Wednesday, September 28, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊበፋሺስት ኢጣሊያ ላይ የተገኘው ድል የአልማዝ ኢዮቤልዩ

  በፋሺስት ኢጣሊያ ላይ የተገኘው ድል የአልማዝ ኢዮቤልዩ

  ቀን:

  ኢትዮጵያን ከ80 ዓመታት በፊት በወረራ ይዞ የነበረው የፋሺስት ኢጣሊያ ሠራዊት ድል ከተመታ 75 ዓመታት ሞሉ፡፡ በጥቁሮች ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ120 ዓመታት በፊት ዓድዋ ላይ ድል በተመታው የኢጣሊያ ወራሪ ሠራዊት ቁጭት ውስጥ የገባው የቤኔቶ ሙሶሎኒ ፋሺስት ኢጣሊያ ሠራዊት፣ ከ40 ዓመታት ቆይታ በኋላ ሽንፈቱን ለመበቀልና ኢትዮጵያን በቅኝ ለመያዝ በ1928 ዓ.ም. ወረራውን ቢፈጽምም ያሰበው አልተሳካለትም፡፡ ፋሺስት ኢጣሊያ በወቅቱ የኢትዮጵያን ጦር ፈትቶ ለአምስት ዓመታት በከተሞች ተወስኖ እንዲቆይ ያስገደደው፣ በተለይ ጀግኖች አርበኞች የአገሪቱን ነፃነት ለማስከበርና የሕዝቡን ልዕልና ለማስጠበቅ ያደረጉትን ተጋድሎ ነው፡፡ በዓለም የተከለከለውን መርዝ ጋዝ (መስተርድ ጋዝ) በመጠቀም ያደረሰው ዕልቂት ለጀግኖች አርበኞች የማይታገሡት ጥቃት ነበር፡፡ ‹‹ኧረ ጥራኝ ዱሩ ኧረ ጥራኝ ጫካው…›› በማለት በዱር በገደሉ የዘመቱ ጀግኖች አርበኞች ከውስጥ አርበኞች ጋር በተቀናጀ ጥረት፣ በንጉሠ ነገሥቱ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዲፕሎማሲያዊ ትግል፣ እንዲሁም በፊት ከኢጣሊያ ጋር ባበረው በኋላ ፊቱን ባዞረው በእንግሊዝ ሠራዊት ድጋፍ ፋሺስት ኢጣሊያ አዲስ አበባን በያዘ በአምስት ዓመቱ ሚያዝያ 27 ቀን 1933 ዓ.ም. ድል መመታቱ ይታወሳል፡፡ የፋሺስት ኢጣሊያ ሠራዊት ድል የተመታበት 75ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓል ከሚያዝያ 19 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ድል በዓሉ ዕለት ሚያዝያ 27 ቀን 2008 ዓ.ም. ድረስ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው፡፡ የጥንታዊት ኢትዮጵያ አርበኞች ማኅበር ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር እየተከበረ ያለው የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓል፣ በመክፈቻው ዕለት፣ ‹‹እኔ ለአገሬ›› በሚል መሪ ቃል የባህል ሲምፖዚየም የተካሄደ ሲሆን፣ የፋሺስት ወረራን የተዋጉ አገራዊ የሥነ ቃል ትሩፋቶች፣ ሽለላ፣ ቀረርቶ፣ የፉከራ፣ መዲናና ዘለሰኛ ሙሾን ጨምሮ ጥናት ቀርቦበታል፡፡ የአርበኛነት ተጋድሎን የሚያሳይ ዓውደ ርዕይም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም ሲከፈት፣ ሚያዝያ 25 ቀን 2008 ዓ.ም. በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ የአርበኝነቱን ታሪክ የሚመለከት የታሪክ ሲምፖዚየም ተካሂዷል፡፡ በምሥሉ ላይ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር አባላት ይታያሉ፡፡       

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በቤንዚንና ነጭ ናፍጣ ላይ ጭማሪ ተደረገ

  ከዛሬ መስከረም 18 ቀን 2015 ዓም እኩለ ሌሊት ጀምሮ...

  ‹‹ለሰላምና ለዕርቅ መሸነፍ የለብንም›› ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ

  የሰው ልጅ ጠብን በዕርቅ፣ በደልን በይቅርታ፣ ድህነትን በልማት፣ ክህደትን...

  መፍትሔ አልባ ጉዞ የትም አያደርስም!

  ኢትዮጵያ ችግሮቿን የሚቀርፉ አገር በቀል መፍትሔዎች ላይ ማተኮር ይኖርባታል፡፡...

  ጦርነቱና ውስጣዊ ችግሮች

  መስከረም 14 ቀን 2015 ዓ.ም. የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ባወጣው...