ሩብ ኪሎ ሥጋ
ሦስት የሾርባ ማንኪያ ደርቆ የተፈጨ ዳቦ
ሦስት የሾርባ ማንኪያ ወተት ወይም ውኃ
አንድ የሻይ ማንኪያ ጨው
ሁለት እራስ ሽንኩርት መካከለኛ
አንድ እንቁላል
የተፈጨ ቁንዶ በርበሬ (በጥቂቱ መጨመር)
አሠራሩ
፩ የተፈጨውን ዳቦ በወተት መዘፍዘፍ
፪ ሥጋውን መፍጨት
፫ ሽንኩርቱን አድቆ መክተፍ
፬ ሥጋውን፤ ሽንኩርቱን፤ ቅመሙንና ጨውን አንድ ላይ አደባልቆ እተመታው እንቁላል ውስጥ መጨመር
፭ የተዘፈዘፈውን ዳቦ መጨመርና ማደባለቅ
፮ በእጅ እያድበለበሉ መጥበስ
- ገነት አጥናፉ ‹‹የቤት መሰናዶ በመልካም ዘዴ›› (1955)