜና መዋዕሎች የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮችን የሚያንፀባርቁ ብቻ ከዘመን ወደ ዘመን ለውጥያሳዩ መሄዳቸውን በመጀመርያ ወቅት ላይ የተጻፉት ዜና መዋዕሎች ከአፈሪክ ብዙም ያልተላቀቁ ስለነበር የተጋነነ አገላለጽ የሚበዛባቸውና የዘመን ቅደም ተከተልንምብዛም ንዳልጠበቁ ተመልቷል፡፡

16ኛው ምዕት ዓመት ጀምሮ ግን ዜና መዋዕሎች በይበልጥ ተጨባጭና የዘመናትንና የቀናትን ቅደም ተከተል የጠበቁ ሆነው ተገኝተዋል፡፡ በሌላ በኩልም የነገሥƒ ሪኮች ለየብቻቸው የቆሙ ሳይሆኑ ተያያዥነትና ተወራራሽነት ያላቸው መሆኑን ጸሐፊዎች በመገንዘባቸው የነገሥቱን ሪክ በማዋሃድ አንድ ወጥ የሆነ ሪክ መጽሐፍ ለመጻፍ አስችሏቸዋል፡፡ ለዚህም ጥሩ ምስክር የሚሆነው ‹‹አጭርሪክ ነገሥት›› የሚባለው ሪክ መጽሐፍንደሆነ አጥኚው ያብራራሉ፡፡

ዜና መዋዕሎች የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮችን የሚያስተናግዱ ቢሆንም በአወቃቀራቸው ግን ተመሳሳይነት አላቸው ማለት ይቻላል፡፡ አብዛኞቹ መግቢያ፣ ዋና አካልና (ትረካ) መደምደሚያ አላቸው፡፡ በመግቢያ ውስጥ ስለመጽሐፉ ይዘትና ዓላማ ወይም ስለደራሲው ብዙም ነገር አይገኝም፡፡ ጸሐፊው በአብዛኛው የሚጥረውግዚአብሔርን ለማመስገን ጽሑፉን በደህናንዲያስጨርሰው ለመማጸን፣ ሪኩን ባለቤት ገናናነት ለማሳየት ነው፡፡

ሁለተኛው ክፍል የዜና መዋዕል እዕምብርት ትረካው ነው፡፡ በአብዛኛዎቹ ዜና መዋዕሎች ውስጥ ትረካው በምዕራፎች የተከፋፈለ ነው፡፡ ዜና መዋዕሉንደ ሁኔታው ከንጉሡ ልደት፣ ዘውድ ከጫነበት ቀን፣ ወይም ከሱ በፊት ከነበረው ንጉሥ የመጨረሻ ዓመƒ ሊጀምር ይችላል፡፡

የዜና መዋዕሉ ጸሐፊምሪኩን የሚጽፈው የክርስትናን ሃይማኖት መሠረተ ሐሳቦች ተከትሎ ነው፡፡

የመካከለኛው ዘመን ሪክ ጸሐፊዎችንቅስቃሴያቸውን የሚያካሄዱት ‹‹ግዚአብሔር ሥልጣን ውጭ የሚፈጸም ነገር የለም›› የሚለውን የክርስትና ትምህርት መመሪያቸው በማድረግ ነበር፡፡ የሱስንዮስሪክ ጸሐፊ ‹‹የጊዜው ንጉሥ ግዚአብሔርን ፈቃድ ያስፈጽማል፣ ትዕዛዙን ያስከብራልንጂ በራሱ የሚሠራው የለውም›› እንዳለው ሪክን የሚመራውግዚአብሔር ንጂ ንጉሥ ወይም ሕዝብ አይደለም የሚል እምነት ጸሐፊዎቹ እንደነበራቸው አጥኚው ይተነትናሉ፡፡

የዜና መዋዕል ጸሐፊዎች ሪኩን የሚጽፉት ንጉሡን ማዕከል አድርገው በተጋነነ ገለጻ ንጉሡን ጸጋ የተላበሰ፣ በግርማ ሞገሱ አቻ የሌለው፣ በጀግንነቱ ወደር የማይገኝለት አድርገው ይገልጹል፡፡  ለመካከለኛው ዘመንሪክ ጸሐፊ ከንጉሥ ውጭሪክም አገርምንደሌለ የሚቀጥለው ቃል ጥሩ ማስረጃ ነው፡፡ ‹‹ንጉሥ ገላውዴዎስ ከሞተ በኋላ ሕዝቡ ተበተነ. . . እንደ ፀሐይ የበራች አገር ጨለመች፣ ብርሃኗ ጠፍቷልና፡፡ ቤቶችና አጥር ቅጥሮች ፈረሱ፣ ቋሚ የለምና፤ ረሃብ ጠና ምግብ የለምና፤ ጽምእ በዛ የሚጠጣ አልቋልና. . . የበጎችን ጠባቂ ገላውዴዎስን ወስዶልና፤›› 

በዜና መዋዕል ውስጥ ዋና ተዋናይ ሆኖ የሚቀርበው ንጉሡ ነው፡፡ የዘመኑ ታሪክ ጸሐፊ የንጉሡን ቅስቃሴ መሠረት አድርጎ ስለሚጽፈው ከዚያ ውጭ የሆኑ ነገሮች ብዙም ትኩረት አያገኙም ነበር፡፡

ስለአገሪቱ ኢኮኖሚ፣ ስለተራው ሕዝብ አኗኗርና ባህል የሚገልጹ መረጃዎች በዜና መዋዕሎች ብዙም አይገኙም፡፡ በዜና መዋዕል ውስጥ አንድን ሪክ ክስተት የሚገለጽበት የቀን አቆጣጠር የባሕረ ሐሳብ ሥርዓት ለየት ያለና ልዩ ልዩ አቆጣጠሮችን የሚከተል ነው፡፡ ለዚህ ማሳያንዲሆን ከአፄ ገላውዴዎስ ዜና መዋዕል ውስጥ የተገ ጽሑፍ አስረጅ ነው፡፡

‹‹. . .በሰባተኛው ወር፣ 7044 ዓመተ ዓለም የዚህ ታሪክ ባለቤት በነገሠ 12 ዓመት ምስጋና ይግባውና ችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው በሆነ 1544 ዓመት፣ በዓመተ ተንባላት 950 ዓመት. . . ፀሐይ በተውር መስኮት ላላቅ መዓርግ በአሥረኛው መዓርግ ሳለ፣ ማር ገላውዴዎስላቅ የሆነ አገልጋይን አፈወ ድንግልን በተመረጡ ካህናት ላይ አለቃ አድርጎ ሾመው፡፡››

መክረሚያውን በመምህር ዓለሙ ኃይሌ ተርጓሚነት ግዕዝና አማርኛውን ይዞ ታተመው የአፄ ሠርፀ ድንግል ዜና መዋዕል በራሱ በባለሪኩ ዘመነ መንግሥት የተጻፈና በአዋቂዎች ከፍተኛ ግምት የተሰጠው ነው፡፡ ተርጓሚው አቶ ዓለሙ  ንደገለጡት በአፄ ሠርፀ ድንግል ዘመነ መንግሥት በርካ ጠቃሚ ድርጊቶች መፈጸማቸው በልዩ ልዩ ዘርፍ፣ ነገረ ወግ ሳይቀር መጻሕፍት በግዕዝ ተጽፈዋል፡፡ ጃንሆይ መባል የተጀመረውም በሠርፀ ድንግል ዘመን መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...